ኦሪት ዘሌዋውያን 12
12
ሴት ከወለደች በኋላ ከሕርስ ስለምትነጻበት ጊዜ
1እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 2“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፦ ሴት ብታረግዝ ወንድ ልጅም ብትወልድ፥ ሰባት ቀን ያህል የረከሰች ናት፤ 3እንደ ግዳጅዋ ወራት ትረክሳለች። በስምንተኛውም ቀን ልጁ ከሥጋው ሸለፈት ይገረዝ። 4ከደምዋም እስክትነጻ ሠላሳ ሦስት ቀን ትቈይ፤ የመንጻቷ ቀንም እስኪፈጸም ድረስ የተቀደሰን ነገር አትንካ፤ ወደ መቅደስም አትግባ። 5ሴት ልጅም ብትወልድ እንደ ግዳጅዋ ወራት ሁለት ሳምንት ያህል የረከሰች ናት፤ ከደምዋም እስክትነጻ ድረስ ስድሳ ስድስት ቀን ትቈይ።
6“የመንጻቷ ወራትም በተፈጸመ ጊዜ፥ ለወንድ ልጅ ወይም ለሴት ልጅ፥ የአንድ ዓመት ጠቦት ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ የርግብም ግልገል ወይም ዋኖስ ለኀጢአት መሥዋዕት ወደ ምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ታመጣለች። 7ካህኑም በእግዚአብሔር ፊት ያቀርበዋል፤ ያስተሰርይላትማል፤ ከደምዋም ፈሳሽ ትነጻለች። ወንድ ወይም ሴት ለምትወልድ ሴት ሕጉ ይህ ነው። 8ጠቦት ለማምጣት የሚበቃ ገንዘብ በእጅዋ ባይኖራት ሁለት ዋኖሶች፥ ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች፥ አንዱን ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ሌላውንም ለኀጢአት መሥዋዕት ታቀርባለች፤ ካህኑም ያስተሰርይላታል፤ እርስዋም ትነጻለች።”
Aktualisht i përzgjedhur:
ኦሪት ዘሌዋውያን 12: አማ2000
Thekso
Ndaje
Kopjo
A doni që theksimet tuaja të jenë të ruajtura në të gjitha pajisjet që keni? Regjistrohu ose hyr

: