መጽ​ሐፈ ሲራክ 18

18
1ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕያው የሆነ እርሱ ሁሉን በአ​ን​ድ​ነት ፈጠረ።
2እው​ነ​ተኛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ ነው።
3ሥራ​ውን ያውቅ ዘንድ ማን​ንም አላ​ሰ​ና​በ​ተ​ውም፤
የገ​ና​ና​ነ​ቱ​ንስ ፍለጋ ማን መር​ምሮ ያው​ቃል?
4ከሀ​ሊ​ነ​ቱ​ንስ ማን መር​ምሮ ያው​ቃል?
ቸር​ነ​ቱ​ንስ ማን ጠን​ቅቆ ይና​ገ​ራል?
5መጨ​መ​ርም የለም፤ መቀ​ነ​ስም የለም፤
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የጌ​ት​ነ​ቱን ፍለጋ የሚ​ያ​ገኝ የለም።
6ሰውን በፈ​ጠ​ረው ጊዜ ያን​ጊዜ ያዝ​ዘ​ዋል፤
ዘመ​ኑ​ንም ባስ​ጨ​ረ​ሰው ጊዜ ያን​ጊዜ ያሳ​ር​ፈ​ዋል።
7ሰው ምን​ድን ነው? ጥቅ​ሙስ ምን​ድን ነው?
8በጎ​ነቱ ምን​ድን ነው? ክፋ​ቱስ ምን​ድን ነው?
የዘ​መ​ኑም ቍጥር ቢበዛ መቶ ዓመት ነው፤
9በባ​ሕር ውስጥ እንደ አን​ዲት የውኃ ጠብታ፥ ከአ​ሸ​ዋ​ውም ሁሉ እንደ አን​ዲት የአ​ሸዋ ቅን​ጣት፥
እን​ዲሁ በዘ​ለ​ዓ​ለ​ማ​ዊ​ነት ዓመ​ታት ዘንድ የሰው ዘመኑ ጥቂት ነው።
10ስለ​ዚህ ነገር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይታ​ገ​ሣ​ቸ​ዋል።
ምሕ​ረ​ቱን አሳ​ደ​ረ​ባ​ቸው።
11ፍጻ​ሜ​ያ​ቸው ክፉ እንደ ሆነ አይቶ ዐወ​ቃ​ቸው፤
ምሕ​ረ​ቱን እን​ዲሁ አብ​ዝ​ት​ዋ​ልና።
12ሰው ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ብቻ ይቅር ይላል፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ፍጥ​ረ​ቱን ሁሉ ይቅር ይላል፤
13ይቈ​ጣል፥ ይገ​ር​ፋል፥ ይቅር ይላል፥
እረ​ኛም መን​ጋ​ውን እን​ዲ​መ​ልስ ይመ​ል​ሳል።
በተ​ግ​ሣጹ የሚ​ታ​ገ​ሡ​ትን፥ ሕጉ​ንም የሚ​ከ​ተ​ሉ​ትን ሰዎች ይቅር ይላ​ቸ​ዋል።
የተ​ወ​ደደ ምጽ​ዋት
14ልጄ ሆይ፥ በደ​ስ​ታህ መካ​ከል ኀዘ​ንን አታ​ስ​ገባ፤
በም​ት​ስ​ጠ​ውም ሁሉ ክፉ ነገ​ርን አት​ና​ገር።
15ዝናም ዋዕ​ይን የሚ​ያ​ቀ​ዘ​ቅ​ዘው አይ​ደ​ለ​ምን?
እን​ዲሁ በጎ ቃል ከመ​ስ​ጠት ይሻ​ላል።
16እነሆ እን​ግ​ዲህ ከመ​ስ​ጠት መል​ካም ቃል አይ​ሻ​ል​ምን?
ሁለ​ቱም ሁሉ በጻ​ድቅ ሰው ዘንድ ይገ​ኛሉ።
17ንፉግ ልቡ​ና​ውን ደስ ሳይ​ለው ይሰ​ጣል።
ሰነ​ፍም ይላ​ገ​ዳል አያ​መ​ሰ​ግ​ን​ምም።
18ሳት​ና​ገር ተረዳ፥ ሳት​ታ​መ​ምም ዳን።
19ሳይ​ፈ​ረ​ድ​ብህ ራስ​ህን መር​ምር፤
በመ​ከ​ራ​ህም ጊዜ ይቅ​ር​ታን ታገ​ኛ​ለህ።
20ሳት​ደ​ክም ራስ​ህን አዋ​ርድ፥
በበ​ደ​ል​ህም ጊዜ ንስሓ ግባ።
21ስእ​ለ​ት​ህን ፈጥ​ነህ ስጥ፤
ሳት​ሞ​ትም ጽድ​ቅን ሥራት።
22ሳት​ሳ​ልም አስ​ቀ​ድ​መህ ስእ​ለ​ት​ህን አዘ​ጋጅ፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ደ​ሚ​ፈ​ታ​ተ​ነው ሰው አት​ሁን።
23በተ​ቈ​ጣ​ህም ጊዜ የሞ​ትን ቀን ዐስብ፤
የፍ​ዳ​ህ​ንም ቀን ዐስብ፤ ንስ​ሓም ግባ ጸል​ይም።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ፊቱን በመ​መ​ለስ በመ​ጨ​ረሻ ስለ​ሚ​ሆ​ነው ቍጣና የበ​ቀል ቀን ዐስብ” ይላል።
24በጥ​ጋ​ብህ ወራት የረ​ኃ​ብን ወራት ዐስብ።
በተ​ድ​ላ​ህም ወራት የች​ግ​ርን ወራት ዐስብ።
25ኑሮ ከጧት እስከ ማታ ድረስ ትለ​ዋ​ወ​ጣ​ለ​ችና፥
ሁሉም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ አንድ ጊዜ ፈጥኖ ይደ​ረ​ጋ​ልና።
26ብልህ ሰው ግን ፈርቶ በሁሉ ይጠ​በ​ቃል፤
ኀጢ​አት በሚ​ሠ​ራ​በ​ትም ጊዜ ንስሓ ይገ​ባል።
27አስ​ተ​ዋይ ሰው ሁሉ ጥበ​ብን ያገ​ኛ​ታል፤
ያገ​ኛ​ት​ንም ሰው ታስ​መ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለች፥ ታስ​ከ​ብ​ረ​ዋ​ለ​ችም፥
28ነገር ዐዋ​ቂ​ዎች ራሳ​ቸው በል​ቡ​ና​ቸው ይራ​ቀ​ቃሉ፤
የተ​ረዳ ምሳ​ሌ​ንም ይና​ገ​ራሉ።
29አት​ሂድ፥ የኀ​ጢ​አ​ት​ንም ፈቃድ አት​ከ​ተል፤
ከክፉ ፍት​ወ​ትም ራቅ።
30ለሰ​ው​ነ​ትህ የም​ት​ወ​ድ​ደ​ውን ከሰ​ጠ​ኻት፥
ጠላ​ት​ህን በአ​ንተ የጨ​ከነ ታደ​ር​ገ​ዋ​ለች።
31በተ​ድላ ብዛት ደስ አይ​በ​ልህ፤
ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ደስ ይልህ ዘንድ አት​ለ​ምን።
32እን​ዳ​ት​ያዝ አንተ ድሃ ሳለህ፥ በከ​ረ​ጢ​ት​ህም ምንም ሳይ​ኖ​ርህ አት​በ​ደር።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ