ኦሪት ዘፀአት 7:1-6
ኦሪት ዘፀአት 7:1-6 መቅካእኤ
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እይ፥ እኔ ለፈርዖን አምላክ አድርጌሃለሁ፤ ወንድምህም አሮን ነቢይህ ይሆናል። አንተ ያዘዝሁህን ሁሉ ትነግረዋለህ፤ ወንድምህም አሮን የእስራኤልን ልጆች ከአገሩ እንዲለቅ ፈርዖንን ይነግረዋል። እኔም የፈርዖንን ልብ አደነድናለሁ፥ ምልክቶቼንና ድንቆቼን በግብጽ ምድር ላይ አበዛለሁ። ፈርዖንም እናንተን አይሰማችሁም፥ እጄንም በግብጽ ላይ አደርጋለሁ፥ ሠራዊቴን፥ ሕዝቤን የእስራኤልን ልጆች፥ በታላቅ የፍርድ ሥራ ከግብጽ ምድር አወጣለሁ። ግብፃውያንም፥ እጄን በግብጽ ላይ ዘርግቼ የእስራኤልን ልጆች ከመካከላቸው ሳወጣ፥ እኔ ጌታ እንደሆንኩ ያውቃሉ።” ሙሴና አሮንም እንዲሁ አደረጉ፤ ጌታ እንዳዘዛቸው አደረጉ።

