መጽ​ሐፈ ሲራክ 29

29
ስለ ማበ​ደ​ርና መበ​ደር
1ምጽ​ዋ​ትን የሚ​መ​ጸ​ውት ሰው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ለባ​ል​ን​ጀ​ራው የሚ​ያ​በ​ድር” ይላል። ያበ​ድ​ራል፤
በእ​ጁም የሚ​በቃ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እጁን የሚ​ዘ​ረጋ” ይላል። ያለው ትእ​ዛ​ዙን ይፈ​ጽ​ማል።
2በደ​ስ​ታው ጊዜ ከእ​ርሱ ጋር ደስ ይልህ ዘንድ፥
በተ​ቸ​ገረ ጊዜ ለባ​ል​ን​ጀ​ራህ አበ​ድ​ረው።
3ቃል​ህን ጠብቅ፤ ከእ​ር​ሱም ጋራ ተማ​መን፤
በጊ​ዜ​ውም የሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ግ​ህን ነገር ታገ​ኛ​ለህ።
4የብ​ድ​ርን ገን​ዘብ በም​ድር ላይ ወድቆ ያገ​ኙት የሚ​መ​ስ​ላ​ቸው ብዙ​ዎች ናቸው፤
የረ​ዷ​ቸ​ው​ንና ያበ​ደ​ሩ​አ​ቸ​ው​ንም ችግር ይፈ​ጥ​ሩ​ባ​ቸ​ዋል።
5እስ​ኪ​በ​ደ​ርህ ድረስ ራስ​ህን ይስ​ም​ሃል፤ ቃሉ​ንም ያለ​ሰ​ል​ሳል፤
ገን​ዘ​ብ​ህ​ንም እስ​ኪ​ወ​ስድ ድረስ ያባ​ብ​ል​ሃል፤
በሚ​ከ​ፍ​ል​በት ጊዜ ግን ቀጠ​ሮ​ህን ያረ​ዝ​ም​ብ​ሃል፤
በገ​ን​ዘ​ብ​ህም ጠብና ክር​ክ​ርን ይከ​ፍ​ል​ሃል፤
ያደ​ክ​ም​ሃል፤ ቀጠ​ሮ​ህ​ንም ያሳ​ል​ፋል።
6እኩ​ሌ​ታ​ውን ቢከ​ፍ​ልህ በጭ​ንቅ ነው፤
ዳግ​መ​ኛም ያንኑ በም​ድር ላይ ወድቆ ያገ​ኘ​ኸው ይመ​ስ​ል​ሃል፤
ይህስ ካል​ሆነ ገን​ዘ​ብ​ህን ሁሉ ታጣ​ለህ፤
ዳግ​መ​ኛም ጠላት ይሆ​ን​ሃል፤ ርግ​ማ​ን​ንና ስድ​ብን ይከ​ፍ​ል​ሃል፤
ከሚ​ያ​ከ​ብ​ር​ህም ይልቅ ያዋ​ር​ድ​ሃል።
7ገን​ዘ​ባ​ቸ​ውን እን​ዳ​ያ​ጡና እን​ዳ​ይ​ጣሉ በመ​ፍ​ራ​ትና ጠብን ባለ​መ​ው​ደድ ገን​ዘ​ባ​ቸ​ውን የማ​ያ​በ​ድሩ ሰዎች ብዙ ናቸው።
ስለ ምጽ​ዋት
8ድሃ​ዉን ግን ታገ​ሠው፤
ምጽ​ዋ​ቱ​ንም ስጠው፤ አል​ፈ​ኸ​ውም አት​ሂድ።
9ችግ​ረኛ ነውና በሕግ እንደ ታዘ​ዘው ድኃ​ዉን በም​ጽ​ዋት ተቀ​በ​ለው፤
ባዶ​ው​ንም አት​መ​ል​ሰው።
10ባል​ን​ጀ​ራ​ህ​ንና ወዳ​ጅ​ህን ከም​ታጣ፥
ተቀ​ብሮ ከሚ​ዝ​ግና በድ​ን​ጋ​ይም ሥር ከሚ​ጠፋ ወር​ቅ​ህን እጣ።
11ስለ ልዑል ትእ​ዛዝ በወ​ር​ቅህ አስ​ተ​ዋ​ፅኦ አድ​ርግ፤
ከወ​ርቅ ድልብ የበ​ለ​ጠም ያተ​ር​ፍ​ል​ሃል።
12ምጽ​ዋ​ትን በቤ​ቶ​ችህ አድ​ል​ባት፤ እር​ስ​ዋም ትሻ​ላ​ለች፤#“እር​ስ​ዋም ትሻ​ላ​ለች” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም።
ከመ​ከ​ራ​ህም ሁሉ አን​ተን ማዳን ትች​ላ​ለች።
ስለ ዋስ​ትና
13ከጦ​ርና ጋሻ ትሻ​ላ​ለች፤
ጠላ​ት​ህን ድል ትነ​ሣ​ል​ሃ​ለች፤ ታጠ​ፋ​ል​ሃ​ለ​ችም።
14ደግ ሰው ጎረ​ቤ​ቱን ይዋ​ሰ​ዋል፤
የማ​ያ​ፍር ሰው ግን ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ቸል ይላል።
15ስለ አንተ ፋንታ ሰው​ነ​ቱን አሳ​ልፎ ሰጥ​ት​ዋ​ልና
የተ​ዋ​ሰ​ህን ሰው ውለታ አት​ርሳ።
16ጠብን ለማ​ጥ​ፋት መዋስ ደግ ነገር ነው።
17ኀጢ​አ​ተኛ ሰው ግን ያዳ​ነ​ውን ሰው ውለታ ይዘ​ነ​ጋል።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ኀጢ​አ​ተኛ ሰው በዋ​ስ​ትና ምክ​ን​ያት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛ​ዛት ያፈ​ር​ሳል ትር​ፍ​ንም ለመ​ፈ​ለግ በሚ​ያ​ደ​ር​ገው ጥረት በፍ​ርድ ላይ ይወ​ድ​ቃል” ይላል።
18መዋስ ብዙ ደጋግ ሰዎ​ችን አሳ​ዘነ፤
እንደ ባሕር ማዕ​በ​ልም አወ​ካ​ቸው፤
አር​በ​ኞች ሰዎ​ች​ንም አሳ​ታ​ቸው፤
ወደ ባዕድ ሕዝ​ብም አሳ​ደ​ዳ​ቸው።
19ኀጢ​አ​ተኛ ሰው ግን በመ​ዋስ ይጠ​ፋል፤
ለት​ር​ፍም የሚ​ሳሳ ሰው በመ​ከራ ይወ​ድ​ቃል።
20በተ​ቻ​ለህ መጠን ባል​ን​ጀ​ራ​ህን ርዳው፤
ነገር ግን እን​ዳ​ያ​ስ​ትህ ራስ​ህን ጠብቅ።
21የሕ​ይ​ወ​ትህ መጀ​መ​ሪያ እህ​ልና ውኃ፥ ልብ​ስም ነው፤
ቤትህ ግን ኀፍ​ረ​ት​ህን የም​ት​ሰ​ው​ር​በት ነው።
22በሌላ ሰው ገን​ዘብ በባ​ዕድ ቤት ፈጽ​መህ ደስ ከሚ​ልህ፥
በራ​ስህ ጎጆ ብት​ቸ​ገር ይሻ​ል​ሃል።
23ለታ​ና​ሹም ለታ​ላ​ቁም ሥራ​ህ​ንና ቃል​ህን አሳ​ምር።
24ካንዱ ቤት ወደ ሌላው ቤት የሚ​ዞር ሰው ኑሮው ክፉ ነው፤
ባደ​ር​ህ​በት ቦታ ክፉ ነገር እን​ዳ​ት​ና​ገር ተጠ​ን​ቀቅ።
25ያም ባይ​ሆን ታበ​ላ​ለህ፤ ታጠ​ጣ​ለ​ህም፤
ምስ​ጋና ግን አይ​ኖ​ር​ህም፥ ከዚ​ህም ሁሉ ጋር መራራ ነገ​ርን ይመ​ል​ሱ​ል​ሃል።
26በተ​ዘ​ጋ​ጀህ ጊዜ ግን እን​ዲህ ይሉ​ሃል፥ “እን​ግ​ዳ​ችን ገብ​ተህ ማዕ​ድን ሥራ፤ ያለ​ህ​ንም አብ​ላን።”
27ብት​ቸ​ገር ግን፥ “እን​ግ​ዳ​ችን ውጣ፤
አማ​ቻ​ችን ደረሰ፤ ቤታ​ች​ንን እን​ፈ​ል​ገ​ዋ​ለን” ይሉ​ሃል።
28ይህ ነገር በብ​ልህ ሰው ዘንድ ጭንቅ ነው፤
ያሳ​ደ​ር​ኸው ሰው ያዋ​ር​ድ​ሃል፤ ያበ​ደ​ር​ኸ​ውም ሰው ይሰ​ድ​ብ​ሃል።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ