1
ኦሪት ዘፍጥረት 17:1
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
አብራምም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ ጌታ ለአብራም ተገለጠለትና፦ “እኔ ኤልሻዳይ ነኝ፥ በፊቴ ተመላለስ፥ ፍጹምም ሁን፥
Paghambingin
I-explore ኦሪት ዘፍጥረት 17:1
2
ኦሪት ዘፍጥረት 17:5
ከዛሬም ጀምሮ እንግዲህ ስምህ አብራም ተብሎ አይጠራ፥ ነገር ግን ስምህ አብርሃም ይሆናል፥ ለብዙ አሕዛብ አባት አድርጌሃለሁና።
I-explore ኦሪት ዘፍጥረት 17:5
3
ኦሪት ዘፍጥረት 17:7
ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር በትውልዳቸው ለዘለዓለም ኪዳን አቆማለሁ፥ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ አምላክ እሆን ዘንድ።
I-explore ኦሪት ዘፍጥረት 17:7
4
ኦሪት ዘፍጥረት 17:4
ለብዙ አሕዛብም አባት ትሆናለህ።
I-explore ኦሪት ዘፍጥረት 17:4
5
ኦሪት ዘፍጥረት 17:19
እግዚአብሔርም አለ፦ “በእውነት ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅን ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ይስሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ፥ ከእርሱ በኋላ ለዘሩ የዘለዓለም ቃል ኪዳን እንዲሆን ቃል ኪዳኔን ከእርሱ ጋር አቆማለሁ።
I-explore ኦሪት ዘፍጥረት 17:19
6
ኦሪት ዘፍጥረት 17:8
በእንግድነት የምትኖርባትን ምድር፥ የከነዓን ምድር ሁሉ፥ ለዘለዓለም ግዛት ይሆንህ ዘንድ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ እሰጣለሁ፥ አምላክም እሆናቸዋለሁ።”
I-explore ኦሪት ዘፍጥረት 17:8
7
ኦሪት ዘፍጥረት 17:17
አብርሃምም በግምባሩ ወደቀ፥ ሳቀም፥ በልቡም አለ፦ “የመቶ ዓመት ሰው በውኑ ልጅ ይወልዳልን? ዘጠና ዓመት የሆናትም ሣራ ትወልዳለችን?”
I-explore ኦሪት ዘፍጥረት 17:17
8
ኦሪት ዘፍጥረት 17:15
እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፦ “የሚስትህን የሦራን ስም ‘ሦራ’ ብለህ አትጥራ፥ ስምዋ ሣራ ይሆናል እንጂ።
I-explore ኦሪት ዘፍጥረት 17:15
9
ኦሪት ዘፍጥረት 17:11
የቍልፈታችሁንም ሥጋ ትገረዛላችሁ፥ በእኔና በእናንተ መካከል ላለውም ቃል ኪዳን ምልክት ይሆናል።
I-explore ኦሪት ዘፍጥረት 17:11
10
ኦሪት ዘፍጥረት 17:21
ቃል ኪዳኔን ግን በሚመጣው ዓመት በዚሁ ጊዜ ሣራ ከምትወልድልህ ከይስሐቅ ጋር አቆማለሁ።”
I-explore ኦሪት ዘፍጥረት 17:21
11
ኦሪት ዘፍጥረት 17:12-13
የስምንት ቀን ልጅ ይገረዝ፥ በቤት የተወለደ ወይም ከዘራችሁ ያልሆነ በብርም ከእንግዳ ሰው የተገዛ፥ ወንድ ሁሉ በትውልዳችሁ ይገረዝ። በቤትህ የተወለደ በብርህም የተገዛ ፈጽሞ ይገረዝ። ቃል ኪዳኔም በሥጋችሁ የዘለዓለም ቃል ኪዳን ይሆናል።
I-explore ኦሪት ዘፍጥረት 17:12-13
Home
Biblia
Mga Gabay
Mga Palabas