መጽ​ሐፈ ሲራክ 24

24
የጥ​በብ ክብር
1ጥበብ ራስ​ዋን ታመ​ሰ​ግ​ና​ለች፤
በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል ትመ​ካ​ለች።
2በል​ዑ​ልም ጉባኤ ትና​ገ​ራ​ለች፤
በኀ​ይ​ሉም ፊት ትመ​ካ​ለች።
3እን​ዲ​ህም አለች፦ እኔ ከል​ዑል አፍ ወጣሁ፤
ምድ​ር​ንም እንደ ጉም ሸፈ​ን​ኋት።
4እኔ በሰ​ማይ ኖርሁ፤
ዙፋ​ኔ​ንም በደ​መና ዐምድ ላይ ዘረ​ጋሁ።
5ብቻ​ዬ​ንም በሰ​ማይ ዳርቻ ዞርሁ፤
በው​ቅ​ያ​ኖስ መካ​ከ​ልም ተመ​ላ​ለ​ስሁ፤
6በባ​ሕ​ርም ማዕ​በል ላይ በየ​ብ​ስም መካ​ከል ሁሉ፥
በሕ​ዝ​ቡና በአ​ሕ​ዛቡ ሁሉ ጥሪ​ትን አደ​ረ​ግሁ።#አን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ “ኢያ​ጥ​ረ​ይኩ” ይላል።
7ከዚ​ህም ሁሉ በኋላ ዕረ​ፍ​ትን ፈለ​ግሁ፤
እን​ግ​ዲህ በማን ርስት አድ​ራ​ለሁ?
8ከዚ​ህም በኋላ ሁሉን የፈ​ጠረ አዘ​ዘኝ፤
ፈጣ​ሪም ማደ​ሪ​ያ​ዬን አዘ​ጋ​ጀ​ልኝ፤ እን​ዲ​ህም አለኝ፦
“በያ​ዕ​ቆብ እደሪ፤ ርስ​ት​ሽም በእ​ስ​ራ​ኤል ይሁን።”
9ዓለም ሳይ​ፈ​ጠር ወለ​ደኝ፥
ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙም ከእ​ርሱ አል​ለ​ይም።
10በተ​ቀ​ደሰ ማደ​ሪ​ያ​ውም በፊቱ አገ​ለ​ገ​ልሁ፤
በጽ​ዮ​ንም አደ​ርሁ።
11እን​ዲ​ሁም በተ​ወ​ደ​ደ​ችው ከተማ ዐረ​ፍሁ፤
ግዛ​ቴም ባስ​ገ​ዛኝ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነበር።
12በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት ዕድል ፋንታ፥
በከ​በረ ሕዝብ መካ​ከል ሥር ሰደ​ድሁ።
13በሊ​ባ​ኖስ እን​ዳለ ዝግባ ከፍ ከፍ አልሁ፤
በኤ​ር​ሞን ተራራ እን​ዳለ ዋን​ዛም ገነ​ንሁ።
14በውኃ ዳር እን​ዳለ ዘን​ባ​ባም ረዘ​ምሁ፤
በኢ​ያ​ሪኮ እን​ዳለ ጽጌ​ረዳ፥
በም​ድረ በዳ እን​ዳ​ለች እን​ዳ​ማ​ረች የዘ​ይት እን​ጨ​ትም መዓ​ዛዬ የተ​ወ​ደደ ሆነ፤
እንደ ዋርካ ዛፍም ገነ​ንሁ።
15መዓ​ዛ​ዬም እንደ ቀና​ን​ሞ​ስና እንደ ደር​ሶኒ ሽቱ የተ​ወ​ደደ ሆነ፤
መዓ​ዛ​ዬም እን​ዳ​ማረ የሽቱ መዓዛ ሆነ፤
እንደ ልባ​ን​ጃና እንደ ጥርኝ፥ ሰጡ​ቃጤ እን​ደ​ሚ​ባል ሽቱም፥
በደ​ብ​ተራ ኦሪት እን​ዳለ እንደ ነጭ ዕጣን መዓ​ዛም የተ​ወ​ደደ ሆነ።
16ቅር​ን​ጫ​ፎች እንደ ቡጥም ረዘሙ፤
ቅር​ን​ጫ​ፎ​ችም የክ​ብ​ርና የጌ​ት​ነት ቅር​ን​ጫ​ፎች ናቸው።
17እኔስ እንደ ተወ​ደደ የወ​ይን ሐረግ መወ​ደ​ድን አስ​ገ​ኘሁ።
18አበ​ባ​ዬም የክ​ብ​ርና የባ​ለ​ጸ​ግ​ነት ፍሬ ነው።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እኔ የፍ​ቅ​ርና የፍ​ር​ሀት የዕ​ው​ቀ​ትና የቅ​ዱስ ተስፋ እናት ነኝ ፤ ስለ​ዚ​ህም በስሙ ለተ​ጠሩ ልጆች ሁሉ ዘለ​ዓ​ለ​ማ​ዊት ሆኜ ተሰ​ጥ​ቻ​ለሁ” ይላል።
19የም​ት​ወ​ዱኝ ሰዎች ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤
ከፍ​ሬ​ዬም ትጠ​ግ​ባ​ላ​ችሁ።
20ስም አጠ​ራሬ ከማር፥
ርስ​ት​ነ​ቴም ከሸ​ን​ኮር ይልቅ ይጣ​ፍ​ጣ​ልና።
21የሚ​መ​ገ​ቡ​ኝም አይ​ጠ​ግ​ቡ​ኝም፤
የሚ​ጠ​ጡ​ኝም አይ​ሰ​ለ​ቹ​ኝም።
22የሚ​ሰ​ማ​ኝም አያ​ፍ​ርም፤
ለእኔ የሚ​ገዙ ሰዎች አይ​ስ​ቱም።
23ይህ ሁሉ ነገር የል​ዑል የሕጉ መጽ​ሐፍ ነው፤
ስለ ያዕ​ቆ​ብም ወገ​ኖች ርስት ሙሴ ያዘ​ዘ​በት ሕግ ነው።
24በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ጸና አይ​ደ​ክ​ምም፤
እርሱ ያጸ​ና​ችሁ ዘንድ ተከ​ተ​ሉት፤
ሁሉን የሚ​ችል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ ነው፤
ከእ​ር​ሱም በቀር ሌላ አዳኝ የለም።
25ጥበ​ብን እንደ ኤፌ​ሶን ፈሳሽ፥
በሚ​ያ​ዝ​ያም ወራት እን​ደ​ሚ​መላ እንደ ጤግ​ሮስ ፈሳሽ የሚ​መ​ላት እርሱ ነው።
26ምክ​ር​ንም እንደ ኤፍ​ራ​ጥስ ፈሳሽ፥
ባዝ​መ​ራም ወራት እንደ ዮር​ዳ​ኖስ ፈሳሽ የሚ​መ​ላት እርሱ ነው።
27ጥበ​ብን እንደ ብር​ሃን፥
በወ​ይን አዝ​መራ ወራ​ትም እንደ አባይ ፈሳሽ የሚ​ገ​ል​ጣት እርሱ ነው።
28የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው አላ​ወ​ቃ​ትም፤
የመ​ጨ​ረ​ሻ​ውም ፍለ​ጋ​ዋን አላ​ገ​ኘም።
29ምሥ​ጢሯ ከባ​ሕር ውኃ ይልቅ ይበ​ዛል፤
ምክ​ሯም ከባ​ሕሩ ጥል​ቀት ይልቅ ይጠ​ል​ቃል።
30ከወ​ንዝ እን​ደ​ሚ​ፈ​ስስ ውኃ ሆንሁ፤
እንደ መስኖ ውኃም ወደ ተክል ቦታ ገባሁ፤
31እን​ዲ​ህም አልሁ፥ “የተ​ክል ቦታ​ዬን ላጠ​ጣት፤ የጎ​መን ቦታ​ዬን ላጠ​ጣት፤”
ፈፋዬ እንደ ወንዝ ሆነ​ልኝ፤ ወን​ዜም እንደ ባሕር ሆነ​ልኝ።
32ዳግ​መ​ኛም ጥበ​ብን እንደ ጥዋት አበ​ራ​ታ​ለሁ፤
እስከ ሩቅም ድረስ ብር​ሃ​ን​ዋን አሳ​ያ​ለሁ።
33ትም​ህ​ር​ትን እንደ ትን​ቢት አፈ​ስ​ሳ​ታ​ለሁ፤
ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ለልጅ ልጅ አጸ​ና​ታ​ለሁ።
34እነሆ፥ የደ​ከ​ምሁ ለሚ​ፈ​ል​ጉኝ ሰዎች ሁሉ ነው እንጂ፥
ለእኔ ብቻ እን​ዳ​ይ​ደለ እዩ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ