ኦሪት ዘኊልቊ 5:6-7

ኦሪት ዘኊልቊ 5:6-7 አማ05

“ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ በላቸው፦ ከወንዶችም ሆኑ ከሴቶች ማናቸውም ሰው ለእግዚአብሔር ታማኝ ሆኖ ባለመገኘት በማንም ሰው ላይ በደል ቢፈጽም፥ ያ ሰው በደለኛ ነው። ኃጢአቱን ይናዘዝ፤ ስለ በደል ሊከፈል በሚገባው ዋጋ ላይ ከመቶ ኻያ እጅ በመጨመር ለተበደለው ሰው ካሳ ይስጥ።