1
የማቴዎስ ወንጌል 15:18-19
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ከአፍ የሚወጣው ግን ከልብ ይወጣል፤ ሰውን የሚያረክሰውም እርሱ ነው። ክፉ ማሰብ፥ ሰው መግደል፥ ማመንዘር፥ ዝሙት ማድረግ፥ መስረቅ፥ በሐሰት መመስከር የሰውን ስም ማጥፋት፥ ይህ ሁሉ ከሰው ልብ ይወጣል።
Vergelyk
Verken የማቴዎስ ወንጌል 15:18-19
2
የማቴዎስ ወንጌል 15:11
ሰውን የሚያረክሰው ከአፍ የሚወጣው ነው እንጂ ወደ አፍ የሚገባው አይደለም!”
Verken የማቴዎስ ወንጌል 15:11
3
የማቴዎስ ወንጌል 15:8-9
‘ይህ ሕዝብ በአፉ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ ሰው ሠራሽ ወግና ሥርዓትን፥ እንደ ሕግ አድርጎ እያስተማረ በከንቱ ያመልከኛል።’ ”
Verken የማቴዎስ ወንጌል 15:8-9
4
የማቴዎስ ወንጌል 15:28
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ “አንቺ ሴት እምነትሽ! ትልቅ ነው፤ ስለዚህ እንደ ፍላጎትሽ ይሁንልሽ!” አላት። የሴትዮዋም ልጅ በዚያኑ ሰዓት ዳነች።
Verken የማቴዎስ ወንጌል 15:28
5
የማቴዎስ ወንጌል 15:25-27
ሴትዮዋ ግን ቀርባ በእግሩ ሥር ተንበረከከችና “ጌታ ሆይ! እባክህ እርዳኝ!” አለችው። ኢየሱስም “የልጆችን እንጀራ ወስዶ ለውሾች መጣል የተገባ አይደለም” አለ። እርስዋም “ጌታ ሆይ! እርግጥ ነው፤ ነገር ግን ውሾችም ከጌቶቻቸው ማእድ የሚወድቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ” አለች።
Verken የማቴዎስ ወንጌል 15:25-27
Tuisblad
Bybel
Leesplanne
Video's