መጽ​ሐፈ ሲራክ 14

14
1በአፉ ያል​ተ​ሰ​ነ​ካ​ከለ ሰው ብፁዕ ነው፤
ኀጢ​አ​ተኛ ሰውን ግን ኀዘን አያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጠ​ውም።
2ሰው​ነ​ቱን የማ​ያ​ሳ​ዝን፥
ተስ​ፋ​ው​ንም የማ​ይ​ቈ​ርጥ ሰው ብፁዕ ነው።
ሀብ​ትን በሚ​ገባ ስለ መጠ​ቀም
3ነገ​ርን ለማ​ያ​ውቅ ሰው ብል​ጽ​ግና አይ​ገ​ባ​ውም፤
ለን​ፉ​ግም ሰው ገን​ዘብ አይ​ገ​ባ​ውም።
4ሰው​ነ​ቱን የሚ​ነ​ፍ​ጋት ሰው ለሌላ ያከ​ማ​ቻል፥
ሌላ ሰው ግን በገ​ን​ዘቡ ደስ ይለ​ዋል።
5ሰው​ነ​ቱን የሚ​ነ​ፍግ በገ​ን​ዘ​ቡም ደስ የማ​ይ​ለው ሰው፥
ለማን ይለ​ግስ ዘንድ አለው?
6ሰው​ነ​ቱን ከሚ​ነ​ፍግ ሰው የሚ​ከፋ የለም፤
ለክ​ፋ​ቱም እርሱ ፍዳ ይሆ​ነ​ዋል።
7በጎ ቢያ​ደ​ር​ግም ባረጀ ጊዜ ብቻ ነው፥
ኋላም ክፋ​ቱን ያሳ​ው​ቃል።
8የን​ፉግ ሰው ዐይኑ ክፉ ነው፥
ከድሃ ፊቱን የሚ​መ​ልስ ሰው​ነ​ቱን ቸል ይላል።
9ለስሱ ሰው ዐይን ድር​ሻው አያ​ጠ​ግ​በ​ውም፤
የል​ቡ​ና​ውም ክፋት ሰው​ነ​ቱን ያከ​ሳ​ዋል።
10የን​ፉግ ሰው ዐይኑ እህል ይነ​ፍ​ጋል፤
በማ​ዕ​ድም ይነ​ፍ​ጋል።
11ልጄ ሆይ፥ የሚ​ቻ​ል​ህን ያህል ሰው​ነ​ት​ህን አዘ​ጋ​ጃት፥
እን​ደ​ሚ​ገ​ባ​ህም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባእ አግባ።
12ሞት እን​ደ​ማ​ይ​ቀር ዐስብ፥
የም​ት​ሞ​ት​ባ​ትም ቀን ትቀ​ራ​ለች ብለህ አት​ጠ​ራ​ጠር።
13ሳት​ሞት ለባ​ል​ን​ጀ​ራህ በጎ አድ​ርግ፤
እጅ​ህ​ንም ዘር​ግ​ተህ የተ​ቻ​ለ​ህን ያህል ስጥ።
14በደ​ስ​ታህ ጊዜ አት​ታጣ፤
በጎ ድር​ሻ​ህም አያ​ም​ል​ጥህ።
15ገን​ዘ​ብ​ህን ለባ​ዕድ የም​ት​ተው አይ​ደ​ለ​ምን?
ወራ​ሾ​ች​ህስ ገን​ዘ​ብ​ህን ሁሉ የሚ​ካ​ፈሉ አይ​ደ​ለ​ምን?
16ገን​ዘ​ብ​ህን አን​ሥ​ተህ ስጥ፥
ሰው​ነ​ት​ህ​ንም ደስ አሰ​ኛት፥
በመ​ቃ​ብር የም​ታ​ገ​ኘው ደስታ የለ​ምና።
17ሰው ሁሉ እንደ ልብስ ያረ​ጃል፥
ሞትን ትሞት ዘንድ የሕግ ትእ​ዛዝ ተሠ​ር​ት​ዋ​ልና።
18ቅጠሉ ጭፍቅ ያለ የእ​ን​ጨት ቅጠል የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቅጠል እን​ዲ​ረ​ግፍ
የኋ​ላ​ውም እን​ዲ​ለ​መ​ልም፤
ደማ​ዊና ሥጋዊ ፍጥ​ረት ሁሉ እን​ዲሁ ነው፤
ይህ ይወ​ለ​ዳል ያም ይሞ​ታል።
19ሥራ ሁሉ ፈጽሞ ይጠ​ፋል፤
ሠሪ​ውም ከሥ​ራው ጋር ይጠ​ፋል።
ጥበ​ብን በመ​ፈ​ለግ የሚ​ገኝ ደስታ
20ነገር ግን ብልህ ሆኖ የሞተ፥
ጥበ​ቡ​ንም ተምሮ የጠ​በቀ ሰው ብፁዕ ነው።
21የጥ​በ​ብን መን​ገድ በልቡ የሚ​ያ​ስብ፥
ምሥ​ጢ​ሯ​ንም የሚ​ማር፥
22ጥበ​ብን የሚ​ከ​ተ​ላት፥ ፍለ​ጋ​ዋ​ንም የሚ​መ​ረ​ምር፥
መን​ገ​ድ​ዋ​ንም የሚ​ጠ​ብቅ፥
23መስ​ኮ​ት​ዋን የሚ​ጎ​በኝ፥
በበ​ሮ​ች​ዋም ተቀ​ምጦ የሚ​ያ​ዳ​ምጥ፥
24በቤ​ት​ዋም አጠ​ገብ የሚ​ኖር፥
በዙ​ሪ​ያ​ዋም የድ​ን​ኳ​ኑን ካስማ የሚ​ተ​ክል፥
25ድን​ኳ​ኑን በአ​ጠ​ገ​ብዋ የሚ​ያ​ቆም፥
ባማረ ማደ​ሪ​ያ​ዋም የሚ​ኖር፥
26ልጆ​ቹ​ንም በጥ​ላ​ዎ​ችዋ የሚ​ያ​ስ​ቀ​ምጥ፥
በቅ​ር​ን​ጫ​ፎ​ች​ዋም በታች የሚ​ያ​ድር፥
27ከበ​ረሃ ሐሩ​ርም በበ​ታ​ችዋ የሚ​ጠ​ለል፤
በክ​ብ​ር​ዋም የሚ​ያ​ርፍ ብፁዕ ነው።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ