1
ወደ ሮም ሰዎች 3:23-24
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ሰዎች ሁሉ ኃጢአት ሠርተዋል፤ እግዚአብሔር የሰጣቸውንም ክብር አጥተዋል። ስለዚህ ሰዎች ኢየሱስ ክርስቶስ በፈጸመው በአዳኝነት ሥራ በእግዚአብሔር ጸጋ ብቻ ይጸድቃሉ።
Összehasonlít
Fedezd fel: ወደ ሮም ሰዎች 3:23-24
2
ወደ ሮም ሰዎች 3:22
ስለዚህ እግዚአብሔር ምንም ልዩነት ሳያደርግ በኢየሱስ ክርስቶስ ለሚያምኑ ሁሉ ጽድቅን ይሰጣል።
Fedezd fel: ወደ ሮም ሰዎች 3:22
3
ወደ ሮም ሰዎች 3:25-26
እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበው በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ በደሙ የኃጢአታቸውን ስርየት እንዲያገኙ ነው፤ እግዚአብሔር ይህን ማድረጉ በትዕግሥቱ የቀድሞውን ኃጢአት እንዳልነበረ በማድረግ የራሱን ትክክለኛ ፍርድ ለመግለጥ ነው። በአሁኑም ዘመን እግዚአብሔር ራሱ ጻድቅ መሆኑን የሚያሳየው በኢየሱስ የሚያምኑትን ሁሉ በማጽደቅ ነው።
Fedezd fel: ወደ ሮም ሰዎች 3:25-26
4
ወደ ሮም ሰዎች 3:20
ስለዚህ ማንም ሰው በእግዚአብሔር ፊት፥ ሕግን በመፈጸም አይጸድቅም፤ ሕግ የሚያሳየው ሰው ሁሉ ኃጢአተኛ መሆኑን ነው።
Fedezd fel: ወደ ሮም ሰዎች 3:20
5
ወደ ሮም ሰዎች 3:10-12
እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፦ “አንድ እንኳ ጻድቅ ሰው የለም፤ አንድ እንኳን የለም፤ አስተዋይም የለም፤ እግዚአብሔርንም የሚፈልግ አንድም የለም። ሁሉም ከመንገድ ወጥተዋል፤ በአንድነት ሆነው ተሳስተዋል። ደግ ሥራ የሚሠራ አንድ ሰው እንኳ የለም።
Fedezd fel: ወደ ሮም ሰዎች 3:10-12
6
ወደ ሮም ሰዎች 3:28
ስለዚህ እግዚአብሔር ሰውን የሚያጸድቀው፥ ሰው የሕግን ሥራ በመፈጸሙ ሳይሆን በእምነት መሆኑን እንገነዘባለን።
Fedezd fel: ወደ ሮም ሰዎች 3:28
7
ወደ ሮም ሰዎች 3:4
ከቶ አያስቀርም! “ከቃልህ የተነሣ እውነተኛ ትሆናለህ፤ ባላጋራህንም በፍርድ ትረታለህ” ተብሎ እንደ ተጻፈው ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ቢሆንም እግዚአብሔር እውነተኛ ነው።
Fedezd fel: ወደ ሮም ሰዎች 3:4
Kezdőoldal
Biblia
Olvasótervek
Videók