ዘኍልቍ 5:6-7
ዘኍልቍ 5:6-7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ወንድ ወይም ሴት ቸል ብለው ወይም ባለማወቅ ሰው ከሚሠራው ኀጢአት ሁሉ የሠሩት ቢኖር፥ ያች ሰውነት ብትናዘዝ፥ ያደረገችውንም ኀጢአት ሁሉ ብትናገር የወሰደውን ዓይነቱን ሁሉ ይመልስ። አምስተኛ እጅም ለባለ ገንዘቡ ይጨምር።
ያጋሩ
ዘኍልቍ 5 ያንብቡዘኍልቍ 5:6-7 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፤ ‘ወንድም ሆነ ሴት በማናቸውም ረገድ ሌላውን ቢበድልና ከዚህም የተነሣ ለእግዚአብሔር ባይታመን በደለኛ ነው በሠራው ኀጢአት ይናዘዝ፤ ስለ በደሉም ሙሉ ካሳ ይክፈል፤ የተመደበበትም ካሳ ላይ አንድ ዐምስተኛ በመጨመር በደል ላደረሰበት ሰው ይስጥ፤
ያጋሩ
ዘኍልቍ 5 ያንብቡዘኍልቍ 5:6-7 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው፦ ወንድ ወይም ሴት የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይተላለፍ ዘንድ ሰው የሚሠራውን ኃጢአት ቢሠራ፥ በዚያም ሰው ላይ በደል ቢሆን፥ በሠራው ኃጢአት ይናዘዝ፤ የወሰደውንም በሙሉ ይመልስ አምስተኛውንም ይጨምርበት፥ ለበደለውም ሰው ይስጠው።
ያጋሩ
ዘኍልቍ 5 ያንብቡ