1
ትንቢተ ኤርምያስ 37:17
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ንጉሡ ሴዴቅያስ ልኮ አስመጣው፥ ንጉሡም በቤቱ፦ “በውኑ ከጌታ ዘንድ የሆነ ቃል አለን?” ብሎ በድብቅ ጠየቀው። ኤርምያስም፦ “አዎን አለ” ብሎ መለሰ። ከዚያም በኋላ፦ “በባቢሎን ንጉሥ እጅ ተላልፈህ ትሰጣለህ” አለ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ትንቢተ ኤርምያስ 37:15
አለቆችም ተቈጥተው ኤርምያስን መቱት፥ የጸሐፊውንም የዮናታንን ቤት የእስር ቤት አድርገውት ነበርና በዚያ ቤት አስረው አኖሩት።
3
ትንቢተ ኤርምያስ 37:2
በነቢዩ በኤርምያስም በኩል የተናገረውን የጌታን ቃላት እርሱም ሆነ ባርያዎቹ የአገሩም ሕዝብ አልሰሙም።
4
ትንቢተ ኤርምያስ 37:9
ጌታ እንዲህ ይላል፦ አይሄዱምና፦ “ከለዳውያን በእርግጥ ከእኛ ዘንድ ይሄዳሉ” ብላችሁ ራሳችሁን አታታሉ።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች