ኦሪት ዘጸአት 7:1-6

ኦሪት ዘጸአት 7:1-6 አማ54

እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ “እይ፤ እኔ ለፈርዖን አምላክ አድርጌሃለሁ፤ ወንድምህም አሮን ነቢይ ይሆንልሃል። ያዘዝሁህን ነገር ሁሉ አንተ ትነግረዋለህ፤ ወንድምህም አሮን የእስራኤልን ልጆች ከአገሩ ይለቅቅ ዘንድ ከፈርዖን ጋር ይናገራል። እኔም የፈርዖንን ልብ አጸናለሁ፤ በግብፅ ምድርም ድንቄንና ተአምራቴን አበዛለሁ። ፈርዖንም አይሰማችሁም፤ እጄንም በግብፅ ላይ አደርጋለሁ፤ ሠራዊቴንም የእስራኤልን ልጆች ሕዝቤን በታላቅ ፍርድ ከግብፅ አገር አወጣለሁ። ግብፃውያንም፥ እጄን በግብፅ ላይ በዘረጋሁ ጊዜ፥ የእስራኤልንም ልጆች ከመካከላቸው ባወጣሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆነሁ ያውቃሉ።” ሙሴና አሮንም እንዲህ አደረጉ፤ እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው አደረጉ።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}