1
የማቴዎስ ወንጌል 14:30-31
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ነገር ግን የነፋሱን ኀይል አይቶ ፈራ፤ ወደ ባሕሩ ውስጥ መስጠም በጀመረ ጊዜ “ጌታ ሆይ! አድነኝ!” ሲል ጮኸ። ኢየሱስ ወዲያውኑ እጁን ዘርግቶ ያዘውና፦ “አንተ እምነት የጐደለህ! ስለምን ተጠራጠርክ?” አለው።
Cymharu
Archwiliwch የማቴዎስ ወንጌል 14:30-31
2
የማቴዎስ ወንጌል 14:30
ነገር ግን የነፋሱን ኀይል አይቶ ፈራ፤ ወደ ባሕሩ ውስጥ መስጠም በጀመረ ጊዜ “ጌታ ሆይ! አድነኝ!” ሲል ጮኸ።
Archwiliwch የማቴዎስ ወንጌል 14:30
3
የማቴዎስ ወንጌል 14:27
ኢየሱስም ወዲያውኑ “አይዞአችሁ! እኔ ነኝ፤ አትፍሩ!” አላቸው።
Archwiliwch የማቴዎስ ወንጌል 14:27
4
የማቴዎስ ወንጌል 14:28-29
በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ፥ “ጌታ ሆይ! አንተስ ከሆንክ በባሕሩ ላይ እየተራመድኩ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ!” አለው። ኢየሱስም “ና!” አለው። ስለዚህ ጴጥሮስ ከጀልባው ወርዶ ወደ ኢየሱስ ለመሄድ በባሕሩ ላይ ተራመደ።
Archwiliwch የማቴዎስ ወንጌል 14:28-29
5
የማቴዎስ ወንጌል 14:33
በጀልባውም ውስጥ የነበሩት ሁሉ “በእርግጥ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ!” ብለው ለኢየሱስ ሰገዱለት።
Archwiliwch የማቴዎስ ወንጌል 14:33
6
የማቴዎስ ወንጌል 14:16-17
ኢየሱስ ግን፦ “እናንተ የሚበሉትን ስጡአቸው እንጂ እነርሱ እንዲሁ ሊሄዱ አይገባም!” አላቸው። ደቀ መዛሙርቱም “እኛ እዚህ ያለን አምስት እንጀራና ሁለት ዓሣ ብቻ ነው” አሉት።
Archwiliwch የማቴዎስ ወንጌል 14:16-17
7
የማቴዎስ ወንጌል 14:18-19
ኢየሱስም “እነርሱኑ ወደ እኔ አምጡልኝ!” አላቸው። ከዚህ በኋላ ሕዝቡ በመስኩ ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ፤ አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሣ አንሥቶ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየና የምስጋና ጸሎት አደረገ፤ እንጀራውንም ቈርሶ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ ዐደሉ።
Archwiliwch የማቴዎስ ወንጌል 14:18-19
8
የማቴዎስ ወንጌል 14:20
ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ የተረፈውን ፍርፋሪ፥ ደቀ መዛሙርቱ በዐሥራ ሁለት መሶብ ሞልተው አነሡ።
Archwiliwch የማቴዎስ ወንጌል 14:20
Gartref
Beibl
Cynlluniau
Fideos