መጽ​ሐፈ ሲራክ 28

28
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለሚ​ታ​ገሥ ሰው ይበ​ቀ​ል​ለ​ታል፤
ኀጢ​አ​ቱ​ንም ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ተበ​ቃይ ሰው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀ​ልን ያገ​ኛል ፤ ኀጢ​አ​ቱ​ንም በእ​ው​ነት ይጠ​ባ​በ​ቃል” ይላል።
2ባል​ን​ጀ​ራህ የበ​ደ​ለ​ህን በደል ይቅር በለው፥
የዚ​ያን ጊዜ ንስሓ ከገ​ባህ ኀጢ​አ​ት​ህን ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ል​ሃል።
3አንተ ሰው ስት​ሆን እንደ አንተ ያለ​ውን ሰው ከተ​ቀ​የ​ምህ፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዴት ይቅር በለኝ ትለ​ዋ​ለህ?
4እንደ አንተ ያለ ሰውን ይቅር ሳትል፥
ኀጢ​አ​ት​ህን ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ልህ ዘንድ እን​ግ​ዲህ እን​ዴት ትለ​ም​ነ​ዋ​ለህ?
5ሥጋ ለባሹ ቂመኛ ከሆነ
ኀጢ​አ​ቱን ማን ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል?
6ፍጻ​ሜ​ህን ዐስ​በህ ጠብን ተዋት።
ሞት​ንና ሙስና መቃ​ብ​ርን ዐስብ፤ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ጠብቅ።
7ሕጉን ዐስ​በህ ባል​ን​ጀ​ራ​ህን አት​ቀ​የም፤
የል​ዑ​ልን ፍር​ዱን ዐስ​በህ ቍጣን አር​ቃት።
8ኀጢ​አ​ቶ​ች​ህን ታሳ​ን​ስ​ልህ ዘንድ ክር​ክ​ርን ተዋት፤
ቍጡ ሰው ክር​ክ​ርን ያነ​ሣ​ሣል።
9ኀጢ​አ​ተኛ ሰውም ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ያደ​ክ​ማል፤
ወዳ​ጆ​ቹ​ንም ያጣ​ላል።
10በእ​ን​ጨቱ ልክ የእ​ሳቱ ነዲድ ይበ​ዛል፤
በክ​ር​ክ​ሩም ብዛት መጠን ጠቡ ይበ​ዛል፤
የሰው ኀይሉ በቁ​መቱ መጠን ነው፤
በባ​ለ​ጸ​ግ​ነ​ቱም ብዛት መጠን ቍጣ​ውን ያበ​ዛ​ታል።
11መታ​በ​ይን የሚ​ያ​በ​ዛት ሰው እሳ​ትን ያቀ​ጣ​ጥ​ላ​ታል፤
ለጠብ የሚ​ቸ​ኵል ሰውም ፈጥኖ ደምን ያፈ​ስ​ሳል።
ክፉ ምላስ
12ፍምን እፍ ብት​ላት ትነ​ድ​ዳ​ለች፤
ትፍ ብት​ል​ባ​ትም ትጠ​ፋ​ለች፤ ሁለ​ቱም ከአ​ንድ አፍ ይወ​ጣሉ።
13ሐሜ​ተ​ኛ​ንና ሁለት አን​ደ​በት ያለ​ውን ሰው ይረ​ግ​ሙ​ታል፤
ብዙ ወዳ​ጆ​ችን አጋ​ድ​ሎ​አ​ልና።
14ነገረ ሠሪ አን​ደ​በት ብዙ ሰዎ​ችን አወ​ካ​ቸው፤
ከሕ​ዝ​ብም ወደ ሕዝብ አሳ​ደ​ዳ​ቸው።
የጸኑ ከተ​ሞ​ች​ንም አፈ​ረሰ፤
የመ​ኳ​ን​ን​ቱ​ንም ቤት ጣለ።
15ቀባ​ጣሪ አን​ደ​በት ደጋግ ሴቶ​ችን ከባ​ሎ​ቻ​ቸው ቤት አስ​ወ​ጥታ ሰደ​ደ​ቻ​ቸው፤
ገን​ዘ​ባ​ቸ​ው​ንም አጠ​ፋ​ች​ባ​ቸው።
16ከእ​ር​ስዋ ያል​ተ​ጠ​በቀ ሰው ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ አያ​ር​ፍም፤
በሰ​ላ​ምም አይ​ኖ​ርም።
17የግ​ር​ፋት ቍስል መግል ይይ​ዛል፤
የአ​ን​ደ​በት ቍስል ግን አጥ​ን​ትን ይሰ​ብ​ራል።
18በጦር የወ​ደቁ ሰዎች ብዙ ናቸው፤
ነገር ግን በአ​ን​ደ​በት እንደ ጠፉ አይ​ደ​ሉም።
19ከእ​ርሷ የዳ​ነና በጥ​ፋ​ትዋ ያል​ተ​ሰ​ነ​ካ​ከለ፥
በቀ​ን​በ​ሯም ያላ​ረሰ፥ በእ​ግር ብረ​ት​ዋም ያል​ታ​ሰረ ብፁዕ ነው።
20ቀን​በ​ርዋ የብ​ረት ቀን​በር ነውና፤
እግር ብረ​ቷም የብ​ርት ነውና።
21ሞት​ዋም ክፉ ሞት ነው፤
ከእ​ር​ስ​ዋም ሲኦል ትቀ​ላ​ለች።
22በጻ​ድ​ቃን ግን አት​ደ​ር​ስ​ባ​ቸ​ውም፤
በእ​ሳ​ቷም አይ​ቃ​ጠ​ሉም።
23እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የዘ​ነጉ ሰዎች በእ​ር​ስዋ ይወ​ድ​ቃሉ፤
በማ​ይ​ጠፋ እሳ​ት​ዋም ታቃ​ጥ​ላ​ቸ​ዋ​ለች።
እንደ አን​በ​ሳም ትወ​ረ​ወ​ር​ባ​ቸ​ዋ​ለች፤
እንደ ነብ​ርም ትይ​ዛ​ቸ​ዋ​ለች።
24ንብ​ረ​ት​ህን በእ​ሾህ ብታ​ጥር፥
ወር​ቅ​ህ​ንና ብር​ህ​ንም ብት​ቈ​ልፍ፥
25ነገ​ር​ህን በሚ​ዛን ብት​መ​ዝን፥
ለአ​ፍ​ህም መዝ​ጊ​ያና ቍልፍ ብታ​ደ​ርግ፥
26ዳግ​መ​ኛም በአ​ን​ደ​በ​ትህ እን​ዳ​ት​ሰ​ነ​ካ​ከል፥
በሚ​ያ​ድ​ን​ህም ፊት እን​ዳ​ት​ጥ​ልህ ተጠ​በቅ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ