1
የማቴዎስ ወንጌል 6:33
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
እናንተ ግን፥ አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ፤ የቀረው ነገር ሁሉ ይጨመርላችኋል፤
Krahaso
Eksploroni የማቴዎስ ወንጌል 6:33
2
የማቴዎስ ወንጌል 6:34
ነገ ለራሱ ይጨነቃል፤ ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።”
Eksploroni የማቴዎስ ወንጌል 6:34
3
የማቴዎስ ወንጌል 6:25
ስለዚህ እንዲህ እላችኋለሁ፤ ‘ምን እንበላለን? ምን እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን?’ በማለት ስለ ኑሮአችሁ አትጨነቁ፤ ከምግብ ሕይወት፥ ከልብስም ሰውነት አይበልጥምን?
Eksploroni የማቴዎስ ወንጌል 6:25
4
የማቴዎስ ወንጌል 6:6
አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ ክፍልህ ገብተህ፥ በርህን ዝጋና በስውር ወዳለው ወደማይታይ አባትህ ጸልይ፤ በስውር የተሠራውን የሚያይ አባትህም የመልካም ሥራህን ዋጋ ይከፍልሃል።
Eksploroni የማቴዎስ ወንጌል 6:6
5
የማቴዎስ ወንጌል 6:9-10
ስለዚህ እናንተ እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ፦ ‘በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ! ስምህ ይመስገን፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነ፥ እንዲሁም በምድር ይሁን።
Eksploroni የማቴዎስ ወንጌል 6:9-10
6
የማቴዎስ ወንጌል 6:11
የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን።
Eksploroni የማቴዎስ ወንጌል 6:11
7
የማቴዎስ ወንጌል 6:12
እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል፥ በደላችንን ይቅር በለን፤
Eksploroni የማቴዎስ ወንጌል 6:12
8
የማቴዎስ ወንጌል 6:13
ከክፉ አድነን እንጂ፥ ወደ ፈተና አታግባን፤ [መንግሥት፥ ኀይልና ክብር ለዘለዓለም ያንተ ነው፤ አሜን።’]
Eksploroni የማቴዎስ ወንጌል 6:13
9
የማቴዎስ ወንጌል 6:14
“የሰዎችን በደል ይቅር ብትሉላቸው፥ እናንተንም የሰማዩ አባታችሁ ይቅር ይልላችኋል።
Eksploroni የማቴዎስ ወንጌል 6:14
10
የማቴዎስ ወንጌል 6:26
እስቲ በሰማይ ላይ ወደሚበሩት ወፎች ተመልከቱ፤ እነርሱ አይዘሩም፤ አያጭዱም፤ በጐተራ አይከቱም፤ ነገር ግን የሰማዩ አባታችሁ ይመግባቸዋል። ታዲያ እናንተ ከወፎች እጅግ ትበልጡ የለምን?
Eksploroni የማቴዎስ ወንጌል 6:26
11
የማቴዎስ ወንጌል 6:19-21
ደግሞም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ብልና ዝገት በሚያጠፉበት፥ ሌቦችም ሰብረው በሚሰርቁበት፥ በዚህ ምድር ላይ ለራሳችሁ ሀብት አታከማቹ። ይልቅስ ብልና ዝገት ሊያጠፉት በማይችሉበት፥ ሌቦችም ሰብረው በማይሰርቁበት በሰማይ ሀብታችሁን አከማቹ። ሀብትህ ባለበት ልብህም በዚያ ይገኛል።
Eksploroni የማቴዎስ ወንጌል 6:19-21
12
የማቴዎስ ወንጌል 6:24
“አንድ ሰው ለሁለት ጌቶች አገልጋይ ሊሆን አይችልም፤ ወይም አንዱን ይጠላል፥ ሌላውንም ይወዳል፤ ወይም አንዱን ያከብራል፥ ሌላውን ይንቃል፤ እንዲሁም አንድ ሰው በአንድ ጊዜ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ አገልጋይ መሆን አይችልም።
Eksploroni የማቴዎስ ወንጌል 6:24
13
የማቴዎስ ወንጌል 6:30
ታዲያ ዛሬ ታይቶ ነገ በእሳት ውስጥ የሚጣለውን የሜዳ ሣር፥ እግዚአብሔር እንዲህ የሚያለብስ ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጐደላችሁ! እናንተንማ እንዴት አብልጦ አያለብሳችሁም!
Eksploroni የማቴዎስ ወንጌል 6:30
14
የማቴዎስ ወንጌል 6:3-4
አንተ ግን ምጽዋት ስትመጸውት ቀኝ እጅህ የሚያደርገውን ግራ እጅህ አይወቅ። እንግዲህ ምጽዋትህ በስውር ይሁን፤ በስውር የተሠራውን የሚያየው አባትህ፥ የመልካም ሥራህን ዋጋ ይከፍልሃል።
Eksploroni የማቴዎስ ወንጌል 6:3-4
15
የማቴዎስ ወንጌል 6:1
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ሰዎች ይዩልን ብላችሁ መልካም ሥራችሁን በሰዎች ፊት ከማድረግ ተጠንቀቁ፤ አለበለዚያ ግን፥ በሰማይ አባታችሁ ዘንድ ምንም ዋጋ አታገኙም።
Eksploroni የማቴዎስ ወንጌል 6:1
16
የማቴዎስ ወንጌል 6:16-18
ኢየሱስም ቀጥሎ እንዲህ አለ፦ “በምትጾሙበት ጊዜ፥ መጾማቸውን ሰዎች እንዲያውቁላቸው፥ ፊታቸውን እንደሚለውጡት እንደ ግብዞች፥ ፊታችሁን አታጠውልጉ፤ በእውነት እላችኋለሁ፥ እነርሱ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። አንተ ግን በምትጾምበት ጊዜ ፊትህን ታጠብ፤ ራስህንም ተቀባ፤ በዚህ አኳኋን፥ መጾምህን በስውር ካለው አባትህ በቀር ሌላ ማንም አያውቅም። በስውር የተሠራውን የሚያይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል።”
Eksploroni የማቴዎስ ወንጌል 6:16-18
Kreu
Bibla
Plane
Video