መጽ​ሐፈ ሲራክ 39

39
1ጥበ​ብስ በቀ​ደሙ ሰዎች ሁሉ ዘንድ ተመ​ረ​መ​ረች።
2በሃ​ይ​ማ​ኖት ስማ​ቸ​ውን ላስ​ጠሩ ሰዎች ትን​ቢ​ትን ታስ​ተ​ም​ራ​ለች፤
ወደ ነቢ​ያ​ትም ምሳሌ ታገ​ባ​ለች።
3የተ​ሰ​ወ​ረ​ው​ንም ምሳሌ ትመ​ረ​ም​ራ​ለች፤
ምሳ​ሌ​ው​ንም ወደ መተ​ር​ጐም ትመ​ል​ሳ​ለች።#ምዕ. 39 ከቍ. 1 እስከ 3 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ልዩ ነው።
4በመ​ኳ​ን​ን​ትም መካ​ከል ትጠ​ቅ​ማ​ለች፤
በአ​ለ​ቆ​ችም መካ​ከል ትታ​ያ​ለች፤
ልዩ ወደ ሆኑ ወደ አሕ​ዛ​ብም ሀገር ትገ​ባ​ለች፤
5ሰዎ​ችን በበ​ጎም፥ በክ​ፉም ትፈ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለ​ችና፥
ወደ ፈጣ​ሪው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሄድ ዘንድ፥
በል​ዑ​ልም ፊት ይጸ​ልይ ዘንድ ልቡን ይመ​ል​ሳል፤
አፉ​ንም ይከ​ፍ​ታል፤ ይለ​ም​ና​ልም፤ ስለ ኀጢ​አ​ቱም ይና​ዘ​ዛል።
6ነገር ግን ገናና የሆ​ነው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፈ​ቀደ፥
የጥ​በ​ብ​ንም መን​ፈስ ካሳ​ደ​ረ​በት፥ እርሱ የጥ​በ​ቡን ነገር ያፈ​ል​ቃል፤
በጸ​ሎ​ቱም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይገ​ዛል።
7እር​ሱም ጥበ​ብ​ንና ምክ​ርን ይገ​ል​ጥ​ለ​ታል፤
የተ​ሰ​ወ​ረ​ው​ንም ያውቅ ዘንድ ያሳ​ስ​በ​ዋል።
8እር​ሱም የት​ም​ህ​ር​ቱን ጥበብ ያሳ​ያል፤
በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የኪ​ዳን ሕግም ይመ​ካል።
9ስለ ጥበ​ቡም ብዙ ሰዎች ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙም አይ​ደ​መ​ሰ​ስም፤ ስም አጠ​ራ​ሩም አይ​ጠ​ፋም፤
ስሙም ለልጅ ልጅ ጸንቶ ይኖ​ራል።
10አሕ​ዛ​ብም ጥበ​ቡን ይና​ገ​ራሉ፤
በሸ​ንጎ መካ​ከ​ልም ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።
11ከሺህ ልጅ ስምን ማስ​ጠ​ራት ይሻ​ላል፤
ከሞ​ተም በኋላ ሥራው ጸንቶ ይኖ​ራል።
የም​ስ​ጋና መዝ​ሙር
12ዳግ​መ​ኛም አስቤ እና​ገ​ራ​ለሁ፤
እንደ ሙሉ ጨረቃ ሙሉ ነኝና።
13የጻ​ድ​ቃን ልጆች ስሙኝ፤ ለም​ልሙ፤ ታደሱ፤
አበባ በም​ድረ በዳ ጠል እን​ደ​ሚ​ያ​ብብ አብቡ።
14እንደ ሊባ​ኖስ መዓዛ መዓ​ዛ​ችሁ ይጣ​ፍጥ፤
አበ​ባ​ች​ሁን እንደ ጽጌ​ረዳ አብ​ቅሉ ፤
መዓ​ዛ​ች​ሁ​ንም አጣ​ፍጡ፤
መዝ​ሙ​ርን ዘምሩ፤ በሥ​ራ​ውም ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት።
15ስሙን አግ​ን​ኑት፤
በአ​ንድ ሺህ#ግሪኩ “በከ​ን​ፈ​ራ​ችሁ መዝ​ሙር” ይላል። መዝ​ሙ​ርና በመ​ሰ​ንቆ ስሙን አግ​ን​ኑት
በም​ታ​መ​ሰ​ግ​ኑ​ትም ጊዜ እን​ዲህ በሉ።
16“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራው ገናና ነው።
እጅ​ግም ያማረ ነው፤ ሥር​ዐ​ቱም ሁሉ በየ​ጊ​ዜው ነው።”
17“ይህ ለም​ን​ድን ነው? ያስ ለም​ን​ድን ነው?” ማለት አይ​ገ​ባም፤
ሁሉም በጊ​ዜው ይፈ​ቀ​ዳል፤
ውኃ​ው​ንም በቃሉ እንደ ግድ​ግዳ አጸ​ናው፤
በአፉ ቃልም እንደ ኵሬ ውኃ፤
18በት​እ​ዛ​ዙም ሁሉ የተ​ወ​ደደ ነው፤
መድ​ኀ​ኒ​ት​ነ​ቱ​ንም የሚ​ያ​ጐ​ድል የለም።
19የሰው ሁሉ ሥራ በፊቱ ነው፤
ከዐ​ይ​ኖ​ቹም ፊት መሰ​ወር የሚ​ችል የለም።
20ዓለም ሳይ​ፈ​ጠር እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ ሁሉን ዐወቀ፤
በፊ​ቱም ምንም ልዩ ፍጥ​ረት የለም።
21ሁሉም ለመ​ፍ​ቅ​ዳ​ቸው ተፈ​ጥ​ሯ​ልና
“ይህ ለም​ን​ድን ነው? ያስ ለም​ን​ድን ነው?” የሚል የለም።
22በረ​ከ​ቱም እንደ ፈሳሽ ውኃ መላች፤
እንደ ጎርፍ ውኃም ምድ​ርን አረ​ካ​ቻት፤
23እን​ደ​ዚሁ ቍጣው አሕ​ዛ​ብን ከፈ​ለ​ቻ​ቸው።
24የጻ​ድቅ መን​ገዱ የቀና ነው፤
የኃ​ጥእ መን​ገድ ግን ዕን​ቅ​ፋት ነው፤
ውኃ​ው​ንም የሚ​ለ​ው​ጠው፥ ጨውም የሚ​ያ​ደ​ር​ገው እርሱ ነው።
25በጎ ነገር ከጥ​ንት ጀምሮ ለበጎ ሰዎች ተፈ​ጠ​ረች፤
እን​ደ​ዚሁ ክፉ ነገ​ርም ለኃ​ጢ​አ​ተ​ኞች ተፈ​ጠ​ረች።
26የሰው የመ​ፍ​ቅዱ ሁሉ መጀ​መ​ሪያ፥
ውኃ፥ እሳት፥ ብረት፥ ጨው፥ እህል፥ ስንዴ፥
ማር፥ ወተት፥ ወይን፥ ዘይ​ትና ልብስ ነው።
27ይህ ሁሉ ለጻ​ድ​ቃን ሰዎች በረ​ከ​ታ​ቸው ነው፤
እን​ደ​ዚ​ሁም ሁሉ በኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ሰዎች ወደ ክፉ ይመ​ለ​ስ​ባ​ቸ​ዋል።
28ለበ​ቀል የተ​ፈ​ጠ​ረች መን​ፈስ አለች፤
በጥ​ፋ​ታ​ቸው መቅ​ሠ​ፍ​ታ​ቸ​ውን ያበ​ዟ​ታል፤
በዘ​መ​ና​ቸው ኀይ​ላ​ቸው ይደ​ክ​ማል፤
የፈ​ጣ​ሪ​ያ​ቸው መቅ​ሠ​ፍ​ትም ይመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋል።
29እሳት፥ በረድ፥ ረኃ​ብና ቸነ​ፈር ይህ ሁሉ ለበ​ቀል ተፈ​ጠረ።
30የም​ድር አራ​ዊት ጥርስ ጊን​ጥና እፉ​ኝት፥
ጦርም ኀጢ​አ​ተ​ኞ​ችን ታጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ተፈ​ጠ​ረች።
31እርሱ ግን በይ​ቅ​ር​ታው ደስ ያሰ​ኛል፤
የዓ​ለ​ም​ንም መፍ​ቅድ ያዘ​ጋ​ጃል።
ሁሉም ጊዜው ከደ​ረሰ ከዕ​ድ​ሜው አያ​ል​ፍም።
32ስለ​ዚህ ነገር ከጥ​ንት ጀምሮ ሁሉም ተዘ​ጋጀ፤
ይህ​ንም አስቤ በመ​ጽ​ሐፍ ጻፍ​ሁት።
33የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራው ሁሉ ያማረ ነውና፤
ለሰ​ውም በየ​ጊ​ዜው መፍ​ቅ​ዱን ይሰ​ጣል።
34“ይህን ክፉ ፈጠ​ርህ፤ ያንም አሳ​መ​ርህ” የሚ​ለው የለም።
ሁሉን ቀኑ ይገ​ል​ጠ​ዋ​ልና።
35አሁ​ንም በፍ​ጹም ልቡ​ና​ችሁ፤ በፍ​ጹ​ምም አን​ደ​በ​ታ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት፤
ሁል​ጊ​ዜም ለስሙ ምስ​ጋና አቅ​ርቡ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ