1
ኦሪት ዘፀአት 2:24-25
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
እግዚአብሔርም የለቅሶአቸውን ድምፅ ሰማ፥ እግዚአብሔርም ከአብርሃምና ከይስሐቅ ከያዕቆብም ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን አስታወሰ። እግዚአብሔርም የእስራኤልን ሕዝቦች አየ፥ እግዚአብሔርም የደረሰባቸውን ነገር አወቀ።
Paghambingin
I-explore ኦሪት ዘፀአት 2:24-25
2
ኦሪት ዘፀአት 2:23
ከብዙ ቀኖች በኋላ የግብጽ ንጉሥ ሞተ፤ የእስራኤልም ሕዝቦች ከባርነት የተነሣ አለቀሱ፥ ጮኹም፥ ስለባርነታቸውም የልመና ጩኸታቸው ወደ እግዚአብሔር ወጣ።
I-explore ኦሪት ዘፀአት 2:23
3
ኦሪት ዘፀአት 2:10
ሕፃኑም አደገ፥ ወደ ፈርዖንም ልጅ አመጣችው፥ ለእርሷም ልጅ ሆነላት። እኔ ከውኃ አውጥቼዋለሁና ስትልም ስሙን ሙሴ ብላ ጠራችው።
I-explore ኦሪት ዘፀአት 2:10
4
ኦሪት ዘፀአት 2:9
የፈርዖንም ልጅ፦ “ይህን ሕፃን ወስደሽ አጥቢልኝ፥ ዋጋሽንም እከፍልሻለሁ” አለቻት። ሴቲቱም ሕፃኑን ወስዳ አጠባችው።
I-explore ኦሪት ዘፀአት 2:9
5
ኦሪት ዘፀአት 2:5
የፈርዖንም ልጅ ልትታጠብ ወደ ወንዝ ወረደች፤ ደንገጥሮችዋም በወንዝ ዳር ይሄዱ ነበር፤ ሣጥኑንም በቄጠማ ውስጥ አየች፥ ደንገጥሩዋንም ልካ አስመጣችው።
I-explore ኦሪት ዘፀአት 2:5
6
ኦሪት ዘፀአት 2:11-12
በነዚያም ቀኖች፥ ሙሴ ባደገ ጊዜ ወደ ወንድሞቹ ወጣ፥ የሥራቸውንም መከራ ተመለከተ፤ የግብጽም ሰው ከወንድሞቹ አንድ የሆነውን ዕብራዊ ሰው ሲመታ አየ። ወዲህና ወዲያም ተመለከተ፥ ማንንም አላየም፥ ግብፃዊውንም ገደለው፥ በአሸዋም ውስጥ ደበቀው።
I-explore ኦሪት ዘፀአት 2:11-12
Home
Biblia
Mga Gabay
Mga Palabas