1
ኦሪት ዘፍጥረት 13:15
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ይህን የምታየውን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ እሰጣችኋለሁ፤ ለዘለዓለምም የእናንተ ይሆናል፤
Paghambingin
I-explore ኦሪት ዘፍጥረት 13:15
2
ኦሪት ዘፍጥረት 13:14
ሎጥ ከሄደ በኋላ እግዚአብሔር አብራምን እንዲህ አለው፤ “ካለህበት ስፍራ ሆነህ ወደ ሰሜን፥ ወደ ደቡብ፥ ወደ ምሥራቅና ምዕራብ ተመልከት፤
I-explore ኦሪት ዘፍጥረት 13:14
3
ኦሪት ዘፍጥረት 13:16
ዘርህን እንደ ምድር አሸዋ አበዛዋለሁ፤ የምድር አሸዋ ሊቈጠር እንደማይቻል ሁሉ የአንተም ዘር እንዲሁ ሊቈጠር የማይቻል ይሆናል።
I-explore ኦሪት ዘፍጥረት 13:16
4
ኦሪት ዘፍጥረት 13:8
ከዚህ በኋላ አብራም ሎጥን እንዲህ አለው፤ “እኛ ወንድማማች ስለ ሆንን በእኔና በአንተ መካከል እንዲሁም በእኔ እረኞችና በአንተ እረኞች መካከል ጠብ ሊነሣ አይገባም፤
I-explore ኦሪት ዘፍጥረት 13:8
5
ኦሪት ዘፍጥረት 13:18
ስለዚህ አብራም ድንኳኑን ነቅሎ በኬብሮን የመምሬ የተቀደሱ የወርካ ዛፎች ወደአሉበት ስፍራ ለመኖር ሄደ፤ እዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ።
I-explore ኦሪት ዘፍጥረት 13:18
6
ኦሪት ዘፍጥረት 13:10
ሎጥ ዙሪያውን በተመለከተ ጊዜ የዮርዳኖስ ሸለቆ እስከ ጾዓር ድረስ እንደ እግዚአብሔር ገነት ወይም እንደ ግብጽ ምድር ውሃ የሞላበት መሆኑን አየ፤ ይህን የተመለከተው እግዚአብሔር የሰዶምንና የገሞራን ከተሞች ከማጥፋቱ በፊት ነበር።
I-explore ኦሪት ዘፍጥረት 13:10
Home
Biblia
Mga Gabay
Mga Palabas