መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልእ 12
12
የግብፅ ንጉሥ ሱስቀም ኢየሩሳሌምን እንደ ወረረ
(1ነገ. 14፥25-28)
1እንዲህም ሆነ፤ የሮብዓም መንግሥት በጸናች ጊዜ፥ እርሱም በበረታ ጊዜ፥ የእግዚአብሔርን ሕግ ረሳ፤ እስራኤልም ሁሉ ከእርሱ ጋር ረሱ። 2ሮብዓም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የግብፅ ንጉሥ ሱስቀም ወደ ኢየሩሳሌም መጣ። እግዚአብሔርን በድለዋልና፤ 3ሺህ ሁለት መቶ ሰረገሎችንና ስድሳ ሺህ ፈረሰኞችን ይዞ መጣ፤ ከእርሱም ጋር ከግብፅ ለመጣው ሕዝብ ቍጥር አልነበረውም፤ እነርሱም የልብያ ሰዎች፥ ሞጠግሊያናውያን፥#ዕብ. “ሱካውያን” ይላል። የኢትዮጵያም ሰዎች ነበሩ። 4በይሁዳም የነበሩትን ምሽጎች ከተሞች ያዙ። እስከ ኢየሩሳሌምም ደረሱ። 5ነቢዩም ሰማያ ወደ ሮብዓምና ከሱስቀም ሸሽተው በኢየሩሳሌም ወደ ተሰበሰቡት ወደ ይሁዳ መሳፍንት መጥቶ እንዲህ አላቸው፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እናንተ ተዋችሁኝ፤ ስለዚህ እኔ ደግሞ በግብፅ ንጉሥ በሱስቀም እጅ ተውኋችሁ።” 6የእስራኤልም መሳፍንትና ንጉሡ አፈሩ፥ “እግዚአብሔር ጻድቅ ነው” አሉ። 7እግዚአብሔርም እንደ ተመለሱና እንደ ተፀፀቱ ባየ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል፥ “ከተመለሱ አላጠፋቸውም፤ ከጥቂት ቀንም በኋላ አድናቸዋለሁ፤ ቍጣዬም#ዕብ. “በሱሳቂም እጅ” የሚል ይጨምራል። በኢየሩሳሌም ላይ አይፈስስም” ሲል ወደ ሰማያ መጣ። 8ለእኔ መገዛትንና ለምድር ነገሥታት መገዛትን ያውቃሉና አገልጋዮች ይሆናሉ።
9የግብፅ ንጉሥ ሱስቀምም ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፤ የእግዚአብሔርንም ቤተ መዛግብትና የንጉሡን ቤተ መዛግብት ወሰደ፤ ሁሉንም ወሰደ፤ ደግሞም ሰሎሞን የሠራቸውን የወርቁን አላባሽ አግሬ ጋሻዎችን ወሰደ። 10ንጉሡም ሮብዓም በእነርሱ ፋንታ የናስ አላባሽ አግሬ ጋሻዎችን ሠራ፤ ሮብዓምም የንጉሡን ቤት ደጅ በሚጠብቁ በዘበኞች አለቃ እጅ አኖራቸው። 11ንጉሡም ወደ እግዚአብሔር ቤት በገባ ቍጥር ዘበኞች መጥተው ይሸከሙአቸው ነበር፤ መልሰውም በዘበኞች ቤት ውስጥ ያኖሩአቸው ነበር። 12በተፀፀተም ጊዜ የእግዚአብሔር ቍጣ ከእርሱ ዘንድ ራቀ፤ ፈጽሞም አላጠፋውም፤ በይሁዳ መልካም ነገር ተገኝቶአልና።
13ንጉሡም ሮብዓም በኢየሩሳሌም ጸና፤ ንጉሥም ሆነ፤ ሮብዓምም በነገሠ ጊዜ የአርባ አንድ ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ እግዚአብሔርም ስሙን ያኖርባት ዘንድ ከእስራኤል ሀገር ሁሉ በመረጣት ከተማ በኢየሩሳሌም ዐሥራ ሰባት ዓመት ነገሠ፤ እናቱም የአሞን ሴት ንዑማ ነበረች። 14እግዚአብሔርንም ይሻ ዘንድ ልቡን አላቀናም ነበርና ክፉ ነገርን አደረገ።
15የሮብዓምም የፊተኛውና የኋለኛው ነገር እነሆ፥ በነቢዩ ሰማያና በባለ ራእዩ በአዶ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? ሮብዓምም ከኢዮርብዓም ጋር በዘመኑ ሁሉ ይዋጋ ነበር። 16ሮብዓምም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ተቀበረ፤ ልጁም አብያ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልእ 12: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ