1
አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 16:11
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
በእግዚአብሔርና በኀያል ሥልጣኑ ተማመኑ፤ ዘወትርም እርሱን ፈልጉ፤
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 16:34
ቸር ስለ ሆነ፥ ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ስለ ሆነ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ!
3
አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 16:8
እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤ ያደረገውንም ሁሉ ለሕዝቦች ንገሩ፤
4
አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 16:10
በቅዱስ ስሙ ደስ ይበላችሁ! እግዚአብሔርን የሚፈልግ ሰው ሁሉ ሐሴት ያድርግ!
5
አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 16:12-13
አገልጋዮቹ የሆናችሁ የእስራኤል ልጆች ሆይ! የእግዚአብሔር ምርጥ የሆናችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ! እግዚአብሔር ያደረጋቸውን ድንቅ ነገሮች፥ የሰጠውን ፍርድና ያደረጋቸውን ተአምራት አስታውሱ።
6
አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 16:9
ለእግዚአብሔር የምስጋና መዝሙር ዘምሩ፤ ያደረገውን አስደናቂ ነገር ሁሉ ተናገሩ፤
7
አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 16:25
እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ ከፍ ያለ ምስጋናም ይገባዋል፤ ከአማልክት ሁሉ ይበልጥ ሊፈራ ይገባዋል፤
8
አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 16:29
ለስሙ ተገቢ የሆነውን ክብር ለእግዚአብሔር ስጡ፤ ወደ መቅደሱም መባ ይዛችሁ ቅረቡ፤ ግርማ በተመላ ቅድስናው ለእግዚአብሔር ስገዱ።
9
አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 16:27
በዙሪያው ያለው ክብርና ግርማ ነው፤ መቅደሱንም ኀይልና ደስታ እንዲሞላበት አድርጎአል።
10
አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 16:23
በምድር የምትኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ለእግዚአብሔር ዘምሩ! የአዳኝነቱን መልካም ዜና በየቀኑ አብሥሩ፤
11
አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 16:24
በሕዝቦች መካከል ክብሩን አስታውቁ፤ ለሕዝቦችም ሁሉ ታላቅ ሥራውን አውሩ።
12
አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 16:22
“የተመረጡ አገልጋዮቼን አትንኩ። ነቢያቴንም አትጒዱ” በማለት አስጠነቀቃቸው።
13
አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 16:26
ሌሎች ሕዝቦች የሚሰግዱላቸው አማልክት ጣዖቶች ናቸው፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን የፈጠረ አምላክ ነው።
14
አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 16:15
ቃል ኪዳኑን ወይም የሰጠውን ተስፋ እስከ ሺህ ትውልድም ሆነ ለዘለዓለም አይረሳም።
15
አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 16:31
ሰማይና ምድር ደስ ይበላቸው! ሕዝቦች ሁሉ “እግዚአብሔር ንጉሥ ነው” ይበሉ።
16
አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 16:36
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን! ሕዝቡ ሁሉ “አሜን” አሉ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ።
17
አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 16:28
በምድር የምትኖሩ ሕዝቦች ሁሉ! ስለ ክብሩና ስለ ኀይሉ እግዚአብሔርን አመስግኑት።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች