ኤርምያስ 37:15
ኤርምያስ 37:15 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አለቆችም በኤርምያስ ላይ ተቈጥተው መቱት፤ የግዞት ቤት አድርገውት ነበርና ወደ ጸሓፊው ወደ ዮናታን ቤት ላኩት።
ኤርምያስ 37:15 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
መኳንንቱም እጅግ ተቈጥተው ኤርምያስን ደበደቡት፤ የግዞት ቤትም አድርገውት በነበረው፤ በጸሓፊው በዮናታን ቤት አሰሩት።
ኤርምያስ 37:15 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
አለቆችም ተቈጥተው ኤርምያስን መቱት፥ የጸሐፊውንም የዮናታንን ቤት የግዞት ቤት አድርገውት ነበርና በዚያ አኖሩት።