ሐዲስ ኪዳን በ 90 ቀናትናሙና

የማርቆስ ወንጌል መግቢያ
ምንም እንኳን የማርቆስ ወንጌል በሐዲስ ኪዳን ውስጥ ሁለተኛው መጽሐፍ ቢሆንም በመጀመሪያ የተፃፈው ወንጌል ነው። ምሁራን ከ 55-65 ዓም ባለው ግዜ ውስጥ እንደተጻፈ ይናገራሉ። የማርቆስ ወንጌል ለአህዛብና ለሮማውያን ስለተፃፈ በርካታ የአይሁድ ባህሎችና ትውፊቶች ተብራርተው ይገኙበታል። በርካታ የማርቆስ ወንጌል ክፍሎች በቀሪዎቹ ወንጌሎች ውስጥም ተጠቅሰው እናገኛለን።
ማርቆስ የመጀመሪያውን ሐዋርያዊ አገልግሎት ከ ጳውሎስ ጋር አድርጓል። ከኢየሱስ 12 ቱ ሐዋርያት መካከል ለነበረው ጴጥሮስ ተከታይ እንደነበረ የሚታመነው ማርቆስ የበርናባስ አጎት ልጅም ነው። ማርቆስ የኢየሱስ የአይን ምስክር ባለመሆኑ ምክንያት ይህን መጽሐፍ ሲፅፍ ከጴጥሮስ በሰማው ምስክርነት ላይ በመመስረት ነው።
ስለዚህ እቅድ

በቀጣዩ 90 ቀናት ውስጥ የሐዲስ ኪዳንን 260 ምዕራፎች ከ ማቴዎስ ወንጌል በመጀመር የማርቆስ ወንጌልን ፣ የሉቃስ ወንጌልን ፣ የዮሐንስ ወንጌልን በማንበብ እስከ መጨረሻው መጽሐፍ የዮሐንስ ራእይ ድረስ ይዘልቃል።Journey through the 260 chapters of the New Testament over the next 90 days. From the gospels of Matthew, Mark, Luke, and John, all the way to the final book of Revelation, God will speak to you throughout the teachings of those who were transformed by our Savior.
More