መጽሐፈ ሲራክ 15
15
1እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንዲህ ያደርጋል፤
ሕጉንም የሚጠብቅ ሰው ጥበብን ያገኛታል።
2እንደ እናቱ ትንከባከበዋለች፤
እንደ ቆንጆ ሴትም ትቀበለዋለች።
3የጥበብን እህል ትመግበዋለች፤
የዕውቀትንም ውኃ ታጠጣዋለች።
4በእርስዋ ይመረኰዛል፥ አይፍገመገምም፤
የሚታመንባትም አያፍርም።
5ከባልንጀራው ይልቅ ከፍ ከፍ ታደርገዋለች፥
በብዙ ሰዎች መካከልም አፉን ገልጦ ይናገራል።
6ደስታን ትሰጠዋለች፥
የደስታ ዘውድንም ታቀዳጀዋለች፥
ስሙንም ለዘለዓለም ያስጠራል።
7አላዋቂዎች ግን አያገኙአትም፤
ኀጢአተኞችም አያዩአትም።
8ከትዕቢተኞች ሰዎችም የራቀች ናት፤
ሐሰተኞች ሰዎች አያስቧትም።
9የኀጢአተኛ ሰው የቃሉ ነገር ያማረ አይደለም፥
እግዚአብሔርን በመፍራት የሚናገር አይደለምና።
10ምሳሌን በጥበብ ይናገሯታል፤
እግዚአብሔርም የሚማራትን ሰው ይረዳዋል።
11“ስለ እግዚአብሔር ብዬ ተከለከልሁ” አትበል፤
እርሱ የሚጠላውንም አታድርግ።
12“እርሱ አሳተኝ” አትበል፤
እርሱስ ኀጢአተኛ ሰውን አይወድድም፤
13እግዚአብሔር የረከሰውን ሁሉ ይጠላልና፤
የሚፈሩትንም ሰዎች ይወዳቸዋል።#ግሪኩ “ኀጢአትን እየወደዱ እግዚአብሔርን እፈራለሁ ማለት አይቻልም” ይላል።
14እርሱ አስቀድሞ ሰውን በንጽሕ ፈጠረው፥
እንደ ጠባዩም በወደደው እንዲሠራ ተወው።
15ትእዛዙን ትጠብቅ ዘንድ፥
ሃይማኖቱንም ታጸና ዘንድ ብትወድ ግን ፈቃዱ ነው።#ግሪኩ “የአንተ ፈቃድ ነው” ይላል።
16እጅህን በመረጥኸው ትጨምር ዘንድ፥
እነሆ፥ እሳትንና ውኃን አኖረልህ።
17ሕይወትና ሞትም በሰው ፊት ናቸው፥
ከእነርሱም የመረጠውን ይሰጡታል።
18የእግዚአብሔር ጥበቡ ታላቅ ነውና፥
ኀይሉም የጸና ነውና ሁሉን ያውቃል፥ ሁሉንም ያያል።
19ዐይኖቹም የሚፈሩትን ሰዎች ይመለከታሉ፤
እርሱም የሰውን ሥራ ሁሉ ያውቃል።
20እርሱስ ኀጢአትን ይሠራ ዘንድ ያዘዘው የለም፤
ይበድልም ዘንድ ማንንም አላሰናበተም፤
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 15: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ