1
ኦሪት ዘፍጥረት 37:5
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ዮሴፍም ሕልምን አለመ፥ ለወንድሞቹም ነገራቸው፥ እነርሱም እንደገና አብዝተው ጠሉት።
Krahaso
Eksploroni ኦሪት ዘፍጥረት 37:5
2
ኦሪት ዘፍጥረት 37:3
እስራኤልም ዮሴፍን ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ ይወደው ነበር፥ እርሱ በሽምግልናው የወለደው ነበርና፥ በብዙ ኅብር ያጌጠችም ቀሚስ አደረገለት።
Eksploroni ኦሪት ዘፍጥረት 37:3
3
ኦሪት ዘፍጥረት 37:4
ወንድሞቹም አባታቸው ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ እንደሚወደው ባዩ ጊዜ ጠሉት፥ በሰላም ሊያናግሩትም አልቻሉም።
Eksploroni ኦሪት ዘፍጥረት 37:4
4
ኦሪት ዘፍጥረት 37:9
ደግሞም ሌላ ሕልምን አለመ፥ ለወንድሞቹም፦ “እነሆ ደግሞ ሌላ ሕልምን አለምሁ፥ እነሆ ፀሐይና ጨረቃ ዐሥራ አንድ ከዋክብትም ሲሰግዱልኝ አየሁ።” ሲል ነገራቸው።
Eksploroni ኦሪት ዘፍጥረት 37:9
5
ኦሪት ዘፍጥረት 37:11
ወንድሞቹም ቀኑበት፥ አባቱ ግን ነገሩን ጠብቆ አኖረው።
Eksploroni ኦሪት ዘፍጥረት 37:11
6
ኦሪት ዘፍጥረት 37:6-7
እርሱም አላቸው፦ “እኔ ያለምሁትን ሕልም ስሙ፥ እነሆ እኛ በእርሻ መካከል ነዶ ስናስር ነበር፥ እነሆም፥ የእኔ ነዶ ቀጥ ብላ ቆመች፥ የእናንተም ነዶች በዙሪያ ከብበው እነሆ ለእኔ ነዶ ሰገዱ።”
Eksploroni ኦሪት ዘፍጥረት 37:6-7
7
ኦሪት ዘፍጥረት 37:20
ኑ፥ እንግደለውና በአንዱ ጉድጓድ ውስጥ እንጣለው፦ ክፉ አውሬም በላው እንላለን፥ የሕልሞቹን መጨረሻ እናያለን።”
Eksploroni ኦሪት ዘፍጥረት 37:20
8
ኦሪት ዘፍጥረት 37:28
የምድያም ነጋዶችም አለፉ፥ እነርሱም ዮሴፍን አንሥተው ከጉድጓድ አወጡት፥ ለእስማኤላውያንም ዮሴፍን በሃያ ብር ሸጡት፥ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወሰዱት።
Eksploroni ኦሪት ዘፍጥረት 37:28
9
ኦሪት ዘፍጥረት 37:19
እርስ በርሳቸውም እንዲህ ተባባሉ፦ “ያ ሕልም አላሚ ይኸው መጣ።
Eksploroni ኦሪት ዘፍጥረት 37:19
10
ኦሪት ዘፍጥረት 37:18
እነርሱም በሩቅ ሳለ አዩት፥ ወደ እነርሱም ገና ሳይቀርብ ይገድሉት ዘንድ በእርሱ ላይ ተማከሩ።
Eksploroni ኦሪት ዘፍጥረት 37:18
11
ኦሪት ዘፍጥረት 37:22
“ደም አታፍስሱ፥ በዚህች ምድረ በዳ ባለችው ጉድጓድ ጣሉት፥ ነገር ግን እጃችሁን አትጣሉበት” አላቸው። እንዲህም ማለቱ ከእጃቸው ሊያድነውና ወደ አባቱ ሊመልሰው ነው።
Eksploroni ኦሪት ዘፍጥረት 37:22
Kreu
Bibla
Plane
Video