መጽ​ሐፈ ሲራክ 25

25
1በእ​ነ​ዚህ በሦ​ስቱ ነገ​ሮች ያማ​ርሁ ሆንሁ፤
በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በሰው ፊትም ያማ​ርሁ ሆኜ ቆምሁ፥
እነ​ዚ​ህም በአ​ንድ ልብ የሚ​ተ​ባ​በሩ ወን​ድ​ማ​ማ​ቾች፥
የባ​ል​ን​ጀ​ሮች ፍቅር፥ የባ​ልና ሚስ​ትም ስም​ም​ነት ናቸው።
2ሦስት ዐይ​ነት ሰዎ​ችን ሰው​ነቴ ፈጽማ ጠላ​ቻ​ቸው፤
ኑሯ​ቸ​ውም እጅግ አበ​ሳ​ጨኝ፤
እነ​ዚ​ህም ትዕ​ቢ​ተኛ ድሃ፥
ንፉግ ባለ​ጸ​ጋና አእ​ምሮ የሌ​ለው ሴሰኛ ሽማ​ግሌ ናቸው።
3ከሕ​ፃ​ን​ነ​ትህ ጀም​ረህ ያል​ተ​መ​ከ​ርህ፥
በእ​ር​ጅ​ናህ ጊዜ እን​ዴት ብልህ ትሆ​ና​ለህ?
4ሺበት ፍርድ ሊሰጥ ይገ​ባ​ዋል፤
ሽማ​ግ​ሎ​ችም መም​ከር ይገ​ባ​ቸ​ዋል።
5ለሽ​ማ​ግ​ሎ​ችም ጥበብ ይገ​ባ​ቸ​ዋል፤
ለታ​ላ​ላቅ ሰዎ​ችም ጥበ​ብን መማር ይገ​ባ​ቸ​ዋል።
6የት​ም​ህ​ርት ብዛት የሽ​ማ​ግ​ሎች ዘው​ዳ​ቸው ነው፤
መመ​ኪ​ያ​ቸ​ውም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ነው።
7በልቤ ያደ​ነ​ቅ​ኋ​ቸው ዘጠኝ ናቸው፤
ዐሥ​ረ​ኛ​ውን ግን በቃሌ እና​ገ​ራ​ለሁ፤
እነ​ር​ሱም በል​ጆቹ ደስ የሚ​ለው ሰው፥
በሕ​ይ​ወ​ቱም ሳለ የጠ​ላ​ቱን ውድ​ቀት የሚ​ያይ ሰው ናቸው።
8ልባም ሴትን ያገባ ብፁዕ ነው፤
በአ​ን​ደ​በ​ቱም ያል​ሳተ ሰው ብፁዕ ነው፤
ከእ​ርሱ ላነሰ ሰው ያላ​ደረ ብፁዕ ነው፤
9ዕው​ቀ​ትና ጥበ​ብን ያገ​ኛት ሰው፥
የሚ​ታ​ዘ​ዝ​ለ​ት​ንም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ለሚ​ሰ​ሙት ጆሮ​ዎች የሚ​ና​ገር ብፁዕ ነው” ይላል። ያገኘ ሰው ብፁዕ ነው።
10ጥበ​ብን ያገኘ ሰው እን​ዴት ታላቅ ነው!
ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ይህን ይበ​ል​ጠ​ዋል።
11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ከሁሉ ትበ​ል​ጣ​ለች።
12እር​ሷ​ንም የጠ​በቀ ሰውን የሚ​መ​ስ​ለው የለም።#ምዕ. 25 ቍ. 11 እና 12 በግ​ሪኩ ቍ. 11 ነው የግ​ሪ​ኩም ቍ. 12 “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የመ​ው​ደድ መጀ​መ​ሪያ ነው ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ማመን ለእ​ርሱ ታማኝ መሆን ነው” ይላል።
13ከቍ​ስል ሁሉ ይልቅ የልብ ቍስል ይከ​ፋል፤
ከክ​ፋ​ትም ሁሉ የሴት ክፋት ትከ​ፋ​ለች።
14በሁ​ሉም ብት​ወ​ድቅ በጠ​ላ​ትህ እጅ አት​ው​ደቅ፤
ሁሉ ቢበ​ቀ​ልህ ጠላ​ትህ አይ​በ​ቀ​ልህ።
15ከእ​ባብ ራስ የሚ​ከፋ ራስ የለም፤
ከጠ​ላ​ትም ቂም የሚ​ከፋ ቂም የለም።
የክፉ ሴት ተግ​ባር
16ከክፉ ሴት ጋራ ከም​ት​ኖር፥
ከአ​ን​በ​ሶ​ችና ከም​ድር አው​ሬ​ዎች ጋር መኖር ይሻ​ላል።
17ክፋ​ትዋ መል​ኳን ይለ​ው​ጠ​ዋል፤
ፊት​ዋ​ንም እንደ ድብ መልክ#ግሪኩ “እንደ ማቅ” ይላል። ያጠ​ቍ​ረ​ዋል።
18ባሏ​ንም በባ​ል​ን​ጀ​ሮቹ መካ​ከል ይን​ቁ​ታል፤
መራራ ኀዘ​ን​ንም ያሳ​ዝ​ኑ​ታል፤
አስ​ጨ​ን​ቀ​ውም ይይ​ዙ​ታል።
19ክፋት ሁሉ ከሴት ክፋት ታን​ሳ​ለች፤
እር​ስ​ዋም ወደ ኀጢ​አት ዕድል ታደ​ር​ሳ​ለች።
20የአ​ሸዋ ዐቀ​በት የሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ችን እግ​ራ​ቸ​ውን እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ክም፥
እን​ዲሁ ቀባ​ጣሪ ሴት የዋህ ባልን ታደ​ክ​መ​ዋ​ለች።
21የሴት መልኳ አያ​ስ​ትህ፤ ሀብ​ቷም አያ​ስ​ጐ​ም​ጅህ።
መቅ​ሠ​ፍ​ትና ጥፋት ጽኑ ውር​ደ​ትም ናትና፤
22ሴት ባሏን ብት​መ​ግ​በው፥
ቍጣን፥ አለ​ማ​ክ​በ​ር​ንና ብዙ ዘለ​ፋን የተ​ሞ​ላች ትሆ​ና​ለች።
23ለልብ ቍስል ናት፥ ለፊ​ትም ጥቁ​ረት ናት፥ ለነ​ፍ​ስም ኀዘን ናት፤
እን​ዲሁ ባሏን የማ​ታ​ከ​ብር ሴት
እንደ ሽባ እጅና ልምሾ እንደ ሆነ እግር ናት።
24በመ​ጀ​መ​ሪ​ያም ኀጢ​አት ከሴት ተገ​ኘች፤
በእ​ር​ስ​ዋም ምክ​ን​ያት ሁላ​ችን እን​ሞ​ታ​ለን።
25ለውኃ መፍ​ሰሻ አታ​ብ​ጅ​ለት
ለሴ​ትም#ግሪኩ “ለክፉ ሴት” ይላል። የል​ብ​ህን ምሥ​ጢር አታ​ው​ጣ​ላት።
26እንደ ጠባ​ይህ ካል​ሆ​ነች ፍታት፤
ከሰ​ው​ነ​ት​ህም ለያት።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ