1
ኦሪት ዘፍጥረት 26:3
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
እዚሁ ኑር፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እባርክሃለሁም፤ ይህን ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጣለሁ፤ በዚህ ዐይነት ለአባትህ ለአብርሃም የገባሁትን ቃል ኪዳን እፈጽማለሁ፤
Vergelyk
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 26:3
2
ኦሪት ዘፍጥረት 26:4-5
ዘርህን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛዋለሁ፤ ይህንንም ሁሉ ምድር አወርሳቸዋለሁ፤ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ። አንተን የምባርክበትም ምክንያት አባትህ አብርሃም ለእኔ ታዛዥ በመሆን የሰጠሁትን ትእዛዞች፥ ድንጋጌዎችንና ሕጎችን ሁሉ ስለ ጠበቀ ነው።”
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 26:4-5
3
ኦሪት ዘፍጥረት 26:22
ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ የውሃ ጒድጓድ ቈፈረ፤ በዚህኛው የውሃ ጒድጓድ ምክንያት ምንም ጠብ ስላልተነሣ “እነሆ፥ አሁን እግዚአብሔር ሰፊ ቦታ ሰጠን፤ በምድር ላይም እንበዛለን ሲል፥ ያንን ቦታ ‘ረሖቦት’ ” ብሎ ሰየመው።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 26:22
4
ኦሪት ዘፍጥረት 26:2
በዚያም እግዚአብሔር ለይስሐቅ ተገለጠለትና እንዲህ አለው፤ “ወደ ግብጽ አገር አትሂድ፤ እንድትኖርበት በምነግርህ በዚህ ምድር ተቀመጥ፤
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 26:2
5
ኦሪት ዘፍጥረት 26:25
ይስሐቅ በዚያ መሠዊያ ሠራና ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ መኖሪያውንም እዚያ አደረገ፤ አገልጋዮቹም ሌላ ጒድጓድ ቈፈሩ።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 26:25
Tuisblad
Bybel
Leesplanne
Video's