1
የዮሐንስ ወንጌል 16:33
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ይህን ለእናንተ መናገሬ በእኔ ሆናችሁ ሰላም እንዲኖራችሁ ብዬ ነው፤ በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፥ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።”
Vertaa
Tutki የዮሐንስ ወንጌል 16:33
2
የዮሐንስ ወንጌል 16:13
የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል። እርሱ የሚናገረው የሰማውን እንጂ የራሱን ስላልሆነ እርሱ ወደፊት የሚሆኑትን ነገሮች ይነግራችኋል።
Tutki የዮሐንስ ወንጌል 16:13
3
የዮሐንስ ወንጌል 16:24
እስከ አሁን በስሜ ምንም ነገር አለመናችሁም፤ ለምኑ ይሰጣችኋል፤ ደስታችሁም ፍጹም ይሆናል።
Tutki የዮሐንስ ወንጌል 16:24
4
የዮሐንስ ወንጌል 16:7-8
እኔ ግን እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ የእኔ መሄድ ለእናንተ ይጠቅማችኋል፤ እኔ ካልሄድኩ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣም፤ እኔ ከሄድኩ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ። እርሱ በመጣ ጊዜ ስለ ኃጢአት፥ ስለ ጽድቅና ስለ ፍርድም ምክንያት የዓለምን ሰዎች ያጋልጣል።
Tutki የዮሐንስ ወንጌል 16:7-8
5
የዮሐንስ ወንጌል 16:22-23
እንዲሁም እናንተ አሁን ታዝናላችሁ፤ ነገር ግን እኔ እንደገና አያችኋለሁ፤ ልባችሁም ደስ ይለዋል፤ ደስታችሁንም የሚወስድባችሁ የለም። “በዚያን ቀን ከእኔ ምንም አትለምኑም፤ እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ አብን በስሜ ብትለምኑት ሁሉን ነገር ይሰጣችኋል።
Tutki የዮሐንስ ወንጌል 16:22-23
6
የዮሐንስ ወንጌል 16:20
እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ እናንተ ታለቅሳላችሁ፤ ትጮኻላችሁም፤ ዓለም ግን ደስ ይለዋል፤ እናንተ ታዝናላችሁ፤ ነገር ግን ሐዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል።
Tutki የዮሐንስ ወንጌል 16:20
Koti
Raamattu
Suunnitelmat
Videot