1
የማርቆስ ወንጌል 13:13
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ስለ ስሜ በሰው ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ በትዕግሥት የሚጸና ግን ይድናል።
Харьцуулах
የማርቆስ ወንጌል 13:13 г судлах
2
የማርቆስ ወንጌል 13:33
ጊዜው መቼ እንደሚሆን አታውቁምና ተጠንቀቁ፤ ትጉ።
የማርቆስ ወንጌል 13:33 г судлах
3
የማርቆስ ወንጌል 13:11
ሰዎች ይዘው ወደ ፍርድ ሲያቀርቡአችሁ፥ ‘ምን እንናገር ይሆን?’ በማለት አስቀድማችሁ አትጨነቁ፤ የሚናገረው መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁም። ስለዚህ በዚያን ሰዓት የሚሰጣችሁን ብቻ ተናገሩ።
የማርቆስ ወንጌል 13:11 г судлах
4
የማርቆስ ወንጌል 13:31
ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን ጸንቶ ይኖራል።
የማርቆስ ወንጌል 13:31 г судлах
5
የማርቆስ ወንጌል 13:32
“ነገር ግን ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ከአብ በቀር ማንም የሚያውቅ የለም፤ የሰማይ መላእክትም አያውቁም፤ ወልድም አያውቅም።
የማርቆስ ወንጌል 13:32 г судлах
6
የማርቆስ ወንጌል 13:7
በአቅራቢያችሁ ጦርነት ሲደረግና በሩቅም የጦርነትን ወሬ ስትሰሙ አትደንግጡ፤ ይህ ሁሉ ሊሆን ግድ ነው፤ ይሁን እንጂ መጨረሻው ገና ነው።
የማርቆስ ወንጌል 13:7 г судлах
7
የማርቆስ ወንጌል 13:35-37
ስለዚህ የቤቱ ጌታ የሚመጣበትን ጊዜ አታውቁምና ተጠንቀቁ፤ ምናልባትም ወደ ማታ፥ ወይም በእኩለ ሌሊት፥ ወይም ዶሮ ሲጮኽ፥ ወይም ጠዋት በማለዳ ይመጣ ይሆናል፤ በድንገት መጥቶ ተኝታችሁ እንዳያገኛችሁ ትጉ። “ለእናንተ እንደ ነገርኳችሁ ለሌሎችም ሁሉ ትጉ! እላለሁ።”
የማርቆስ ወንጌል 13:35-37 г судлах
8
የማርቆስ ወንጌል 13:8
ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ጦርነት ያነሣል፤ በየስፍራው የምድር መናወጥና ራብ ይሆናል፤ ይህ ሁሉ እንደ ምጥ ጣር ያለ የጭንቅ መጀመሪያ ነው።
የማርቆስ ወንጌል 13:8 г судлах
9
የማርቆስ ወንጌል 13:10
ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ግን ወንጌል ለዓለም ሕዝብ ሁሉ መዳረስ ይገባዋል።
የማርቆስ ወንጌል 13:10 г судлах
10
የማርቆስ ወንጌል 13:6
ብዙዎች ‘እኔ መሲሕ ነኝ!’ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ ብዙ ሰዎችንም ያሳስታሉ፤
የማርቆስ ወንጌል 13:6 г судлах
11
የማርቆስ ወንጌል 13:9
“እናንተም ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ሰዎች ለፍርድ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ በየምኲራቡም ይገርፉአችኋል፤ ምስክር እንድትሆኑኝ በእኔ ምክንያት በገዢዎችና በነገሥታት ፊት ለፍርድ ትቆማላችሁ።
የማርቆስ ወንጌል 13:9 г судлах
12
የማርቆስ ወንጌል 13:22
ሐሰተኞች መሲሖችና ሐሰተኞች ነቢያት ይመጣሉ፤ እነርሱ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ ለማሳሳት ተአምራትና ድንቅ ነገሮችን ያደርጋሉ።
የማርቆስ ወንጌል 13:22 г судлах
13
የማርቆስ ወንጌል 13:24-25
“በዚያን ጊዜ፥ ከዚያ ሁሉ መከራ በኋላ፥ ፀሐይ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ በሰማይ ያሉ ኀይሎችም ይናወጣሉ።
የማርቆስ ወንጌል 13:24-25 г судлах
Нүүр хуудас
Библи
Тѳлѳвлѳгѳѳнүүд
Бичлэгүүд