1
የዮሐንስ ወንጌል 15:5
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
“እኔ የወይን ግንድ ነኝ፤ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ፤ ብዙ ፍሬ የሚያፈራው በእኔ የሚኖርና እኔም በእርሱ የምኖርበት ነው፤ ነገር ግን ያለ እኔ ምንም ማድረግ አትችሉም።
Cymharu
Archwiliwch የዮሐንስ ወንጌል 15:5
2
የዮሐንስ ወንጌል 15:4
በእኔ ኑሩ፤ እኔም በእናንተ እኖራለሁ፤ ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ላይ ጸንቶ ካልኖረ በቀር በራሱ ብቻ ፍሬ ማፍራት እንደማይቻለው እናንተም በእኔ ካልኖራችሁ ፍሬ ማፍራት አትችሉም።
Archwiliwch የዮሐንስ ወንጌል 15:4
3
የዮሐንስ ወንጌል 15:7
በእኔ ብትኖሩ ቃሌም በእናንተ ቢኖር የፈለጋችሁትን ብትለምኑ ታገኛላችሁ።
Archwiliwch የዮሐንስ ወንጌል 15:7
4
የዮሐንስ ወንጌል 15:16
እኔ መረጥኳችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ ሄዳችሁ ብዙ ፍሬ እንድታፈሩ፥ ፍሬአችሁም ነዋሪ እንዲሆን ሾምኳችሁ። ስለዚህ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አብ ይሰጣችኋል።
Archwiliwch የዮሐንስ ወንጌል 15:16
5
የዮሐንስ ወንጌል 15:13
ሰው ሕይወቱን ስለ ወዳጆቹ አሳልፎ ከመስጠት የበለጠ ፍቅር የለውም።
Archwiliwch የዮሐንስ ወንጌል 15:13
6
የዮሐንስ ወንጌል 15:2
በእኔ ላይ ያለውን ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ አባቴ ቈርጦ ይጥለዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውን ቅርንጫፍ ግን አብዝቶ እንዲያፈራ ገርዞ ያጠራዋል።
Archwiliwch የዮሐንስ ወንጌል 15:2
7
የዮሐንስ ወንጌል 15:12
የእኔ ትእዛዝ እኔ እንደ ወደድኳችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው።
Archwiliwch የዮሐንስ ወንጌል 15:12
8
የዮሐንስ ወንጌል 15:8
ብዙ ፍሬ ስታፈሩ በዚህ አባቴ ይከብራል፤ እናንተም የእኔ ደቀ መዛሙርት መሆናችሁን ታሳያላችሁ።
Archwiliwch የዮሐንስ ወንጌል 15:8
9
የዮሐንስ ወንጌል 15:1
“እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ አትክልተኛውም አባቴ ነው፤
Archwiliwch የዮሐንስ ወንጌል 15:1
10
የዮሐንስ ወንጌል 15:6
በእኔ የማይኖር እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጪ ተጥሎ ይደርቃል፤ እንዲህ ያሉት ቅርንጫፎች ተሰብስበው ወደ እሳት ይጣሉና ይቃጠላሉ።
Archwiliwch የዮሐንስ ወንጌል 15:6
11
የዮሐንስ ወንጌል 15:11
ይህን የነገርኳችሁ ደስታዬ በእናንተ እንዲሆንና የእናንተም ደስታ ፍጹም እንዲሆን ነው።
Archwiliwch የዮሐንስ ወንጌል 15:11
12
የዮሐንስ ወንጌል 15:10
እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ፈጸምኩና በፍቅሩ እንደምኖር እናንተም የእኔን ትእዛዝ ብትፈጽሙ በፍቅሬ ትኖራላችሁ።
Archwiliwch የዮሐንስ ወንጌል 15:10
13
የዮሐንስ ወንጌል 15:17
እንግዲህ እኔ የማዛችሁ እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው።
Archwiliwch የዮሐንስ ወንጌል 15:17
14
የዮሐንስ ወንጌል 15:19
የዓለም ብትሆኑ ዓለም የራሱ የሆነውን በወደደ ነበር፤ ነገር ግን የዓለም ስላልሆናችሁና እኔ ከዓለም ለይቼ ስለ መረጥኳችሁ፥ ዓለም ይጠላችኋል።
Archwiliwch የዮሐንስ ወንጌል 15:19
Gartref
Beibl
Cynlluniau
Fideos