መጽ​ሐፈ ሲራክ 40

40
የሰ​ብ​አዊ ሕይ​ወት ችግር
1የሰው የተ​ፈ​ጥ​ሮው መከራ ታላቅ ነው፤
ከእ​ና​ታ​ቸው ማኅ​ፀን ከሚ​ወ​ጡ​በት ጀምሮ በሁሉ እናት ሆድ እስ​ኪ​ቀ​በሩ ድረስ በአ​ዳም ልጆች ላይ ከባድ ሸክም አለ።
2ዕለተ ሞትን ማሰብ በአ​ዳም ልጆች ሁሉ ላይ የም​ታ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጥና ልብ​ንም የም​ታ​ስ​ፈራ ናት።
3በመ​ን​ግ​ሥት ዙፋን ከሚ​ቀ​መጥ ንጉሥ ጀምሮ
በዐ​መ​ድና በት​ቢያ ላይ እስ​ከ​ሚ​ተኛ ድሃ ድረስ፥
4ቀይ ግምጃ ከሚ​ለ​ብ​ስና ዘውድ ከሚ​ቀ​ዳጅ ጀምሮ
የተ​ናቀ ልብ​ስን እስ​ከ​ሚ​ለ​ብስ ድረስ፥
5ቍጣና ቅን​ዓት፥ ንዝ​ን​ዝና ሁከት፥ ሞትን መፍ​ራ​ትና ክር​ክር፥ ሐሜ​ትም አለ፤
በመ​ኝ​ታው በተኛ ጊዜ የሌ​ሊት እን​ቅ​ልፍ አሳ​ቡን ይለ​ው​ጠ​ዋል።
6ዕረ​ፍቱ ጥቂት ወይም እንደ ኢም​ንት ነው፤
ይህ ሁሉ በመ​ኝ​ታው ይታ​ወ​ቃል፤
አንድ ጊዜ እንደ ሸንጎ ተከ​ማ​ችቶ ያገ​ኘ​ዋል፤
ከሰ​ልፍ እን​ደ​ሚ​ሸሽ ሰውም የል​ቡ​ና​ውን ምክር ያወ​ላ​ው​ላ​ታል።
7የሸ​ሸው ሰው ግን ዕለ​ቱን ያመ​ል​ጣል፤
ፍር​ሀ​ቱ​ንም እርሱ ራሱ ያደ​ን​ቃ​ታል፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሁሉም ደኅና ሲሆን ይነ​ቃል ፍር​ሀ​ቱም ሁሉ ከንቱ መሆ​ኑን ሲያ​ውቅ ይደ​ነ​ቃል” ይላል።
8ይህ ሁሉ በሰው ላይ እስከ እን​ስሳ ድረስ አለ፤
ይህም በኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ሰዎች ላይ ሰባት እጥፍ ይብ​ሳል።
9ሞትና መታ​በይ፥ ቸነ​ፈ​ርና ጦር​ነት፥ ቀጠ​ናና የልብ ቍስል፥ መቅ​ሠ​ፍ​ትም።
10ይህ ሁሉ በኀ​ጢ​አ​ተኛ ስዎች ላይ ተፈ​ጠረ፤
በእ​ነ​ር​ሱም ምክ​ን​ያት የጥ​ፋት ውኃ መጣ።
11ሁሉ ከም​ድር ተፈ​ጠረ፤ ሁሉም ወደ ምድር ይመ​ለ​ሳል፤
የወ​ንዙ ውኃ ሁሉ ወደ ውቅ​ያ​ኖስ ይመ​ለ​ሳል።
የክ​ፋት ውጤት
12መማ​ለ​ጃና ዐመፃ ሁሉ ይደ​መ​ሰ​ሳሉ፤
ሃይ​ማ​ኖት ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ ትጸ​ና​ለች።
13የዐ​መፃ ገን​ዘብ እንደ ፈሳሽ ውኃ ይደ​ር​ቃል፤
በዘ​ነ​በም ጊዜ እንደ ታላቅ መብ​ረቅ ጩሆ ይጠ​ፋል።
14እርሱ እጁን ከዘ​ረጋ ደስ ያሰ​ኛል፤
የሚ​ክ​ዱት ሰዎች ግን ፈጽ​መው ይጠ​ፋሉ።
15የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ልጆች ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቻ​ቸው አይ​በ​ዙም፤
የር​ኩ​ሳን ሰዎች ሥራ​ቸው በሚ​ያ​ድጥ ዓለት ላይ እንደ ወደቀ ዘር ነው።
16በው​ኃና በወ​ንዝ ዳር የበ​ቀለ አረ​ምም ከሣሩ ሁሉ ቀድሞ ይነ​ቀ​ላል።
17ጸጋ ግን በበ​ረ​ከት እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገነት ናት፥
ምጽ​ዋ​ትም ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ ጸንቶ ይኖ​ራል።
18የሚ​ዘ​ጋ​ጅና የሚ​ሠራ ሰው ሕይ​ወቱ ጣፋጭ ነው፤
ከእ​ነ​ዚ​ህም ከሁ​ለቱ ይልቅ የተ​ቀ​በረ ወር​ቅን ማግ​ኘት ደስ ያሰ​ኛል።
19ልጆ​ችና የሀ​ገር ሕንጻ ስምን ያስ​ጠ​ራሉ፤
ከእ​ነ​ዚህ ከሁ​ለቱ ይልቅ ምንም ነውር የሌ​ለ​ባት ሴት ደስ ታሰ​ኛ​ለች።
20ወይ​ንና ማሕ​ሌት ልብን ደስ ያሰ​ኛሉ፥
ከሁ​ለ​ቱም ይልቅ ጥበ​ብን መው​ደድ ደስ ያሰ​ኛል።
21በገ​ናና መሰ​ንቆ ሰው​ነ​ትን ደስ ያሰ​ኙ​ኣ​ታል፤
ከሁ​ለ​ቱም ይልቅ ልዝብ አን​ደ​በት ደስ ያሰ​ኛል።
22ደም ግባ​ትና ውበት ዐይ​ንን ደስ ያሰ​ኙ​ኣ​ታል።
ከሁ​ለ​ቱም ይልቅ ቡቃያ ደስ ያሰ​ኛል።
23ወዳ​ጅና ጓደኛ በዘ​መ​ና​ቸው ይጠ​ቅ​ማሉ፤
ከሁ​ለ​ቱም ይልቅ ደግ ሴት ባሏን ትጠ​ቅ​ማ​ለች።
24ወን​ድ​ሞ​ችና ረዳት በመ​ከራ ቀን ይጠ​ቅ​ማሉ፤
ከሁ​ለ​ቱም ይልቅ ለማ​ዳን ምጽ​ዋት ትበ​ል​ጣ​ለች።
25ወር​ቅና ብር ሀገ​ርን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እግ​ርን” ይላል። ያጸ​ናሉ፤
ከሁ​ለ​ቱም ይልቅ በጎ ምክር ደስ ታሰ​ኛ​ለች።
26ባለ​ጸ​ግ​ነ​ትና ገን​ዘብ ልቡ​ናን ደስ ያሰ​ኛሉ፤
ከሁ​ለ​ቱም ይልቅ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ደስ ያሰ​ኛል፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት የም​ታ​ሳ​ጣው የለም፤ አጋ​ዥም አት​ሻም።
27እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት በበ​ረ​ከ​ትዋ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገነት ናት፤
ክብ​ርና ደስ​ታም ሁሉ በእ​ር​ስዋ አለ።
28ልጄ ሆይ! በጉ​ል​በ​ትህ ሳለህ ልመ​ናን አት​ው​ደ​ዳት፤
ከመ​ለ​መን መሞት ይሻ​ላል።
29የሌላ ማዕድ ደጅ የሚ​ጠ​ናና ተስፋ የሚ​ያ​ደ​ርግ ሰው፤
ኑሮው እንደ ሞተ ሰው ነው፤
የሰው እህል የሚ​ወድ ሰው ከሐ​ሜት አይ​ድ​ንም፤
የተ​መ​ከረ ብልህ ሰው ግን ከሁሉ ይጠ​በ​ቃል።
30ለማ​ያ​ፍር ሰው አፍ ልመና ጣፋጭ ነው፤
በሆዱ ግን እሳት ትነ​ድ​ዳ​ለች።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ