መጽ​ሐፈ ሲራክ 41

41
ስለ ሞት
1ሞት ሆይ፥ ሰው በደ​ኅና ሲኖር፥
በሁሉ ተዘ​ጋ​ጅቶ ሳለ፥ ኀይ​ልም ሳለው፥
ለመ​ብ​ላ​ትም ሆዱ ተከ​ፍቶ ሳለ፥
በሰው ላይ በም​ት​መጣ ጊዜ ስም አጠ​ራ​ርህ እን​ዴት መራራ ነው!
2ሞት ሆይ፥ ኀይል በሌ​ለው፥ ፈጽ​ሞም ባረጀ፥
ሊያ​ደ​ር​ገ​ውም የሚ​ችል ምንም በሌ​ለው፥ የሚ​ያ​ው​ቀ​ውም በሌ​ለው፥
በድሃ ሰው ላይ በም​ት​መጣ ጊዜ ፍር​ድህ እን​ዴት መል​ካም ነው!
3የሞ​ትን ፍርድ አት​ፍራ፤
ከአ​ን​ተም በፊት የነ​በ​ሩ​ት​ንና ከአ​ን​ተም በኋላ የሚ​ነ​ሡ​ትን አስ​ባ​ቸው።
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ በሰው ሁሉ ላይ ነው፤
4እን​ግ​ዲህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈቃድ ለምን ትነ​ቅ​ፋ​ለህ?
ዐሥር ዓመት፥ መቶ ዓመት፥ ሺህ ዓመ​ትም በሕ​ይ​ወት ብት​ኖር፥
ከሞት ጋራ ክር​ክር የለ​ህም።
5የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ሰዎች ልጆች ጐስ​ቋ​ሎች ልጆች ይሆ​ናሉ፤
የክ​ፉ​ዎች ሰዎ​ችም ቤታ​ቸው ይፈ​ር​ሳል።
6የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ልጆች ርስ​ታ​ቸ​ውን ያጣሉ፤
ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ከዘ​ራ​ቸው ጋር አደገ።
7ስለ እርሱ ይዋ​ረ​ዳ​ሉና፥
የኀ​ጢ​አ​ተኛ አባት ልጆች ይጐ​ሰ​ቍ​ላሉ።
8የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ላፈ​ረ​ሳ​ችሁ
ኀጢ​አ​ተ​ኞች ሰዎች ወዮ​ላ​ችሁ!
9ብት​ወ​ል​ዱም ለር​ግ​ማን ትወ​ል​ዳ​ላ​ቸሁ፤
ብት​ሞ​ቱም ዕድል ፋን​ታ​ችሁ ርግ​ማን ነው።
10ሁሉ ከም​ድር ተፈ​ጠረ፤ መመ​ለ​ሻ​ውም ወደ ምድር ነው፤
ኀጢ​አ​ተ​ኞ​ችም እን​ዲሁ ከር​ግ​ማን ወደ ጥፋት ይሄ​ዳሉ።
11የሰው ኀዘኑ ስለ ሰው​ነቱ ነው፤
የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችም ስማ​ቸው ይደ​መ​ሰ​ሳል።
12መል​ካም ስምን ታስ​ጠራ ዘንድ አስብ፤
ከሺህ ታላ​ላቅ የወ​ርቅ መዛ​ግ​ብ​ትም እርሱ ብቻ ይቀ​ር​ሃል።
13በዘ​መ​ንህ ቍጥር በደ​ስታ መኖር መል​ካም ነው፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጸንቶ ይኖ​ር​ል​ሃ​ልና መል​ካም ስም ይሻ​ላል።
14ጥበብ ግን ልጆ​ች​ዋን በሰ​ላም ትጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋ​ለች፤
የተ​ሰ​ወረ ጥበ​ብና የማ​ይ​ታይ ድልብ፥ የሁ​ለቱ ጥቅ​ማ​ቸው ምን​ድን ነው?
15ጥበ​ቡን ከሚ​ሰ​ውር ሰው፤
ስን​ፍ​ና​ውን የሚ​ሰ​ውር ሰው ይሻ​ላል።
16እን​ግ​ዲህ ቃሌ​ንና ጥበ​ቤን#“ጥበ​ቤን” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። እፈሩ፤
የሚ​ያ​ፍር ሁሉ በበጎ ይጠ​በ​ቃል፤
በሁሉ ይማ​ከር ዘንድ ሁሉ የታ​መነ አይ​ደ​ለም።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “... ኀፍ​ረ​ትን መጠ​በቅ መል​ካም አይ​ደ​ለ​ምና በማ​ን​ኛ​ውም ነገር ሁሉን ማረ​ጋ​ገጥ አይ​ቻ​ል​ምና” ይላል።
17ልጅ እን​ወ​ል​ዳ​ለን ብለው በዝ​ሙት መኖር፤
ለአ​ባ​ትና ለእ​ናት ኀፍ​ረት ነው#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በአ​ባ​ትና በእ​ናት ፊት አመ​ን​ዝራ ከመ​ሆን እፈሩ” ይላል። ለአ​ለ​ቃና ለታ​ላ​ላ​ቆ​ችም መዋ​ሸት ኀፍ​ረት ነው።
18ለሹ​ምና ለዳኛ ቃል መለ​ወጥ ኀፍ​ረት ነው።
ለማ​ኅ​በ​ርና ለሕ​ዝ​ብም መሳት ኀፍ​ረት ነው፤
ከጓ​ደ​ኛ​ህና ከወ​ዳ​ጅህ ጋር መከ​ዳ​ዳት ኀፍ​ረት ነው።
19ለእ​ን​ግዳ በእ​ን​ግ​ድ​ነት ካደ​ረ​በት ቤት ሰርቆ መሄድ ኀፍ​ረት ነው፤
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም እው​ነ​ትና ቃል ኪዳን ማፍ​ረስ ኀፍ​ረት ነው፤
የሌላ ሰው እህል ለመ​ብ​ላት በመ​ስ​ገ​ብ​ገብ መቅ​ረብ ኀፍ​ረት ነው፤
አደራ ከአ​ስ​ጠ​በ​ቁህ ገን​ዝ​ብና ከባ​ል​ን​ጀ​ራህ ገን​ዘብ መስ​ረቅ ኀፍ​ረት ነው።#ግሪክ ሰባ. ሊ. ልዩ ነው።
20የሚ​ጠ​ራ​ህን ሰው ቸል ማለት ኀፍ​ረት ነው፤#ግሪኩ “ሰላ​ምታ ለሚ​ሰ​ጥህ ሰላ​ም​ታን አለ​መ​ስ​ጠት” ይላል።
ወደ ሌላ ሰው ሚስ​ትም መመ​ል​ከት ኀፍ​ረት ነው።
21በመ​ከ​ራው ጊዜ ባል​ን​ጀ​ራ​ህን ቸል ማለት ኀፍ​ረት ነው፤
በሌላ ሰው ገን​ዘ​ብም መሳ​ሳት ኀፍ​ረት ነው።
የጎ​ል​ማሳ ሚስት ማነ​ጋ​ገ​ርም ኀፍ​ረት ነው።
22ገረ​ዱ​ንም አታ​ባ​ብ​ላት፤ ወደ መኝ​ታ​ዋም አት​ቅ​ረብ፤
ወዳ​ጅ​ህን መሳ​ደብ ኀፍ​ረት ነው፤
ከሰ​ጠ​ኸ​ውም በኋላ አት​ሳ​ደብ፤ የሰ​ማ​ኸ​ውን ነገር ማው​ጣት፥ መና​ገ​ርም ኀፍ​ረት ነው።
ምሥ​ጢ​ር​ንም መግ​ለጥ ኀፍ​ረት ነው፤
23ይህን ብት​ጠ​ብቅ በእ​ው​ነት ኀፊረ ገጽ ያለህ ትሆ​ና​ለህ፤
በሰ​ውም ሁሉ ዘንድ መወ​ደ​ድን ታገ​ኛ​ለህ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ