1
የዮሐንስ ወንጌል 15:5
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
“እኔ የወይን ግንድ ነኝ፤ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ፤ ብዙ ፍሬ የሚያፈራው በእኔ የሚኖርና እኔም በእርሱ የምኖርበት ነው፤ ነገር ግን ያለ እኔ ምንም ማድረግ አትችሉም።
Vertaa
Tutki የዮሐንስ ወንጌል 15:5
2
የዮሐንስ ወንጌል 15:4
በእኔ ኑሩ፤ እኔም በእናንተ እኖራለሁ፤ ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ላይ ጸንቶ ካልኖረ በቀር በራሱ ብቻ ፍሬ ማፍራት እንደማይቻለው እናንተም በእኔ ካልኖራችሁ ፍሬ ማፍራት አትችሉም።
Tutki የዮሐንስ ወንጌል 15:4
3
የዮሐንስ ወንጌል 15:7
በእኔ ብትኖሩ ቃሌም በእናንተ ቢኖር የፈለጋችሁትን ብትለምኑ ታገኛላችሁ።
Tutki የዮሐንስ ወንጌል 15:7
4
የዮሐንስ ወንጌል 15:16
እኔ መረጥኳችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ ሄዳችሁ ብዙ ፍሬ እንድታፈሩ፥ ፍሬአችሁም ነዋሪ እንዲሆን ሾምኳችሁ። ስለዚህ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አብ ይሰጣችኋል።
Tutki የዮሐንስ ወንጌል 15:16
5
የዮሐንስ ወንጌል 15:13
ሰው ሕይወቱን ስለ ወዳጆቹ አሳልፎ ከመስጠት የበለጠ ፍቅር የለውም።
Tutki የዮሐንስ ወንጌል 15:13
6
የዮሐንስ ወንጌል 15:2
በእኔ ላይ ያለውን ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ አባቴ ቈርጦ ይጥለዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውን ቅርንጫፍ ግን አብዝቶ እንዲያፈራ ገርዞ ያጠራዋል።
Tutki የዮሐንስ ወንጌል 15:2
7
የዮሐንስ ወንጌል 15:12
የእኔ ትእዛዝ እኔ እንደ ወደድኳችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው።
Tutki የዮሐንስ ወንጌል 15:12
8
የዮሐንስ ወንጌል 15:8
ብዙ ፍሬ ስታፈሩ በዚህ አባቴ ይከብራል፤ እናንተም የእኔ ደቀ መዛሙርት መሆናችሁን ታሳያላችሁ።
Tutki የዮሐንስ ወንጌል 15:8
9
የዮሐንስ ወንጌል 15:1
“እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ አትክልተኛውም አባቴ ነው፤
Tutki የዮሐንስ ወንጌል 15:1
10
የዮሐንስ ወንጌል 15:6
በእኔ የማይኖር እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጪ ተጥሎ ይደርቃል፤ እንዲህ ያሉት ቅርንጫፎች ተሰብስበው ወደ እሳት ይጣሉና ይቃጠላሉ።
Tutki የዮሐንስ ወንጌል 15:6
11
የዮሐንስ ወንጌል 15:11
ይህን የነገርኳችሁ ደስታዬ በእናንተ እንዲሆንና የእናንተም ደስታ ፍጹም እንዲሆን ነው።
Tutki የዮሐንስ ወንጌል 15:11
12
የዮሐንስ ወንጌል 15:10
እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ፈጸምኩና በፍቅሩ እንደምኖር እናንተም የእኔን ትእዛዝ ብትፈጽሙ በፍቅሬ ትኖራላችሁ።
Tutki የዮሐንስ ወንጌል 15:10
13
የዮሐንስ ወንጌል 15:17
እንግዲህ እኔ የማዛችሁ እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው።
Tutki የዮሐንስ ወንጌል 15:17
14
የዮሐንስ ወንጌል 15:19
የዓለም ብትሆኑ ዓለም የራሱ የሆነውን በወደደ ነበር፤ ነገር ግን የዓለም ስላልሆናችሁና እኔ ከዓለም ለይቼ ስለ መረጥኳችሁ፥ ዓለም ይጠላችኋል።
Tutki የዮሐንስ ወንጌል 15:19
Koti
Raamattu
Suunnitelmat
Videot