መጽሐፈ ሲራክ 40
40
የሰብአዊ ሕይወት ችግር
1የሰው የተፈጥሮው መከራ ታላቅ ነው፤
ከእናታቸው ማኅፀን ከሚወጡበት ጀምሮ በሁሉ እናት ሆድ እስኪቀበሩ ድረስ በአዳም ልጆች ላይ ከባድ ሸክም አለ።
2ዕለተ ሞትን ማሰብ በአዳም ልጆች ሁሉ ላይ የምታስደነግጥና ልብንም የምታስፈራ ናት።
3በመንግሥት ዙፋን ከሚቀመጥ ንጉሥ ጀምሮ
በዐመድና በትቢያ ላይ እስከሚተኛ ድሃ ድረስ፥
4ቀይ ግምጃ ከሚለብስና ዘውድ ከሚቀዳጅ ጀምሮ
የተናቀ ልብስን እስከሚለብስ ድረስ፥
5ቍጣና ቅንዓት፥ ንዝንዝና ሁከት፥ ሞትን መፍራትና ክርክር፥ ሐሜትም አለ፤
በመኝታው በተኛ ጊዜ የሌሊት እንቅልፍ አሳቡን ይለውጠዋል።
6ዕረፍቱ ጥቂት ወይም እንደ ኢምንት ነው፤
ይህ ሁሉ በመኝታው ይታወቃል፤
አንድ ጊዜ እንደ ሸንጎ ተከማችቶ ያገኘዋል፤
ከሰልፍ እንደሚሸሽ ሰውም የልቡናውን ምክር ያወላውላታል።
7የሸሸው ሰው ግን ዕለቱን ያመልጣል፤
ፍርሀቱንም እርሱ ራሱ ያደንቃታል፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሁሉም ደኅና ሲሆን ይነቃል ፍርሀቱም ሁሉ ከንቱ መሆኑን ሲያውቅ ይደነቃል” ይላል።
8ይህ ሁሉ በሰው ላይ እስከ እንስሳ ድረስ አለ፤
ይህም በኀጢአተኞች ሰዎች ላይ ሰባት እጥፍ ይብሳል።
9ሞትና መታበይ፥ ቸነፈርና ጦርነት፥ ቀጠናና የልብ ቍስል፥ መቅሠፍትም።
10ይህ ሁሉ በኀጢአተኛ ስዎች ላይ ተፈጠረ፤
በእነርሱም ምክንያት የጥፋት ውኃ መጣ።
11ሁሉ ከምድር ተፈጠረ፤ ሁሉም ወደ ምድር ይመለሳል፤
የወንዙ ውኃ ሁሉ ወደ ውቅያኖስ ይመለሳል።
የክፋት ውጤት
12መማለጃና ዐመፃ ሁሉ ይደመሰሳሉ፤
ሃይማኖት ግን ለዘለዓለሙ ትጸናለች።
13የዐመፃ ገንዘብ እንደ ፈሳሽ ውኃ ይደርቃል፤
በዘነበም ጊዜ እንደ ታላቅ መብረቅ ጩሆ ይጠፋል።
14እርሱ እጁን ከዘረጋ ደስ ያሰኛል፤
የሚክዱት ሰዎች ግን ፈጽመው ይጠፋሉ።
15የኀጢአተኞች ልጆች ቅርንጫፎቻቸው አይበዙም፤
የርኩሳን ሰዎች ሥራቸው በሚያድጥ ዓለት ላይ እንደ ወደቀ ዘር ነው።
16በውኃና በወንዝ ዳር የበቀለ አረምም ከሣሩ ሁሉ ቀድሞ ይነቀላል።
17ጸጋ ግን በበረከት እንደ እግዚአብሔር ገነት ናት፥
ምጽዋትም ለዘለዓለሙ ጸንቶ ይኖራል።
18የሚዘጋጅና የሚሠራ ሰው ሕይወቱ ጣፋጭ ነው፤
ከእነዚህም ከሁለቱ ይልቅ የተቀበረ ወርቅን ማግኘት ደስ ያሰኛል።
19ልጆችና የሀገር ሕንጻ ስምን ያስጠራሉ፤
ከእነዚህ ከሁለቱ ይልቅ ምንም ነውር የሌለባት ሴት ደስ ታሰኛለች።
20ወይንና ማሕሌት ልብን ደስ ያሰኛሉ፥
ከሁለቱም ይልቅ ጥበብን መውደድ ደስ ያሰኛል።
21በገናና መሰንቆ ሰውነትን ደስ ያሰኙኣታል፤
ከሁለቱም ይልቅ ልዝብ አንደበት ደስ ያሰኛል።
22ደም ግባትና ውበት ዐይንን ደስ ያሰኙኣታል።
ከሁለቱም ይልቅ ቡቃያ ደስ ያሰኛል።
23ወዳጅና ጓደኛ በዘመናቸው ይጠቅማሉ፤
ከሁለቱም ይልቅ ደግ ሴት ባሏን ትጠቅማለች።
24ወንድሞችና ረዳት በመከራ ቀን ይጠቅማሉ፤
ከሁለቱም ይልቅ ለማዳን ምጽዋት ትበልጣለች።
25ወርቅና ብር ሀገርን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እግርን” ይላል። ያጸናሉ፤
ከሁለቱም ይልቅ በጎ ምክር ደስ ታሰኛለች።
26ባለጸግነትና ገንዘብ ልቡናን ደስ ያሰኛሉ፤
ከሁለቱም ይልቅ እግዚአብሔርን መፍራት ደስ ያሰኛል፤
እግዚአብሔርን መፍራት የምታሳጣው የለም፤ አጋዥም አትሻም።
27እግዚአብሔርን መፍራት በበረከትዋ እንደ እግዚአብሔር ገነት ናት፤
ክብርና ደስታም ሁሉ በእርስዋ አለ።
28ልጄ ሆይ! በጉልበትህ ሳለህ ልመናን አትውደዳት፤
ከመለመን መሞት ይሻላል።
29የሌላ ማዕድ ደጅ የሚጠናና ተስፋ የሚያደርግ ሰው፤
ኑሮው እንደ ሞተ ሰው ነው፤
የሰው እህል የሚወድ ሰው ከሐሜት አይድንም፤
የተመከረ ብልህ ሰው ግን ከሁሉ ይጠበቃል።
30ለማያፍር ሰው አፍ ልመና ጣፋጭ ነው፤
በሆዱ ግን እሳት ትነድዳለች።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 40: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፈ ሲራክ 40
40
የሰብአዊ ሕይወት ችግር
1የሰው የተፈጥሮው መከራ ታላቅ ነው፤
ከእናታቸው ማኅፀን ከሚወጡበት ጀምሮ በሁሉ እናት ሆድ እስኪቀበሩ ድረስ በአዳም ልጆች ላይ ከባድ ሸክም አለ።
2ዕለተ ሞትን ማሰብ በአዳም ልጆች ሁሉ ላይ የምታስደነግጥና ልብንም የምታስፈራ ናት።
3በመንግሥት ዙፋን ከሚቀመጥ ንጉሥ ጀምሮ
በዐመድና በትቢያ ላይ እስከሚተኛ ድሃ ድረስ፥
4ቀይ ግምጃ ከሚለብስና ዘውድ ከሚቀዳጅ ጀምሮ
የተናቀ ልብስን እስከሚለብስ ድረስ፥
5ቍጣና ቅንዓት፥ ንዝንዝና ሁከት፥ ሞትን መፍራትና ክርክር፥ ሐሜትም አለ፤
በመኝታው በተኛ ጊዜ የሌሊት እንቅልፍ አሳቡን ይለውጠዋል።
6ዕረፍቱ ጥቂት ወይም እንደ ኢምንት ነው፤
ይህ ሁሉ በመኝታው ይታወቃል፤
አንድ ጊዜ እንደ ሸንጎ ተከማችቶ ያገኘዋል፤
ከሰልፍ እንደሚሸሽ ሰውም የልቡናውን ምክር ያወላውላታል።
7የሸሸው ሰው ግን ዕለቱን ያመልጣል፤
ፍርሀቱንም እርሱ ራሱ ያደንቃታል፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሁሉም ደኅና ሲሆን ይነቃል ፍርሀቱም ሁሉ ከንቱ መሆኑን ሲያውቅ ይደነቃል” ይላል።
8ይህ ሁሉ በሰው ላይ እስከ እንስሳ ድረስ አለ፤
ይህም በኀጢአተኞች ሰዎች ላይ ሰባት እጥፍ ይብሳል።
9ሞትና መታበይ፥ ቸነፈርና ጦርነት፥ ቀጠናና የልብ ቍስል፥ መቅሠፍትም።
10ይህ ሁሉ በኀጢአተኛ ስዎች ላይ ተፈጠረ፤
በእነርሱም ምክንያት የጥፋት ውኃ መጣ።
11ሁሉ ከምድር ተፈጠረ፤ ሁሉም ወደ ምድር ይመለሳል፤
የወንዙ ውኃ ሁሉ ወደ ውቅያኖስ ይመለሳል።
የክፋት ውጤት
12መማለጃና ዐመፃ ሁሉ ይደመሰሳሉ፤
ሃይማኖት ግን ለዘለዓለሙ ትጸናለች።
13የዐመፃ ገንዘብ እንደ ፈሳሽ ውኃ ይደርቃል፤
በዘነበም ጊዜ እንደ ታላቅ መብረቅ ጩሆ ይጠፋል።
14እርሱ እጁን ከዘረጋ ደስ ያሰኛል፤
የሚክዱት ሰዎች ግን ፈጽመው ይጠፋሉ።
15የኀጢአተኞች ልጆች ቅርንጫፎቻቸው አይበዙም፤
የርኩሳን ሰዎች ሥራቸው በሚያድጥ ዓለት ላይ እንደ ወደቀ ዘር ነው።
16በውኃና በወንዝ ዳር የበቀለ አረምም ከሣሩ ሁሉ ቀድሞ ይነቀላል።
17ጸጋ ግን በበረከት እንደ እግዚአብሔር ገነት ናት፥
ምጽዋትም ለዘለዓለሙ ጸንቶ ይኖራል።
18የሚዘጋጅና የሚሠራ ሰው ሕይወቱ ጣፋጭ ነው፤
ከእነዚህም ከሁለቱ ይልቅ የተቀበረ ወርቅን ማግኘት ደስ ያሰኛል።
19ልጆችና የሀገር ሕንጻ ስምን ያስጠራሉ፤
ከእነዚህ ከሁለቱ ይልቅ ምንም ነውር የሌለባት ሴት ደስ ታሰኛለች።
20ወይንና ማሕሌት ልብን ደስ ያሰኛሉ፥
ከሁለቱም ይልቅ ጥበብን መውደድ ደስ ያሰኛል።
21በገናና መሰንቆ ሰውነትን ደስ ያሰኙኣታል፤
ከሁለቱም ይልቅ ልዝብ አንደበት ደስ ያሰኛል።
22ደም ግባትና ውበት ዐይንን ደስ ያሰኙኣታል።
ከሁለቱም ይልቅ ቡቃያ ደስ ያሰኛል።
23ወዳጅና ጓደኛ በዘመናቸው ይጠቅማሉ፤
ከሁለቱም ይልቅ ደግ ሴት ባሏን ትጠቅማለች።
24ወንድሞችና ረዳት በመከራ ቀን ይጠቅማሉ፤
ከሁለቱም ይልቅ ለማዳን ምጽዋት ትበልጣለች።
25ወርቅና ብር ሀገርን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እግርን” ይላል። ያጸናሉ፤
ከሁለቱም ይልቅ በጎ ምክር ደስ ታሰኛለች።
26ባለጸግነትና ገንዘብ ልቡናን ደስ ያሰኛሉ፤
ከሁለቱም ይልቅ እግዚአብሔርን መፍራት ደስ ያሰኛል፤
እግዚአብሔርን መፍራት የምታሳጣው የለም፤ አጋዥም አትሻም።
27እግዚአብሔርን መፍራት በበረከትዋ እንደ እግዚአብሔር ገነት ናት፤
ክብርና ደስታም ሁሉ በእርስዋ አለ።
28ልጄ ሆይ! በጉልበትህ ሳለህ ልመናን አትውደዳት፤
ከመለመን መሞት ይሻላል።
29የሌላ ማዕድ ደጅ የሚጠናና ተስፋ የሚያደርግ ሰው፤
ኑሮው እንደ ሞተ ሰው ነው፤
የሰው እህል የሚወድ ሰው ከሐሜት አይድንም፤
የተመከረ ብልህ ሰው ግን ከሁሉ ይጠበቃል።
30ለማያፍር ሰው አፍ ልመና ጣፋጭ ነው፤
በሆዱ ግን እሳት ትነድዳለች።