መጽ​ሐፈ ሲራክ 15

15
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሰው እን​ዲህ ያደ​ር​ጋል፤
ሕጉ​ንም የሚ​ጠ​ብቅ ሰው ጥበ​ብን ያገ​ኛ​ታል።
2እንደ እናቱ ትን​ከ​ባ​ከ​በ​ዋ​ለች፤
እንደ ቆንጆ ሴትም ትቀ​በ​ለ​ዋ​ለች።
3የጥ​በ​ብን እህል ትመ​ግ​በ​ዋ​ለች፤
የዕ​ው​ቀ​ት​ንም ውኃ ታጠ​ጣ​ዋ​ለች።
4በእ​ር​ስዋ ይመ​ረ​ኰ​ዛል፥ አይ​ፍ​ገ​መ​ገ​ምም፤
የሚ​ታ​መ​ን​ባ​ትም አያ​ፍ​ርም።
5ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ይልቅ ከፍ ከፍ ታደ​ር​ገ​ዋ​ለች፥
በብዙ ሰዎች መካ​ከ​ልም አፉን ገልጦ ይና​ገ​ራል።
6ደስ​ታን ትሰ​ጠ​ዋ​ለች፥
የደ​ስታ ዘው​ድ​ንም ታቀ​ዳ​ጀ​ዋ​ለች፥
ስሙ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያስ​ጠ​ራል።
7አላ​ዋ​ቂ​ዎች ግን አያ​ገ​ኙ​አ​ትም፤
ኀጢ​አ​ተ​ኞ​ችም አያ​ዩ​አ​ትም።
8ከት​ዕ​ቢ​ተ​ኞች ሰዎ​ችም የራ​ቀች ናት፤
ሐሰ​ተ​ኞች ሰዎች አያ​ስ​ቧ​ትም።
9የኀ​ጢ​አ​ተኛ ሰው የቃሉ ነገር ያማረ አይ​ደ​ለም፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በመ​ፍ​ራት የሚ​ና​ገር አይ​ደ​ለ​ምና።
10ምሳ​ሌን በጥ​በብ ይና​ገ​ሯ​ታል፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ማ​ራ​ትን ሰው ይረ​ዳ​ዋል።
11“ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብዬ ተከ​ለ​ከ​ልሁ” አት​በል፤
እርሱ የሚ​ጠ​ላ​ው​ንም አታ​ድ​ርግ።
12“እርሱ አሳ​ተኝ” አት​በል፤
እር​ሱስ ኀጢ​አ​ተኛ ሰውን አይ​ወ​ድ​ድም፤
13እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የረ​ከ​ሰ​ውን ሁሉ ይጠ​ላ​ልና፤
የሚ​ፈ​ሩ​ት​ንም ሰዎች ይወ​ዳ​ቸ​ዋል።#ግሪኩ “ኀጢ​አ​ትን እየ​ወ​ደዱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እፈ​ራ​ለሁ ማለት አይ​ቻ​ልም” ይላል።
14እርሱ አስ​ቀ​ድሞ ሰውን በን​ጽሕ ፈጠ​ረው፥
እንደ ጠባ​ዩም በወ​ደ​ደው እን​ዲ​ሠራ ተወው።
15ትእ​ዛ​ዙን ትጠ​ብቅ ዘንድ፥
ሃይ​ማ​ኖ​ቱ​ንም ታጸና ዘንድ ብት​ወድ ግን ፈቃዱ ነው።#ግሪኩ “የአ​ንተ ፈቃድ ነው” ይላል።
16እጅ​ህን በመ​ረ​ጥ​ኸው ትጨ​ምር ዘንድ፥
እነሆ፥ እሳ​ት​ንና ውኃን አኖ​ረ​ልህ።
17ሕይ​ወ​ትና ሞትም በሰው ፊት ናቸው፥
ከእ​ነ​ር​ሱም የመ​ረ​ጠ​ውን ይሰ​ጡ​ታል።
18የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበቡ ታላቅ ነውና፥
ኀይ​ሉም የጸና ነውና ሁሉን ያው​ቃል፥ ሁሉ​ንም ያያል።
19ዐይ​ኖ​ቹም የሚ​ፈ​ሩ​ትን ሰዎች ይመ​ለ​ከ​ታሉ፤
እር​ሱም የሰ​ውን ሥራ ሁሉ ያው​ቃል።
20እር​ሱስ ኀጢ​አ​ትን ይሠራ ዘንድ ያዘ​ዘው የለም፤
ይበ​ድ​ልም ዘንድ ማን​ንም አላ​ሰ​ና​በ​ተም፤

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ