መጽሐፈ ሲራክ 14
14
1በአፉ ያልተሰነካከለ ሰው ብፁዕ ነው፤
ኀጢአተኛ ሰውን ግን ኀዘን አያስደነግጠውም።
2ሰውነቱን የማያሳዝን፥
ተስፋውንም የማይቈርጥ ሰው ብፁዕ ነው።
ሀብትን በሚገባ ስለ መጠቀም
3ነገርን ለማያውቅ ሰው ብልጽግና አይገባውም፤
ለንፉግም ሰው ገንዘብ አይገባውም።
4ሰውነቱን የሚነፍጋት ሰው ለሌላ ያከማቻል፥
ሌላ ሰው ግን በገንዘቡ ደስ ይለዋል።
5ሰውነቱን የሚነፍግ በገንዘቡም ደስ የማይለው ሰው፥
ለማን ይለግስ ዘንድ አለው?
6ሰውነቱን ከሚነፍግ ሰው የሚከፋ የለም፤
ለክፋቱም እርሱ ፍዳ ይሆነዋል።
7በጎ ቢያደርግም ባረጀ ጊዜ ብቻ ነው፥
ኋላም ክፋቱን ያሳውቃል።
8የንፉግ ሰው ዐይኑ ክፉ ነው፥
ከድሃ ፊቱን የሚመልስ ሰውነቱን ቸል ይላል።
9ለስሱ ሰው ዐይን ድርሻው አያጠግበውም፤
የልቡናውም ክፋት ሰውነቱን ያከሳዋል።
10የንፉግ ሰው ዐይኑ እህል ይነፍጋል፤
በማዕድም ይነፍጋል።
11ልጄ ሆይ፥ የሚቻልህን ያህል ሰውነትህን አዘጋጃት፥
እንደሚገባህም ለእግዚአብሔር መባእ አግባ።
12ሞት እንደማይቀር ዐስብ፥
የምትሞትባትም ቀን ትቀራለች ብለህ አትጠራጠር።
13ሳትሞት ለባልንጀራህ በጎ አድርግ፤
እጅህንም ዘርግተህ የተቻለህን ያህል ስጥ።
14በደስታህ ጊዜ አትታጣ፤
በጎ ድርሻህም አያምልጥህ።
15ገንዘብህን ለባዕድ የምትተው አይደለምን?
ወራሾችህስ ገንዘብህን ሁሉ የሚካፈሉ አይደለምን?
16ገንዘብህን አንሥተህ ስጥ፥
ሰውነትህንም ደስ አሰኛት፥
በመቃብር የምታገኘው ደስታ የለምና።
17ሰው ሁሉ እንደ ልብስ ያረጃል፥
ሞትን ትሞት ዘንድ የሕግ ትእዛዝ ተሠርትዋልና።
18ቅጠሉ ጭፍቅ ያለ የእንጨት ቅጠል የመጀመሪያው ቅጠል እንዲረግፍ
የኋላውም እንዲለመልም፤
ደማዊና ሥጋዊ ፍጥረት ሁሉ እንዲሁ ነው፤
ይህ ይወለዳል ያም ይሞታል።
19ሥራ ሁሉ ፈጽሞ ይጠፋል፤
ሠሪውም ከሥራው ጋር ይጠፋል።
ጥበብን በመፈለግ የሚገኝ ደስታ
20ነገር ግን ብልህ ሆኖ የሞተ፥
ጥበቡንም ተምሮ የጠበቀ ሰው ብፁዕ ነው።
21የጥበብን መንገድ በልቡ የሚያስብ፥
ምሥጢሯንም የሚማር፥
22ጥበብን የሚከተላት፥ ፍለጋዋንም የሚመረምር፥
መንገድዋንም የሚጠብቅ፥
23መስኮትዋን የሚጎበኝ፥
በበሮችዋም ተቀምጦ የሚያዳምጥ፥
24በቤትዋም አጠገብ የሚኖር፥
በዙሪያዋም የድንኳኑን ካስማ የሚተክል፥
25ድንኳኑን በአጠገብዋ የሚያቆም፥
ባማረ ማደሪያዋም የሚኖር፥
26ልጆቹንም በጥላዎችዋ የሚያስቀምጥ፥
በቅርንጫፎችዋም በታች የሚያድር፥
27ከበረሃ ሐሩርም በበታችዋ የሚጠለል፤
በክብርዋም የሚያርፍ ብፁዕ ነው።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 14: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፈ ሲራክ 14
14
1በአፉ ያልተሰነካከለ ሰው ብፁዕ ነው፤
ኀጢአተኛ ሰውን ግን ኀዘን አያስደነግጠውም።
2ሰውነቱን የማያሳዝን፥
ተስፋውንም የማይቈርጥ ሰው ብፁዕ ነው።
ሀብትን በሚገባ ስለ መጠቀም
3ነገርን ለማያውቅ ሰው ብልጽግና አይገባውም፤
ለንፉግም ሰው ገንዘብ አይገባውም።
4ሰውነቱን የሚነፍጋት ሰው ለሌላ ያከማቻል፥
ሌላ ሰው ግን በገንዘቡ ደስ ይለዋል።
5ሰውነቱን የሚነፍግ በገንዘቡም ደስ የማይለው ሰው፥
ለማን ይለግስ ዘንድ አለው?
6ሰውነቱን ከሚነፍግ ሰው የሚከፋ የለም፤
ለክፋቱም እርሱ ፍዳ ይሆነዋል።
7በጎ ቢያደርግም ባረጀ ጊዜ ብቻ ነው፥
ኋላም ክፋቱን ያሳውቃል።
8የንፉግ ሰው ዐይኑ ክፉ ነው፥
ከድሃ ፊቱን የሚመልስ ሰውነቱን ቸል ይላል።
9ለስሱ ሰው ዐይን ድርሻው አያጠግበውም፤
የልቡናውም ክፋት ሰውነቱን ያከሳዋል።
10የንፉግ ሰው ዐይኑ እህል ይነፍጋል፤
በማዕድም ይነፍጋል።
11ልጄ ሆይ፥ የሚቻልህን ያህል ሰውነትህን አዘጋጃት፥
እንደሚገባህም ለእግዚአብሔር መባእ አግባ።
12ሞት እንደማይቀር ዐስብ፥
የምትሞትባትም ቀን ትቀራለች ብለህ አትጠራጠር።
13ሳትሞት ለባልንጀራህ በጎ አድርግ፤
እጅህንም ዘርግተህ የተቻለህን ያህል ስጥ።
14በደስታህ ጊዜ አትታጣ፤
በጎ ድርሻህም አያምልጥህ።
15ገንዘብህን ለባዕድ የምትተው አይደለምን?
ወራሾችህስ ገንዘብህን ሁሉ የሚካፈሉ አይደለምን?
16ገንዘብህን አንሥተህ ስጥ፥
ሰውነትህንም ደስ አሰኛት፥
በመቃብር የምታገኘው ደስታ የለምና።
17ሰው ሁሉ እንደ ልብስ ያረጃል፥
ሞትን ትሞት ዘንድ የሕግ ትእዛዝ ተሠርትዋልና።
18ቅጠሉ ጭፍቅ ያለ የእንጨት ቅጠል የመጀመሪያው ቅጠል እንዲረግፍ
የኋላውም እንዲለመልም፤
ደማዊና ሥጋዊ ፍጥረት ሁሉ እንዲሁ ነው፤
ይህ ይወለዳል ያም ይሞታል።
19ሥራ ሁሉ ፈጽሞ ይጠፋል፤
ሠሪውም ከሥራው ጋር ይጠፋል።
ጥበብን በመፈለግ የሚገኝ ደስታ
20ነገር ግን ብልህ ሆኖ የሞተ፥
ጥበቡንም ተምሮ የጠበቀ ሰው ብፁዕ ነው።
21የጥበብን መንገድ በልቡ የሚያስብ፥
ምሥጢሯንም የሚማር፥
22ጥበብን የሚከተላት፥ ፍለጋዋንም የሚመረምር፥
መንገድዋንም የሚጠብቅ፥
23መስኮትዋን የሚጎበኝ፥
በበሮችዋም ተቀምጦ የሚያዳምጥ፥
24በቤትዋም አጠገብ የሚኖር፥
በዙሪያዋም የድንኳኑን ካስማ የሚተክል፥
25ድንኳኑን በአጠገብዋ የሚያቆም፥
ባማረ ማደሪያዋም የሚኖር፥
26ልጆቹንም በጥላዎችዋ የሚያስቀምጥ፥
በቅርንጫፎችዋም በታች የሚያድር፥
27ከበረሃ ሐሩርም በበታችዋ የሚጠለል፤
በክብርዋም የሚያርፍ ብፁዕ ነው።