Logoja YouVersion
Ikona e kërkimit

ትንቢተ ሚልክያስ መግቢያ

መግቢያ
ትንቢተ ሚልክያስ የተገኘው ከክርስቶስ ልደት በፊት በአምስተኛው ምእት ዓመት የኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ዳግመኛ ከተሠራ በኋላ ነበር። ነቢዩ አጥብቆ የሚያሳስበው ካህናቱም ሆኑ ሕዝቡ ከእግዚአብሔር ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን ማደስ እንዳለባቸው ነበር፤ የእግዚአብሔር ሕዝብ በአኗኗሩም ሆነ በአምልኮቱ መረን የተለቀቀና የተበላሸ እንደ ነበር ግልጥ ነው፤ ካህናቱና ሕዝቡ ተገቢውን መሥዋዕት ባለማቅረብና በሰጣቸውም መመሪያ ባለመኖር እግዚአብሔርን ለማታለል ይሞክሩ ነበር። ስለ ሆነም እግዚአብሔር መንገዱን ለማዘጋጀትና ቃል ኪዳኑን ለማወጅ መልእክተኛውን አስቀድሞ በመላክ በሕዝቡ ላይ ለመፍረድና ሕዝቡን ለማጥራት ይመጣል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
1. ጌታ ለእስራኤል ሕዝብ ያለው ፍቅር (1፥1-5)
2. የእግዚአብሔር ፍርድ በካህናት ላይ (1፥6—2፥9)
2. የቃል ኪዳን መፍረስ (2፥10-17)
4. የጌታ መምጣት (3፥1-4)
5. እግዚአብሔርን ማታለል የማይገባ መሆኑ (3፥5-15)
6. የታማኞች መሸለምና የክፉዎች መቀጣት (3፥16—4፥6)

Thekso

Ndaje

Kopjo

None

A doni që theksimet tuaja të jenë të ruajtura në të gjitha pajisjet që keni? Regjistrohu ose hyr