1
ኦሪት ዘፍጥረት 27:28-29
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
እግዚአብሔርም ከሰማይ ጠል፥ ከምድርም ስብ፥ የእህልንም፥ የወይንንም፥ የዘይትንም ብዛት ይስጥህ፤ አሕዛብ ይገዙልህ፤ አለቆችም ይስገዱልህ፤ ለወንድምህ ጌታ ሁን፤ የአባትህም ልጆች ይስገዱልህ፤ የሚረግምህ እርሱ ርጉም ይሁን፤ የሚባርክህም ቡሩክ ይሁን።”
Krahaso
Eksploroni ኦሪት ዘፍጥረት 27:28-29
2
ኦሪት ዘፍጥረት 27:36
ዔሳውም አለ፥ “በእውነት ስሙ ያዕቆብ ተባለ፤ ሁለት ጊዜ አሰናክሎኛልና፤ መጀመሪያ ብኵርናዬን ወሰደ፤ አሁንም እነሆ በረከቴን ወሰደ።” ዔሳውም አባቱን አለው፥ “ደግሞም አባቴ ሆይ፥ ለእኔ በረከትን አላስቀረህልኝምን?”
Eksploroni ኦሪት ዘፍጥረት 27:36
3
ኦሪት ዘፍጥረት 27:39-40
አባቱ ይስሐቅም መለሰ፤ አለውም፥ “እነሆ መኖሪያህ ከላይ ከሰማይ ጠል፥ ከምድርም ስብ ይሁን፤ በሰይፍህም ትኖራለህ፤ ለወንድምህም ትገዛለህ፤ ነገር ግን ቀንበሩን ከአንገትህ ልትጥል ብትወድድ ከእርሱ ጋር ተስማማ።”
Eksploroni ኦሪት ዘፍጥረት 27:39-40
4
ኦሪት ዘፍጥረት 27:38
ዔሳውም አባቱን ይስሐቅን አለው፥ “አባቴ ሆይ፥ በረከትህ አንዲት ብቻ ናትን? አባቴ ሆይ፥ እኔንም ደግሞ ባርከኝ።” ዔሳውም ጮሆ አለቀሰ።
Eksploroni ኦሪት ዘፍጥረት 27:38
Kreu
Bibla
Plane
Video