ሐዲስ ኪዳን በ 90 ቀናትናሙና

የዮሐንስ ራእይ መግቢያ
የዮሐንስ ራእይን የጻፈው እራሱ ሐዋርያው ዮሐንስ መሆኑን የምናረጋግጠው ስሙን በ 22 ቱ ምእራፎች ውስጥ አራት ግዜ በመጥቀሱ ሲሆን ከዚህ በፊትም የዮሐንስ ወንጌልን ፣ 1 ኛ የሐንስን ፣ 2 ተኛ ዮሐንስን እንዲሁም 3 ተኛ ዮሐንስን ጽፏል። መልእክቱ በዋነኝነት በእስያ ላሉት ሰባቱ አብያተ ክርስትያናት ሲሆን እነዚህም ኤፌሶን, ሰምርኔስ, ጴርጋሞን, ትያጥሮን, ሰርዴስ, ፊላደልፊያ, እና ሎዲቅያ ናቸው። የኢየሱስን የምሥራች በመስበክ በግዞት ከነበረበት ከፍጥሞ ደሴት ሆኖ በ 95 ዓ.ም አካባቢ እንደጻፈው ይታመናል።
ራእይ አፖካሊፕስ ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም የማይታወቅ ነገር ማለት ነው። ይህ መጽሐፍ በኢየሱስ አዳኝነት ያላመኑ ሰዎችን በፍርድ ጊዜ ስለሚያጋጥማቸው ነገር በትክክል ያሳያል። ስለዚህ አብዛኛው የመጽሐፉ ክፍሎች ምሳሌያዊ አገላለፆችን ይጠቀማል። የመጽሐፉ የመጨረሻዎቹ አራት ምዕራፎች የዚህን መጽሐፍ ዋና መልእክት የሚያስተላልፍ ሲሆን ይህም ክርስቶስ በክፋት ላይ ስለሚቀዳጀው ድል እና ለአማኞች ስለተዘጋጀው አዲሰ አለም ነው።
ስለዚህ እቅድ

በቀጣዩ 90 ቀናት ውስጥ የሐዲስ ኪዳንን 260 ምዕራፎች ከ ማቴዎስ ወንጌል በመጀመር የማርቆስ ወንጌልን ፣ የሉቃስ ወንጌልን ፣ የዮሐንስ ወንጌልን በማንበብ እስከ መጨረሻው መጽሐፍ የዮሐንስ ራእይ ድረስ ይዘልቃል።Journey through the 260 chapters of the New Testament over the next 90 days. From the gospels of Matthew, Mark, Luke, and John, all the way to the final book of Revelation, God will speak to you throughout the teachings of those who were transformed by our Savior.
More