መጽሐፈ ሲራክ 16
16
1ጥቅም የሌላቸው ብዙ ልጆችን አትመኝ፤
በክፉዎች ልጆችም ደስ አይበልህ።
2በእነርሱ እግዚአብሔርን መፍራት ከሌለባቸው፥
ቢበዙም በእነርሱ ደስ አይበልህ።
3በሕይወታቸውም አትተማመንባቸው፥
ብዛታቸውም ደስ አያሰኝህ።
ከሺህ አንድ ደግ ይሻላል፥
ክፉን ከመውለድም ሳይወልዱ መሞት ይሻላል።
4በአንድ ዐዋቂ ሀገር ትጸናለችና፥
በኀጢአተኞች ብዛት ግን ትጠፋለች።
5ዐይኔ እንዲህ ያለ ብዙ ነገርን አየች።
ጆሮዬም ከዚህ የሚበልጥ ሰማች።
6በኀጢአተኞች ወገኖች እሳት ትነድዳለች፤
በወንጀለኞች ሕዝብ ላይም ጥፋት ትነድዳለች።
7በኀይላቸው የታመኑ የቀደሙ አርበኞችም
ራሳቸውን አላዳኑም።
8ሎጥ ለኖረባቸው፥ ራሳቸውንም ላኮሩ፥
ሎጥንም ለተጸየፉት ሀገሮች አልራራላቸውም።
9ኀጢአተኞች ሕዝቦችን ይቅር አላላቸውም፤
በኀጢአታቸው ጠፉ እንጂ።
10እነዚህም የተሰበሰቡ፥ ልቡናቸውንም ያከፉ፥
ስድስት መቶ ሺህ እግረኞች ነበሩ።
11ክሣደ ልቡናውን ያጸና አንድ ሰው ቢኖር
እርሱ ቢድን ድንቅ ነው፥
ይቅርታም መቅሠፍትም ከእርሱ ዘንድ ነውና ይቅር ማለት ይችላል፤
መቅሠፍትንም ማምጣት ይችላል።
12ቍጣው እንደ ቸርነቱ ብዛት መጠን ነው፥
ለሰውም እንደ ሥራው ይከፍለዋል።
13ኀጢአተኛ ሰው ከዳፋ አያመልጥም፤
ጻድቅ ሰውም የትዕግሥቱን ዋጋ አያጣም።
14ምጽዋት ሁሉ ይቅርታን ያመጣል፤
ሰውም ሁሉ እንደ ሥራው ያገኛል።
15“ከእግዚአብሔር አመልጣለሁ፤
በሰማያትም የሚያገኘኝ የለም።
16በብዙ አሕዛብም ዘንድ የሚያውቀኝ የለም።
17የሰውነቴስ ቍጥሯ በዓለም ሁሉ ምንድን ነው?” አትበል።
18እነሆ፥ ሰማይ፥ ከሰማያትም በላይ ያለ ሰማይ፥
ከሰማይም በታች ያለ ውቅያኖስ፥ ምድርም፥
በመዓት በጐበኛቸው ጊዜ ይህ ሁሉ ይነዋወጣል።
19ተራሮችም፥ የምድርም መሠረቶች፥
በመዓት ባያቸው ጊዜ ይንቀጠቀጣሉ ይነዋወጣሉም።
20ይህንም ልብ አያስበውም፤
መንገዶቹንስ ማወቅ ማን ይችላል?
ገናናነቱንስ ጠብቆ መናገር ማን ይችላል?#በግሪክ ሰባ. ሊ. “ገናናነቱንስ ጠንቅቆ መናገር ማን ይችላል” የሚል የለም።
21ከሥራውም አብዛኛው ስውር ነው፥
ሰው የማያየው ዐውሎ ነፋስ ነውና።
22እውነት ሥራ መሥራትን ማን ያስተምራል?
የምሕረቱንስ ተስፋ ማን ደጅ ይጠናል?
23አእምሮ የሌለው ሰው እንዲህ ያስባል፤
ሰነፍና በደለኛ ሰውም ስንፍናን ያስባል።
የእግዚአብሔር ጥበብ በሥነ ፍጥረት
24ልጄ ሆይ፥ ስማኝ፥ ጥበብንም ተማር፥
ነገሬንም ከልቡናህ አድምጠው።
25በሚዛን መዝነህ ጥበብህን ግለጣት፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እገልጣለሁ” ይላል።
የትምህርትህንም ነገሯን ተረዳ።
26የእግዚአብሔር ሥራ ከጥንት ጀምሮ በሥልጣኑ ተፈጠረ።
ሥርዐታቸውንም በየወገናቸው ለየ።
27ዓለም ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖር ዘንድ ሥራውን ሁሉ አዘጋጀ፥
ሠራዊታቸውንም በየወገናቸው አዘጋጀ፥
አይሠሩም፥ አይጠሙም፥ አይራቡምም፥ ሥራቸውም አይቋረጥም፤
28አንዱ ከሌላው ጋር አይጨናነቅም፤
ለዘለዓለሙም ከቃሉ አይወጡም።
29ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ምድርን ተመለከተ፤
ከበረከቱም አጠገባት።
30በደማዊት ነፍስ ሕያው የሆነ ፍጥረት ሁሉ በምድር መላ፤
መመለሻቸውም ወደ ምድር ነው።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 16: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፈ ሲራክ 16
16
1ጥቅም የሌላቸው ብዙ ልጆችን አትመኝ፤
በክፉዎች ልጆችም ደስ አይበልህ።
2በእነርሱ እግዚአብሔርን መፍራት ከሌለባቸው፥
ቢበዙም በእነርሱ ደስ አይበልህ።
3በሕይወታቸውም አትተማመንባቸው፥
ብዛታቸውም ደስ አያሰኝህ።
ከሺህ አንድ ደግ ይሻላል፥
ክፉን ከመውለድም ሳይወልዱ መሞት ይሻላል።
4በአንድ ዐዋቂ ሀገር ትጸናለችና፥
በኀጢአተኞች ብዛት ግን ትጠፋለች።
5ዐይኔ እንዲህ ያለ ብዙ ነገርን አየች።
ጆሮዬም ከዚህ የሚበልጥ ሰማች።
6በኀጢአተኞች ወገኖች እሳት ትነድዳለች፤
በወንጀለኞች ሕዝብ ላይም ጥፋት ትነድዳለች።
7በኀይላቸው የታመኑ የቀደሙ አርበኞችም
ራሳቸውን አላዳኑም።
8ሎጥ ለኖረባቸው፥ ራሳቸውንም ላኮሩ፥
ሎጥንም ለተጸየፉት ሀገሮች አልራራላቸውም።
9ኀጢአተኞች ሕዝቦችን ይቅር አላላቸውም፤
በኀጢአታቸው ጠፉ እንጂ።
10እነዚህም የተሰበሰቡ፥ ልቡናቸውንም ያከፉ፥
ስድስት መቶ ሺህ እግረኞች ነበሩ።
11ክሣደ ልቡናውን ያጸና አንድ ሰው ቢኖር
እርሱ ቢድን ድንቅ ነው፥
ይቅርታም መቅሠፍትም ከእርሱ ዘንድ ነውና ይቅር ማለት ይችላል፤
መቅሠፍትንም ማምጣት ይችላል።
12ቍጣው እንደ ቸርነቱ ብዛት መጠን ነው፥
ለሰውም እንደ ሥራው ይከፍለዋል።
13ኀጢአተኛ ሰው ከዳፋ አያመልጥም፤
ጻድቅ ሰውም የትዕግሥቱን ዋጋ አያጣም።
14ምጽዋት ሁሉ ይቅርታን ያመጣል፤
ሰውም ሁሉ እንደ ሥራው ያገኛል።
15“ከእግዚአብሔር አመልጣለሁ፤
በሰማያትም የሚያገኘኝ የለም።
16በብዙ አሕዛብም ዘንድ የሚያውቀኝ የለም።
17የሰውነቴስ ቍጥሯ በዓለም ሁሉ ምንድን ነው?” አትበል።
18እነሆ፥ ሰማይ፥ ከሰማያትም በላይ ያለ ሰማይ፥
ከሰማይም በታች ያለ ውቅያኖስ፥ ምድርም፥
በመዓት በጐበኛቸው ጊዜ ይህ ሁሉ ይነዋወጣል።
19ተራሮችም፥ የምድርም መሠረቶች፥
በመዓት ባያቸው ጊዜ ይንቀጠቀጣሉ ይነዋወጣሉም።
20ይህንም ልብ አያስበውም፤
መንገዶቹንስ ማወቅ ማን ይችላል?
ገናናነቱንስ ጠብቆ መናገር ማን ይችላል?#በግሪክ ሰባ. ሊ. “ገናናነቱንስ ጠንቅቆ መናገር ማን ይችላል” የሚል የለም።
21ከሥራውም አብዛኛው ስውር ነው፥
ሰው የማያየው ዐውሎ ነፋስ ነውና።
22እውነት ሥራ መሥራትን ማን ያስተምራል?
የምሕረቱንስ ተስፋ ማን ደጅ ይጠናል?
23አእምሮ የሌለው ሰው እንዲህ ያስባል፤
ሰነፍና በደለኛ ሰውም ስንፍናን ያስባል።
የእግዚአብሔር ጥበብ በሥነ ፍጥረት
24ልጄ ሆይ፥ ስማኝ፥ ጥበብንም ተማር፥
ነገሬንም ከልቡናህ አድምጠው።
25በሚዛን መዝነህ ጥበብህን ግለጣት፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እገልጣለሁ” ይላል።
የትምህርትህንም ነገሯን ተረዳ።
26የእግዚአብሔር ሥራ ከጥንት ጀምሮ በሥልጣኑ ተፈጠረ።
ሥርዐታቸውንም በየወገናቸው ለየ።
27ዓለም ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖር ዘንድ ሥራውን ሁሉ አዘጋጀ፥
ሠራዊታቸውንም በየወገናቸው አዘጋጀ፥
አይሠሩም፥ አይጠሙም፥ አይራቡምም፥ ሥራቸውም አይቋረጥም፤
28አንዱ ከሌላው ጋር አይጨናነቅም፤
ለዘለዓለሙም ከቃሉ አይወጡም።
29ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ምድርን ተመለከተ፤
ከበረከቱም አጠገባት።
30በደማዊት ነፍስ ሕያው የሆነ ፍጥረት ሁሉ በምድር መላ፤
መመለሻቸውም ወደ ምድር ነው።