መጽ​ሐፈ ሲራክ 16

16
1ጥቅም የሌ​ላ​ቸው ብዙ ልጆ​ችን አት​መኝ፤
በክ​ፉ​ዎች ልጆ​ችም ደስ አይ​በ​ልህ።
2በእ​ነ​ርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ከሌ​ለ​ባ​ቸው፥
ቢበ​ዙም በእ​ነ​ርሱ ደስ አይ​በ​ልህ።
3በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸ​ውም አት​ተ​ማ​መ​ን​ባ​ቸው፥
ብዛ​ታ​ቸ​ውም ደስ አያ​ሰ​ኝህ።
ከሺህ አንድ ደግ ይሻ​ላል፥
ክፉን ከመ​ው​ለ​ድም ሳይ​ወ​ልዱ መሞት ይሻ​ላል።
4በአ​ንድ ዐዋቂ ሀገር ትጸ​ና​ለ​ችና፥
በኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ብዛት ግን ትጠ​ፋ​ለች።
5ዐይኔ እን​ዲህ ያለ ብዙ ነገ​ርን አየች።
ጆሮ​ዬም ከዚህ የሚ​በ​ልጥ ሰማች።
6በኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ወገ​ኖች እሳት ትነ​ድ​ዳ​ለች፤
በወ​ን​ጀ​ለ​ኞች ሕዝብ ላይም ጥፋት ትነ​ድ​ዳ​ለች።
7በኀ​ይ​ላ​ቸው የታ​መኑ የቀ​ደሙ አር​በ​ኞ​ችም
ራሳ​ቸ​ውን አላ​ዳ​ኑም።
8ሎጥ ለኖ​ረ​ባ​ቸው፥ ራሳ​ቸ​ው​ንም ላኮሩ፥
ሎጥ​ንም ለተ​ጸ​የ​ፉት ሀገ​ሮች አል​ራ​ራ​ላ​ቸ​ውም።
9ኀጢ​አ​ተ​ኞች ሕዝ​ቦ​ችን ይቅር አላ​ላ​ቸ​ውም፤
በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ጠፉ እንጂ።
10እነ​ዚ​ህም የተ​ሰ​በ​ሰቡ፥ ልቡ​ና​ቸ​ው​ንም ያከፉ፥
ስድ​ስት መቶ ሺህ እግ​ረ​ኞች ነበሩ።
11ክሣደ ልቡ​ና​ውን ያጸና አንድ ሰው ቢኖር
እርሱ ቢድን ድንቅ ነው፥
ይቅ​ር​ታም መቅ​ሠ​ፍ​ትም ከእ​ርሱ ዘንድ ነውና ይቅር ማለት ይች​ላል፤
መቅ​ሠ​ፍ​ት​ንም ማም​ጣት ይች​ላል።
12ቍጣው እንደ ቸር​ነቱ ብዛት መጠን ነው፥
ለሰ​ውም እንደ ሥራው ይከ​ፍ​ለ​ዋል።
13ኀጢ​አ​ተኛ ሰው ከዳፋ አያ​መ​ል​ጥም፤
ጻድቅ ሰውም የት​ዕ​ግ​ሥ​ቱን ዋጋ አያ​ጣም።
14ምጽ​ዋት ሁሉ ይቅ​ር​ታን ያመ​ጣል፤
ሰውም ሁሉ እንደ ሥራው ያገ​ኛል።
15“ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አመ​ል​ጣ​ለሁ፤
በሰ​ማ​ያ​ትም የሚ​ያ​ገ​ኘኝ የለም።
16በብዙ አሕ​ዛ​ብም ዘንድ የሚ​ያ​ው​ቀኝ የለም።
17የሰ​ው​ነ​ቴስ ቍጥሯ በዓ​ለም ሁሉ ምን​ድን ነው?” አት​በል።
18እነሆ፥ ሰማይ፥ ከሰ​ማ​ያ​ትም በላይ ያለ ሰማይ፥
ከሰ​ማ​ይም በታች ያለ ውቅ​ያ​ኖስ፥ ምድ​ርም፥
በመ​ዓት በጐ​በ​ኛ​ቸው ጊዜ ይህ ሁሉ ይነ​ዋ​ወ​ጣል።
19ተራ​ሮ​ችም፥ የም​ድ​ርም መሠ​ረ​ቶች፥
በመ​ዓት ባያ​ቸው ጊዜ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ ይነ​ዋ​ወ​ጣ​ሉም።
20ይህ​ንም ልብ አያ​ስ​በ​ውም፤
መን​ገ​ዶ​ቹ​ንስ ማወቅ ማን ይች​ላል?
ገና​ና​ነ​ቱ​ንስ ጠብቆ መና​ገር ማን ይች​ላል?#በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. “ገና​ና​ነ​ቱ​ንስ ጠን​ቅቆ መና​ገር ማን ይች​ላል” የሚል የለም።
21ከሥ​ራ​ውም አብ​ዛ​ኛው ስውር ነው፥
ሰው የማ​ያ​የው ዐውሎ ነፋስ ነውና።
22እው​ነት ሥራ መሥ​ራ​ትን ማን ያስ​ተ​ም​ራል?
የም​ሕ​ረ​ቱ​ንስ ተስፋ ማን ደጅ ይጠ​ናል?
23አእ​ምሮ የሌ​ለው ሰው እን​ዲህ ያስ​ባል፤
ሰነ​ፍና በደ​ለኛ ሰውም ስን​ፍ​ናን ያስ​ባል።
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበብ በሥነ ፍጥ​ረት
24ልጄ ሆይ፥ ስማኝ፥ ጥበ​ብ​ንም ተማር፥
ነገ​ሬ​ንም ከል​ቡ​ናህ አድ​ም​ጠው።
25በሚ​ዛን መዝ​ነህ ጥበ​ብ​ህን ግለ​ጣት፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እገ​ል​ጣ​ለሁ” ይላል።
የት​ም​ህ​ር​ት​ህ​ንም ነገ​ሯን ተረዳ።
26የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ ከጥ​ንት ጀምሮ በሥ​ል​ጣኑ ተፈ​ጠረ።
ሥር​ዐ​ታ​ቸ​ው​ንም በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ለየ።
27ዓለም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጸንቶ ይኖር ዘንድ ሥራ​ውን ሁሉ አዘ​ጋጀ፥
ሠራ​ዊ​ታ​ቸ​ው​ንም በየ​ወ​ገ​ና​ቸው አዘ​ጋጀ፥
አይ​ሠ​ሩም፥ አይ​ጠ​ሙም፥ አይ​ራ​ቡ​ምም፥ ሥራ​ቸ​ውም አይ​ቋ​ረ​ጥም፤
28አንዱ ከሌ​ላው ጋር አይ​ጨ​ና​ነ​ቅም፤
ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙም ከቃሉ አይ​ወ​ጡም።
29ከዚህ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ርን ተመ​ለ​ከተ፤
ከበ​ረ​ከ​ቱም አጠ​ገ​ባት።
30በደ​ማ​ዊት ነፍስ ሕያው የሆነ ፍጥ​ረት ሁሉ በም​ድር መላ፤
መመ​ለ​ሻ​ቸ​ውም ወደ ምድር ነው።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ