ኦሪት ዘጸአት 7:1-6

ኦሪት ዘጸአት 7:1-6 አማ05

እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እነሆ፥ እኔ አንተን ለፈርዖን እንደ አምላክ አደርግሃለሁ፤ ወንድምህም አሮን እንደ ነቢይ ሆኖ ስለ አንተ ይናገራል፤ እኔ የማዝህን ሁሉ ለአሮን ንገረው፤ እርሱም ከአገሩ እንዲወጡ እስራኤላውያንን ይለቅ ዘንድ ለንጉሡ ይነግረዋል፤ ነገር ግን እኔ የንጉሡን ልብ አደነድናለሁ፤ ከዚህም የተነሣ እኔ የቱንም ያኽል ምልክቶችንና ተአምራትን በግብጽ ምድር ባደርግ፥ እናንተን አይሰማችሁም፤ ከዚያን በኋላ በግብጽ ላይ በታላቅ ፍርድ ብርቱ ቅጣት በማምጣት ሠራዊቴን፥ ሕዝቤን የእስራኤልን ልጆች ከምድረ ግብጽ አስወጣቸዋለሁ። በዚህ ዐይነት የኀይል ክንዴን በእነርሱ ላይ አንሥቼ እስራኤላውያንን ከአገራቸው በማወጣበት ጊዜ ግብጻውያን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።” ሙሴና አሮንም እግዚአብሔር ያዘዛቸውን ሁሉ ፈጸሙ።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}