ዮሐንስ 8:45-47
ዮሐንስ 8:45-47 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እኔ ግን እውነትን እናገራለሁና አታምኑኝም። ስለ ኀጢኣት ከእናንተ የሚወቅሰኝ ማን ነው? እኔ እውነት የምናገር ከሆንሁ ለምን አታምኑኝም? ከእግዚአብሔር የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል ይሰማል፤ ስለዚህ እናንተ አትሰሙኝም፤ ከእግዚአብሔር አይደላችሁምና።”
ያጋሩ
ዮሐንስ 8 ያንብቡዮሐንስ 8:45-47 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እኔ ግን እውነት ስለምናገር አታምኑኝም! ከእናንተ ስለ ኀጢአት በማስረጃ ሊከስሰኝ የሚችል አለን? እውነት የምናገር ከሆነ፣ ለምን አታምኑኝም? ከእግዚአብሔር የሆነ እግዚአብሔር የሚለውን ይሰማል፤ እናንተ ግን ከእግዚአብሔር ስላልሆናችሁ አትሰሙም።”
ያጋሩ
ዮሐንስ 8 ያንብቡዮሐንስ 8:45-47 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እኔ ግን እውነትን የምናገር ስለ ሆንሁ አታምኑኝም። ከእናንተ ስለ ኃጢአት የሚወቅሰኝ ማን ነው? እውነት የምናገር ከሆንሁ እናንተ ስለ ምን አታምኑኝም? ከእግዚአብሔር የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል ይሰማል፤ እናንተ ከእግዚአብሔር አይደላችሁምና ስለዚህ አትሰሙም።”
ያጋሩ
ዮሐንስ 8 ያንብቡ