መጽሐፈ ሲራክ 13
13
ከጓደኛ ስለ መጠበቅ
1አደሮ ማር የዳሰሰ ሰው በእርሱ ይያዛል፤
ትዕቢተኛ ሰውንም ወዳጅ ያደረገ እንደ እርሱ ይሆናል።
2የከበደ ሸክምን አንሥተህ በራስህ አትሸከም፥
ገንዘብህንም ከሚበረታብህና ከባለጸጋ ገንዘብ ጋራ አትጨምር፥
የሸክላ ድስት ከብረት ድስት ጋር በየት አንድ ይሆናል?
እርስዋ መትታ እርስዋ ትጮኻለችና፥ እርስዋም ትሰብራለችና።
3እንደዚሁ ሁሉ ባለ ጸጋ እርሱ ይበድላል፥ እርሱም ይቈጣል፤
ድሃ ግን እርሱ ይገፋል፥ እርሱም ይለማመጣል።
4የምትጠቅመው ነገር ቢኖር ወደ እርሱ ያቀርብሃል፤
ብትቸገር ግን ከዚያ በኋላ አያይህም።
5ገንዘብ ቢኖርህ ከአንተ ጋራ አንድ ይሆናል፥
ያንተንም ይጨርስልሃል፤ ዳግመኛም አያመሰግንህም።
6አንተን የሚፈልግበት ግዳጅ ቢኖረው ያባብልሃል፤
ብዙ ተስፋም ይሰጥሃል፤ ይሥቅልሃል፤
በጎ ነገርም ይናገርሃል፤ ምን ትፈልጋለህም ይልሃል።
7በመብሉም ይሸነግልሃል፤ አንድ ጊዜ፥ ሁለት ጊዜ፥ ሦስት ጊዜም ያስትሃል፤
ከዚህም በኋላ እንደማይሰማህ ወደ ኋላ ይመለሳል፤
ቢያይህም ይሥቅብሃል፤ ራሱንም ይነቀንቅብሃል።
8እንዳያስትህና እንዳያታልልህ ከእንዲህ ያለ ሰው ተጠበቅ፥
በደስታህም መካከል ኀዘን አታግባ።
9ባለጸጋ ያዘዘህን ለጊዜው እሽ በለው፥
ቢጠራህም እንቢ አትበለው፤ ፈጽሞም ይወድሃል።
10አትራቅ አትሳትም፥
ነገር ግን እንዳይዘነጋህ ፈጽመህ አትራቀው።
11ከእርሱ ጋር ነገርን አታብዛ፤
በነገሩ ብዛት ይፈትንሃልና፤
ከአንተም ጋራ የሚሥቅ መስሎ ይመረምርሃልና በነገሩ ብዛት አትመነው።
12መታሰሩና ጥፋቱ አያሳዝነውምና፥
የባልንጀራውን ምሥጢር ለሚያወጣ ሰው ይቅርታ የለውም።
13ከገዳይህ ጋር ትሄዳለህና ዕወቅ፤
አጥብቀህም ተጠበቅ።
14ከብት ሁሉ ዘመዱን ይወድዳል፤
ሰውም ሁሉ ባልንጀራውን ይወድዳል።
15ፍጥረቱ ሁሉ እንደ እርሱ ካለ ፍጥረት ጋራ አንድ ይሆናል፤
ሰውም የሚመስለውን ይከተላል።
16ተኵላ ከበግ ጋር በየት ወዳጅ ይሆናል?
ኀጢአተኛ ሰውም ከጻድቅ ሰው ጋራ እንዲሁ ነው።
17ውሾችን ከጅቦች ጋር ማን ያስማማቸዋል?
ድሃውንስ ከባለጸጋው ጋራ ማን ወዳጅ ያደርገዋል?
18የሜዳ አህዮች የአንበሶች አደን ናቸው፤
እንደዚሁም ሁሉ ባለጸጋው ድሃውን ይቀማዋል።
19ትዕቢተኛ ሰው ራሱን የሚያዋርደውን ሰው ይጸየፈዋል፤
እንዲሁም ሁሉ ባለጸጋው ድሃውን ይጸየፈዋል።
20ባለጸጋ ቢፍገመገም ወዳጆቹ ይደግፉታል፤
ድሃ ግን ቢወድቅ ባልንጀሮቹ ይረግጡታል።
21ባለጸጋ ቢያድጠው ብዙ ሰዎች ያነሡታል፥
ክፉ ቢናገርም ነገሩን ያቀኑለታል፤
ድሃ ግን ቢስት ይረግሙታል፤
በጎ ነገርም ቢናገር አያደምጡትም።
22ባለጸጋ ቢናገር ሁሉ ዝም ይላል፤
ቃሉንም ያደንቁለታል፥ ነገሩንም እስከ ደመና ያደርሱለታል፤
ድሃ ግን ምንም በጎ ነገር ቢናገር ይህ ምንድን ነው? ይሉታል፤ ቢሰነካከልም ያዳፉታል።
23ኀጢአት ሳትሠራ ባለጸግነት መልካም ነው፤
ኃጥእ ድህነቱን ባፉ ያክፋፋታል።
24ደስ ቢለው፥ ቢያዝንም
የሰው ልቡ ፊቱን ይለውጠዋል።
25ደስ ያለው ልቡና ምልክቱ ብሩህ ገጽ ነው፥
ደክመህ የጥበብን ምክር ታገኛለህ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 13: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፈ ሲራክ 13
13
ከጓደኛ ስለ መጠበቅ
1አደሮ ማር የዳሰሰ ሰው በእርሱ ይያዛል፤
ትዕቢተኛ ሰውንም ወዳጅ ያደረገ እንደ እርሱ ይሆናል።
2የከበደ ሸክምን አንሥተህ በራስህ አትሸከም፥
ገንዘብህንም ከሚበረታብህና ከባለጸጋ ገንዘብ ጋራ አትጨምር፥
የሸክላ ድስት ከብረት ድስት ጋር በየት አንድ ይሆናል?
እርስዋ መትታ እርስዋ ትጮኻለችና፥ እርስዋም ትሰብራለችና።
3እንደዚሁ ሁሉ ባለ ጸጋ እርሱ ይበድላል፥ እርሱም ይቈጣል፤
ድሃ ግን እርሱ ይገፋል፥ እርሱም ይለማመጣል።
4የምትጠቅመው ነገር ቢኖር ወደ እርሱ ያቀርብሃል፤
ብትቸገር ግን ከዚያ በኋላ አያይህም።
5ገንዘብ ቢኖርህ ከአንተ ጋራ አንድ ይሆናል፥
ያንተንም ይጨርስልሃል፤ ዳግመኛም አያመሰግንህም።
6አንተን የሚፈልግበት ግዳጅ ቢኖረው ያባብልሃል፤
ብዙ ተስፋም ይሰጥሃል፤ ይሥቅልሃል፤
በጎ ነገርም ይናገርሃል፤ ምን ትፈልጋለህም ይልሃል።
7በመብሉም ይሸነግልሃል፤ አንድ ጊዜ፥ ሁለት ጊዜ፥ ሦስት ጊዜም ያስትሃል፤
ከዚህም በኋላ እንደማይሰማህ ወደ ኋላ ይመለሳል፤
ቢያይህም ይሥቅብሃል፤ ራሱንም ይነቀንቅብሃል።
8እንዳያስትህና እንዳያታልልህ ከእንዲህ ያለ ሰው ተጠበቅ፥
በደስታህም መካከል ኀዘን አታግባ።
9ባለጸጋ ያዘዘህን ለጊዜው እሽ በለው፥
ቢጠራህም እንቢ አትበለው፤ ፈጽሞም ይወድሃል።
10አትራቅ አትሳትም፥
ነገር ግን እንዳይዘነጋህ ፈጽመህ አትራቀው።
11ከእርሱ ጋር ነገርን አታብዛ፤
በነገሩ ብዛት ይፈትንሃልና፤
ከአንተም ጋራ የሚሥቅ መስሎ ይመረምርሃልና በነገሩ ብዛት አትመነው።
12መታሰሩና ጥፋቱ አያሳዝነውምና፥
የባልንጀራውን ምሥጢር ለሚያወጣ ሰው ይቅርታ የለውም።
13ከገዳይህ ጋር ትሄዳለህና ዕወቅ፤
አጥብቀህም ተጠበቅ።
14ከብት ሁሉ ዘመዱን ይወድዳል፤
ሰውም ሁሉ ባልንጀራውን ይወድዳል።
15ፍጥረቱ ሁሉ እንደ እርሱ ካለ ፍጥረት ጋራ አንድ ይሆናል፤
ሰውም የሚመስለውን ይከተላል።
16ተኵላ ከበግ ጋር በየት ወዳጅ ይሆናል?
ኀጢአተኛ ሰውም ከጻድቅ ሰው ጋራ እንዲሁ ነው።
17ውሾችን ከጅቦች ጋር ማን ያስማማቸዋል?
ድሃውንስ ከባለጸጋው ጋራ ማን ወዳጅ ያደርገዋል?
18የሜዳ አህዮች የአንበሶች አደን ናቸው፤
እንደዚሁም ሁሉ ባለጸጋው ድሃውን ይቀማዋል።
19ትዕቢተኛ ሰው ራሱን የሚያዋርደውን ሰው ይጸየፈዋል፤
እንዲሁም ሁሉ ባለጸጋው ድሃውን ይጸየፈዋል።
20ባለጸጋ ቢፍገመገም ወዳጆቹ ይደግፉታል፤
ድሃ ግን ቢወድቅ ባልንጀሮቹ ይረግጡታል።
21ባለጸጋ ቢያድጠው ብዙ ሰዎች ያነሡታል፥
ክፉ ቢናገርም ነገሩን ያቀኑለታል፤
ድሃ ግን ቢስት ይረግሙታል፤
በጎ ነገርም ቢናገር አያደምጡትም።
22ባለጸጋ ቢናገር ሁሉ ዝም ይላል፤
ቃሉንም ያደንቁለታል፥ ነገሩንም እስከ ደመና ያደርሱለታል፤
ድሃ ግን ምንም በጎ ነገር ቢናገር ይህ ምንድን ነው? ይሉታል፤ ቢሰነካከልም ያዳፉታል።
23ኀጢአት ሳትሠራ ባለጸግነት መልካም ነው፤
ኃጥእ ድህነቱን ባፉ ያክፋፋታል።
24ደስ ቢለው፥ ቢያዝንም
የሰው ልቡ ፊቱን ይለውጠዋል።
25ደስ ያለው ልቡና ምልክቱ ብሩህ ገጽ ነው፥
ደክመህ የጥበብን ምክር ታገኛለህ።