1
የማርቆስ ወንጌል 13:13
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
በእኔ ምክንያት በሰው ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻው የሚጸና ግን ይድናል።
ஒப்பீடு
የማርቆስ ወንጌል 13:13 ஆராயுங்கள்
2
የማርቆስ ወንጌል 13:33
ስለዚህ ጊዜው መቼ እንደሚሆን አታውቁምና ተጠንቀቁ፤ ትጉ፥ ጸልዩም።
የማርቆስ ወንጌል 13:33 ஆராயுங்கள்
3
የማርቆስ ወንጌል 13:11
ተይዛችሁ ለፍርድ በምትቀርቡበት ጊዜ፥ በዚያች ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩ እንጂ ምን እንናገራለን በማለት አስቀድማችሁ አትጨነቁ፤ የሚናገረው መንፈስ ቅዱስ እንጂ እናንተ አይደላችሁምና።
የማርቆስ ወንጌል 13:11 ஆராயுங்கள்
4
የማርቆስ ወንጌል 13:31
ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም።
የማርቆስ ወንጌል 13:31 ஆராயுங்கள்
5
የማርቆስ ወንጌል 13:32
ነገር ግን ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያችም ሰዓት ከአብ በቀር፥ የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ፥ ወልድም ቢሆን፥ ማንም አያውቅም።
የማርቆስ ወንጌል 13:32 ஆராயுங்கள்
6
የማርቆስ ወንጌል 13:7
ስለ ጦርነትና ስለ ጦርነት ወሬ በምትሰሙበት ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህማ መሆን አለበት፤ ፍጻሜው ግን ገና ነው።
የማርቆስ ወንጌል 13:7 ஆராயுங்கள்
7
የማርቆስ ወንጌል 13:35-37
እንግዲህ የቤቱ ባለቤት በምሽት ወይም በውድቅት፥ በዶሮ ጩኸት ወይም ጎሕ ሲቀድ እንደሚመጣ አታውቁምና ተግታችሁ ጠብቁ፤ ድንገት ሲመጣ ተኝታችሁ እንዳያገኛችሁ ለእናንተ የምነግራችሁን ለሰው ሁሉ እናገራለሁ፤ ተግታችሁ ጠብቁ።
የማርቆስ ወንጌል 13:35-37 ஆராயுங்கள்
8
የማርቆስ ወንጌል 13:8
ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ መንግሥት በመንግሥት ላይ ይነሣል፤ በብዙ ቦታም የመሬት መንቀጥቀጥና ራብ ይሆናል፤ እነዚህ ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።
የማርቆስ ወንጌል 13:8 ஆராயுங்கள்
9
የማርቆስ ወንጌል 13:10
አስቀድሞ ግን ወንጌል ለሕዝብ ሁሉ መሰበክ አለበት።
የማርቆስ ወንጌል 13:10 ஆராயுங்கள்
10
የማርቆስ ወንጌል 13:6
ብዙዎች፥ “እኔ እርሱ ነኝ” እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።
የማርቆስ ወንጌል 13:6 ஆராயுங்கள்
11
የማርቆስ ወንጌል 13:9
ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ለሸንጎ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ በምኵራብ ይገርፏችኋል፤ ምስክር ትሆኑም ዘንድ በእኔ ምክንያት በገዢዎችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ።
የማርቆስ ወንጌል 13:9 ஆராயுங்கள்
12
የማርቆስ ወንጌል 13:22
ሐሰተኛ ክርስቶሶችና ሐሰተኛ ነቢያት ተነሥተው፥ ምልክቶችንና ድንቆችን በማድረግ፥ ቢቻላቸው የተመረጡትን እንኳ ያስታሉ።
የማርቆስ ወንጌል 13:22 ஆராயுங்கள்
13
የማርቆስ ወንጌል 13:24-25
በዚያን ጊዜ፥ ከመከራው በኋላ ፀሓይ ትጨልማለች፥ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም፤ ከዋክብት ከሰማይ ይረግፋሉ፤ የሰማይ ኀይላትም ይናወጣሉ።
የማርቆስ ወንጌል 13:24-25 ஆராயுங்கள்
முகப்பு
வேதாகமம்
வாசிப்புத் திட்டங்கள்
காணொளிகள்