1
ወደ ሮም ሰዎች 12:2
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።
Cymharu
Archwiliwch ወደ ሮም ሰዎች 12:2
2
ወደ ሮም ሰዎች 12:1
እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።
Archwiliwch ወደ ሮም ሰዎች 12:1
3
ወደ ሮም ሰዎች 12:12
በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ፤
Archwiliwch ወደ ሮም ሰዎች 12:12
4
ወደ ሮም ሰዎች 12:21
ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።
Archwiliwch ወደ ሮም ሰዎች 12:21
5
ወደ ሮም ሰዎች 12:10
በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤
Archwiliwch ወደ ሮም ሰዎች 12:10
6
ወደ ሮም ሰዎች 12:9
ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን። ክፉውን ነገር ተጸየፉት፤ ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ፤
Archwiliwch ወደ ሮም ሰዎች 12:9
7
ወደ ሮም ሰዎች 12:18
ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።
Archwiliwch ወደ ሮም ሰዎች 12:18
8
ወደ ሮም ሰዎች 12:19
ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና።
Archwiliwch ወደ ሮም ሰዎች 12:19
9
ወደ ሮም ሰዎች 12:11
ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤
Archwiliwch ወደ ሮም ሰዎች 12:11
10
ወደ ሮም ሰዎች 12:3
እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ የእምነትን መጠን እንዳካፈለው፥ እንደ ባለ አእምሮ እንዲያስብ እንጂ ማሰብ ከሚገባው አልፎ በትዕቢት እንዳያስብ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ በተሰጠኝ ጸጋ እናገራለሁ።
Archwiliwch ወደ ሮም ሰዎች 12:3
11
ወደ ሮም ሰዎች 12:17
ለማንም ስለ ክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ።
Archwiliwch ወደ ሮም ሰዎች 12:17
12
ወደ ሮም ሰዎች 12:16
እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ፤ የትዕቢትን ነገር አታስቡ፥ ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ። ልባሞች የሆናችሁ አይምሰላችሁ።
Archwiliwch ወደ ሮም ሰዎች 12:16
13
ወደ ሮም ሰዎች 12:20
ጠላትህ ግን ቢራብ አብላው፤ ቢጠማ አጠጣው፤ ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና።
Archwiliwch ወደ ሮም ሰዎች 12:20
14
ወደ ሮም ሰዎች 12:14-15
የሚያሳድዱአችሁን መርቁ፥ መርቁ እንጂ አትርገሙ። ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፥ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ።
Archwiliwch ወደ ሮም ሰዎች 12:14-15
15
ወደ ሮም ሰዎች 12:13
ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ፤ እንግዶችን ለመቀበል ትጉ።
Archwiliwch ወደ ሮም ሰዎች 12:13
16
ወደ ሮም ሰዎች 12:4-5
በአንድ አካል ብዙ ብልቶች እንዳሉን፥ የብልቶቹም ሁሉ ሥራ አንድ እንዳይደለ፥ እንዲሁ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እርስ በርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው ብልቶች ነን።
Archwiliwch ወደ ሮም ሰዎች 12:4-5
Gartref
Beibl
Cynlluniau
Fideos