ዘፀአት 7:1-6

ዘፀአት 7:1-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “እነሆ፥ እኔ ለፈ​ር​ዖን አም​ላክ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ ወን​ድ​ም​ህም አሮን ነቢይ ይሆ​ን​ል​ሃል። ያዘ​ዝ​ሁ​ህን ነገር ሁሉ አንተ ትነ​ግ​ረ​ዋ​ለህ፤ ወን​ድ​ም​ህም አሮን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከሀ​ገሩ ይለ​ቅቅ ዘንድ ለፈ​ር​ዖን ይን​ገ​ረው። እኔም የፈ​ር​ዖ​ንን ልብ አጸ​ና​ለሁ፤ በግ​ብፅ ምድ​ርም ድን​ቄ​ንና ተአ​ም​ራ​ቴን አበ​ዛ​ለሁ። ፈር​ዖ​ንም አይ​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ እጄ​ንም በግ​ብፅ ላይ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ሕዝ​ቤን በኀ​ይሌ በታ​ላቅ ፍርድ ከግ​ብፅ ሀገር አወ​ጣ​ለሁ። ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም እጄን በግ​ብፅ ላይ በዘ​ረ​ጋሁ ጊዜ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው በአ​ወ​ጣሁ ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።” ሙሴና አሮ​ንም እን​ዲህ አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው አደ​ረጉ።