መጽሐፈ ሲራክ 28
28
1እግዚአብሔርን ለሚታገሥ ሰው ይበቀልለታል፤
ኀጢአቱንም ያስተሰርይለታል።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ተበቃይ ሰው ከእግዚአብሔር በቀልን ያገኛል ፤ ኀጢአቱንም በእውነት ይጠባበቃል” ይላል።
2ባልንጀራህ የበደለህን በደል ይቅር በለው፥
የዚያን ጊዜ ንስሓ ከገባህ ኀጢአትህን ያስተሰርይልሃል።
3አንተ ሰው ስትሆን እንደ አንተ ያለውን ሰው ከተቀየምህ፥
እግዚአብሔርን እንዴት ይቅር በለኝ ትለዋለህ?
4እንደ አንተ ያለ ሰውን ይቅር ሳትል፥
ኀጢአትህን ያስተሰርይልህ ዘንድ እንግዲህ እንዴት ትለምነዋለህ?
5ሥጋ ለባሹ ቂመኛ ከሆነ
ኀጢአቱን ማን ያስተሰርይለታል?
6ፍጻሜህን ዐስበህ ጠብን ተዋት።
ሞትንና ሙስና መቃብርን ዐስብ፤ ትእዛዙንም ጠብቅ።
7ሕጉን ዐስበህ ባልንጀራህን አትቀየም፤
የልዑልን ፍርዱን ዐስበህ ቍጣን አርቃት።
8ኀጢአቶችህን ታሳንስልህ ዘንድ ክርክርን ተዋት፤
ቍጡ ሰው ክርክርን ያነሣሣል።
9ኀጢአተኛ ሰውም ባልንጀራውን ያደክማል፤
ወዳጆቹንም ያጣላል።
10በእንጨቱ ልክ የእሳቱ ነዲድ ይበዛል፤
በክርክሩም ብዛት መጠን ጠቡ ይበዛል፤
የሰው ኀይሉ በቁመቱ መጠን ነው፤
በባለጸግነቱም ብዛት መጠን ቍጣውን ያበዛታል።
11መታበይን የሚያበዛት ሰው እሳትን ያቀጣጥላታል፤
ለጠብ የሚቸኵል ሰውም ፈጥኖ ደምን ያፈስሳል።
ክፉ ምላስ
12ፍምን እፍ ብትላት ትነድዳለች፤
ትፍ ብትልባትም ትጠፋለች፤ ሁለቱም ከአንድ አፍ ይወጣሉ።
13ሐሜተኛንና ሁለት አንደበት ያለውን ሰው ይረግሙታል፤
ብዙ ወዳጆችን አጋድሎአልና።
14ነገረ ሠሪ አንደበት ብዙ ሰዎችን አወካቸው፤
ከሕዝብም ወደ ሕዝብ አሳደዳቸው።
የጸኑ ከተሞችንም አፈረሰ፤
የመኳንንቱንም ቤት ጣለ።
15ቀባጣሪ አንደበት ደጋግ ሴቶችን ከባሎቻቸው ቤት አስወጥታ ሰደደቻቸው፤
ገንዘባቸውንም አጠፋችባቸው።
16ከእርስዋ ያልተጠበቀ ሰው ግን ለዘለዓለሙ አያርፍም፤
በሰላምም አይኖርም።
17የግርፋት ቍስል መግል ይይዛል፤
የአንደበት ቍስል ግን አጥንትን ይሰብራል።
18በጦር የወደቁ ሰዎች ብዙ ናቸው፤
ነገር ግን በአንደበት እንደ ጠፉ አይደሉም።
19ከእርሷ የዳነና በጥፋትዋ ያልተሰነካከለ፥
በቀንበሯም ያላረሰ፥ በእግር ብረትዋም ያልታሰረ ብፁዕ ነው።
20ቀንበርዋ የብረት ቀንበር ነውና፤
እግር ብረቷም የብርት ነውና።
21ሞትዋም ክፉ ሞት ነው፤
ከእርስዋም ሲኦል ትቀላለች።
22በጻድቃን ግን አትደርስባቸውም፤
በእሳቷም አይቃጠሉም።
23እግዚአብሔርን የዘነጉ ሰዎች በእርስዋ ይወድቃሉ፤
በማይጠፋ እሳትዋም ታቃጥላቸዋለች።
እንደ አንበሳም ትወረወርባቸዋለች፤
እንደ ነብርም ትይዛቸዋለች።
24ንብረትህን በእሾህ ብታጥር፥
ወርቅህንና ብርህንም ብትቈልፍ፥
25ነገርህን በሚዛን ብትመዝን፥
ለአፍህም መዝጊያና ቍልፍ ብታደርግ፥
26ዳግመኛም በአንደበትህ እንዳትሰነካከል፥
በሚያድንህም ፊት እንዳትጥልህ ተጠበቅ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 28: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፈ ሲራክ 28
28
1እግዚአብሔርን ለሚታገሥ ሰው ይበቀልለታል፤
ኀጢአቱንም ያስተሰርይለታል።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ተበቃይ ሰው ከእግዚአብሔር በቀልን ያገኛል ፤ ኀጢአቱንም በእውነት ይጠባበቃል” ይላል።
2ባልንጀራህ የበደለህን በደል ይቅር በለው፥
የዚያን ጊዜ ንስሓ ከገባህ ኀጢአትህን ያስተሰርይልሃል።
3አንተ ሰው ስትሆን እንደ አንተ ያለውን ሰው ከተቀየምህ፥
እግዚአብሔርን እንዴት ይቅር በለኝ ትለዋለህ?
4እንደ አንተ ያለ ሰውን ይቅር ሳትል፥
ኀጢአትህን ያስተሰርይልህ ዘንድ እንግዲህ እንዴት ትለምነዋለህ?
5ሥጋ ለባሹ ቂመኛ ከሆነ
ኀጢአቱን ማን ያስተሰርይለታል?
6ፍጻሜህን ዐስበህ ጠብን ተዋት።
ሞትንና ሙስና መቃብርን ዐስብ፤ ትእዛዙንም ጠብቅ።
7ሕጉን ዐስበህ ባልንጀራህን አትቀየም፤
የልዑልን ፍርዱን ዐስበህ ቍጣን አርቃት።
8ኀጢአቶችህን ታሳንስልህ ዘንድ ክርክርን ተዋት፤
ቍጡ ሰው ክርክርን ያነሣሣል።
9ኀጢአተኛ ሰውም ባልንጀራውን ያደክማል፤
ወዳጆቹንም ያጣላል።
10በእንጨቱ ልክ የእሳቱ ነዲድ ይበዛል፤
በክርክሩም ብዛት መጠን ጠቡ ይበዛል፤
የሰው ኀይሉ በቁመቱ መጠን ነው፤
በባለጸግነቱም ብዛት መጠን ቍጣውን ያበዛታል።
11መታበይን የሚያበዛት ሰው እሳትን ያቀጣጥላታል፤
ለጠብ የሚቸኵል ሰውም ፈጥኖ ደምን ያፈስሳል።
ክፉ ምላስ
12ፍምን እፍ ብትላት ትነድዳለች፤
ትፍ ብትልባትም ትጠፋለች፤ ሁለቱም ከአንድ አፍ ይወጣሉ።
13ሐሜተኛንና ሁለት አንደበት ያለውን ሰው ይረግሙታል፤
ብዙ ወዳጆችን አጋድሎአልና።
14ነገረ ሠሪ አንደበት ብዙ ሰዎችን አወካቸው፤
ከሕዝብም ወደ ሕዝብ አሳደዳቸው።
የጸኑ ከተሞችንም አፈረሰ፤
የመኳንንቱንም ቤት ጣለ።
15ቀባጣሪ አንደበት ደጋግ ሴቶችን ከባሎቻቸው ቤት አስወጥታ ሰደደቻቸው፤
ገንዘባቸውንም አጠፋችባቸው።
16ከእርስዋ ያልተጠበቀ ሰው ግን ለዘለዓለሙ አያርፍም፤
በሰላምም አይኖርም።
17የግርፋት ቍስል መግል ይይዛል፤
የአንደበት ቍስል ግን አጥንትን ይሰብራል።
18በጦር የወደቁ ሰዎች ብዙ ናቸው፤
ነገር ግን በአንደበት እንደ ጠፉ አይደሉም።
19ከእርሷ የዳነና በጥፋትዋ ያልተሰነካከለ፥
በቀንበሯም ያላረሰ፥ በእግር ብረትዋም ያልታሰረ ብፁዕ ነው።
20ቀንበርዋ የብረት ቀንበር ነውና፤
እግር ብረቷም የብርት ነውና።
21ሞትዋም ክፉ ሞት ነው፤
ከእርስዋም ሲኦል ትቀላለች።
22በጻድቃን ግን አትደርስባቸውም፤
በእሳቷም አይቃጠሉም።
23እግዚአብሔርን የዘነጉ ሰዎች በእርስዋ ይወድቃሉ፤
በማይጠፋ እሳትዋም ታቃጥላቸዋለች።
እንደ አንበሳም ትወረወርባቸዋለች፤
እንደ ነብርም ትይዛቸዋለች።
24ንብረትህን በእሾህ ብታጥር፥
ወርቅህንና ብርህንም ብትቈልፍ፥
25ነገርህን በሚዛን ብትመዝን፥
ለአፍህም መዝጊያና ቍልፍ ብታደርግ፥
26ዳግመኛም በአንደበትህ እንዳትሰነካከል፥
በሚያድንህም ፊት እንዳትጥልህ ተጠበቅ።