ኦሪት ዘኍልቊ 5:6-7

ኦሪት ዘኍልቊ 5:6-7 መቅካእኤ

“ለእስራኤል ልጆች ተናገር፦ ወንድ ወይም ሴት በጌታ ላይ ፈጽሞ እምነት በማጉደል ሰው የሚሠራውን ማናቸውንም ኃጢአት ቢሠሩ፥ የሠራው ያ ሰው በደለኛ ነው፥ የሠራውንም ኃጢአት ይናዘዝ፤ የወሰደውንም በሙሉ ይመልስ፥ በእርሱም ላይ አምስት እጅ ይጨምርበት፥ ለበደለውም ሰው ይስጠው።