መጽ​ሐፈ ሲራክ 17

17
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰውን ከም​ድር ፈጠ​ረው፥
ዳግ​መ​ኛም ወደ ምድር ይመ​ል​ሰ​ዋል።
2ዓመ​ታ​ት​ንና ቀና​ትን በቍ​ጥር ሰጣ​ቸው፤
በው​ስ​ጧም ያለ​ውን ሁሉ አስ​ገ​ዛ​ቸው።
3ለእ​የ​ራ​ሳ​ቸው ኀይ​ልን አሳ​ደ​ረ​ባ​ቸው፤
በም​ሳ​ሌ​ውም ፈጠ​ራ​ቸው።
4ፍጥ​ረቱ ሁሉ እን​ዲ​ፈ​ሩ​አ​ቸው አደ​ረገ።
5አው​ሬ​ዎ​ች​ንና ወፎ​ች​ንም እን​ዲ​ገ​ዟ​ቸው አደ​ረገ።
6ቃል​ንና አን​ደ​በ​ትን፥ ዐይ​ንና ጆሮን፥
የሚ​ያ​ስ​ቡ​በት ልቡ​ና​ንም ሰጣ​ቸው።
7ጥበ​ብን ማወ​ቅ​ንም አጠ​ገ​ባ​ቸው፤
ክፉ​ንና በጎ​ንም አሳ​ያ​ቸው።
8የሥ​ራ​ውን ገና​ና​ነ​ትና መፈ​ራ​ቱ​ንም ያሳ​ያ​ቸው ዘንድ፥
በል​ቡ​ና​ቸው ፍር​ሀ​ትን አሳ​ደ​ረ​ባ​ቸው።
9ቅዱስ ስሙን ያመ​ሰ​ግ​ኑት ዘንድ።
10የሥ​ራ​ው​ንም ገና​ና​ነት ይና​ገሩ ዘንድ፥
11ጥበ​ብን ሰጣ​ቸው፤
የሚ​ያ​ድ​ና​ቸው ሕጉ​ንም አወ​ረ​ሳ​ቸው።
12የዘ​ለ​ዓ​ለም መሐ​ላ​ንም ተማ​ማ​ላ​ቸው፤
ፍር​ዱ​ንም ነገ​ራ​ቸው።
13ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም የጌ​ት​ነ​ቱን ገና​ና​ነት አዩ።
14የጌ​ት​ነ​ቱ​ንም ቃል ጆሮ​ቻ​ቸው ሰሙ፥
15ከኀ​ጢ​አት ሁሉ ተጠ​በቁ አላ​ቸው፤
ሁሉ​ንም ባል​ጀ​ራ​ች​ሁን ውደዱ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው።
16መን​ገ​ዳ​ቸ​ውም ሁል​ጊዜ በፊቱ ነው፥
ከዐ​ይ​ኖ​ቹም የሚ​ሰ​ወ​ሩ​በት የላ​ቸ​ውም።
17ለአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ነገ​ሥ​ታ​ትን አነ​ገ​ሠ​ላ​ቸው።
18እስ​ራ​ኤል ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክፍል ሆነ።
19ሥራ​ቸ​ውም ሁሉ በፊቱ እንደ ፀሐይ ነው፤
ዐይ​ኖ​ቹም ሁል​ጊዜ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን ያያሉ።
20ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ከእ​ርሱ አል​ተ​ሰ​ወ​ረ​ችም፤
በደ​ላ​ቸ​ውም ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ነው።
21የሰው ምጽ​ዋቱ ከእ​ርሱ ጋራ እንደ ማኅ​ተም ነው።
22የሰው ዋጋው እንደ ዐይን ብሌን ትጠ​በ​ቅ​ለ​ታ​ለች።
23ኋላ ተመ​ልሶ ዋጋ​ቸ​ውን ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል፤
የኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ፍዳ ወደ ራሳ​ቸው ይመ​ል​ሳል።
24ነገር ግን ንስሓ የሚ​ገ​ቡ​በ​ትን መን​ገድ ሰጣ​ቸው፤
ተስፋ የቈ​ረጡ ሰዎ​ች​ንም ደስ ያሰ​ኛ​ቸ​ዋል።
የን​ስሓ ጥሪ
25ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተመ​ለስ፥
ኀጢ​አ​ት​ንም ተዋት በፊ​ቱም ጸልይ፥
ለበ​ደ​ል​ህም ንስሓ ግባ፤
26ከበ​ደ​ል​ህም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተመ​ለስ፤
ኀጢ​አ​ትን ሁሉ ጥላ ፈቃ​ዱ​ንም አድ​ርግ።#“ፈቃ​ዱ​ንም አድ​ርግ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም።
27በሕ​ይ​ወት ሳሉ እን​ደ​ሚ​ገ​ዙ​ለት ሰዎች፥
ልዑ​ልን በመ​ቃ​ብር የሚ​ያ​መ​ሰ​ግ​ነው ማን​ነው?
28የሞተ ሰውን ግን ንስሓ እንደ ኢም​ንት አለ​ፈው፤
በሕ​ይ​ወ​ትህ ደስ እያ​ለህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ነው።
29የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር​ነቱ ታላቅ ነውና፤
የሚ​ገ​ዙ​ለ​ትን ሰዎች ይቅር ይላ​ቸ​ዋል።
30ሰው ሟች ስለ ሆነ፥
ሁሉ በሰው ዘንድ ሊሆን አይ​ች​ልም።
31ከፀ​ሐይ የሚ​በራ ምን አለ? እር​ሱም እንኳ ያል​ፋል።
ደማ​ዊና ሥጋ​ዊም ክፉ ነገ​ርን ያስ​ባል።
32እርሱ የሰ​ማ​ይን ምጥ​ቀት ኀይል ያው​ቃል፥
ሰው ሁሉ ግን አመ​ድና ትቢያ ነው።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ